The Bible Way to Heaven (Amharic)

Video

October 17, 2015

በደህንነት ላይ መፅሃፍ ቅዱስ ግልፅ ነው፡፡ ጥሩዎች ስለሆናችሁ አይደለም፡፡ ብዙ ሰዎች

ራሳቸውን መልካም እንደሆኑ አድርገው ያስባሉ በዚህም መንግስተ ሰማይ እንደሚገቡ ያስባሉ፡፡

ነገር ግን መጽሃፍ ቅዱሰ እንዲህ ይላል “ሁሉም ሃጢአትን ሰርተዋልና የእግዚአብሄርም ክብር ጎድሎአቸዋል፡፡”

መጽሃፍ ቅዱሰ እንዲህ ይላል “እንዲህ ተብሎ እንደተፃፈ ፃድቅ የለም አንድ ስንኳ” እኔ ጻድቅ አይደለሁም፡፡

እናንተ ጻድቃን አይደላችሁም፡፡ መልካም ስራችን መንግሰተ ሰማያት

የሚያስገባን ቢሆን ኖሮ ማንም አይገባም ነበር፡፡

.ሃጢአተኛ መሆናችሁን እመኑ

ደግሞም የእግዚአብሄር ቃል ራዕይ ፡ ላይ እንዲህ ይላል፡ “ነገር ግን ፈሪዎች፣ የማያምኑ፣ ርኩሶች፣

ነፍሰ ገዳዮች፣ አመንዝሮች፣ አስማተኞች፣ ጣኦት አምላኪዎች፣ ውሸተኞች ሁሉ ዕጣ ፈንታቸው

በዲንና በእሳት ባሕር ውስጥ መጣል ይሆናልና፡፤ ይህም ሁለተኛው ሞት ነው፡፡”

እኔ ከዚህ በፊት ዋሽቻለሁ፤ ሁሉም ሰው ከዚህ በፊት ዋሽቷል፡፡ ሁላችንም ሃጢአትን ሰርተናል፡፡

ከውሸት የበለጡ ክፋቶችን አድርገናል፡፡ እንጋፈጠው ሁላችንም ገሃነም ነበር የሚገባን፡፡

.የሃጢአት ቅጣት ምን እንደሆነ እንረዳ

ነገር ግን የእግዚአብሄር ቃል እንዲህ ይላል፡ እንዲህ ይላል፡ “ነገር ግን ገና ኀጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ

ስለ እኛ ሞተ፤ ይህም እግዚአብሄር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያሳያል፡፡”

ስለዚህ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለወደደን ወዲዚህ አለም መጣ፡፡ የእግዚአብሄር ቃል ሲናገር በስጋ የተገለጠ አምላክ ነበር፡፡

እግዚአብሔር የሰውን አምሳል ወሰደ፡፡ ሃጢአት የሌለበትን ህይወት ኖረ፤ ምንም ዓይነት

ሃጢአት አልሰራም፡፡ እርግጥ ነው መቱት፣ ተፉበት፣ በመስቀል ላይ ሰቀሉት፡፡

ቃሉ እንደሚናገር በመስቀል ላይ በነበረበት ጊዜ የሁላችንም ኃጢአት በስጋው ተሸከመ፡፡

ስለዚህ ማንኛውም እኔና እናንተ የሰራነው ሃጢአት በክርስቶስ ላይ ሆኖ ለእኛ ተሰቀለ፤

ስለእኛ ሃጢአት ተቀጣ፡፡ እርግጥ ነው በመስቀል ላይ ሲሞት

አካሉን ወሰዱትና በመቃብር ውስጥ አኖሩት፡፡ ነፍሱ ለ ቀን እና

ለ ሌሊት በሲኦል አደረ፡፡ ከሶስት ቀን በኋላም ከሞት ተነሳ፡፡

ለደቀመዛሙርቱ በምስማር የተቸነከሩትን የእጆቹን ምልክት አሳያቸው፡፡ ኢየሱስ ለሁሉም የሰው ዘር

እንደሞተ ቅዱስ ቃሉ ይነግረናል፤ ይህም ለእኛ ሃጢአት ብቻ ሳይሆን ለሰው ልጆች ሁሉ ሃጢአት እንደሞተ ይናገራል፡፡

ነገር ግን ለመዳን ማድረግ ያለብን ነገር አለ፡፡ ይህን ጥያቄ መጽሃፍ ቅዱስ ላይ አለ፡-

የሐዋ.ስራ ፡ “እናንት ሰዎች፤ እድን ዘንድ ምን ላድርግ?” አላቸው፡፡ እነርሱም፣

“በጌታ በኢየሱስ እመን፤ አንተም ቤተ ሰቦችህም ትድናላችሁ” አሉት፡፡

ይኸው ነው፡፡ “ቤተ ክርስቲያንን ተቀላቀልና ትድናለህ፣ ተጠመቅና ትድናለህ፣ ጥሩ ሕይወት ኑርና ትድናለህ፣

ሁሉንም ሃጢአትህን ተናዘዝና ትድናለህ ” አላለውም፡፡ ያለው “እመን” ነው፡፡

.ኢየሱስ ላንተ እንደሞተ፣ እንደተቀበረ፣ ከሞትም እንደተነሳ እመን፡፡

መጽሃፍ ቅዱስ ውስጥ ካሉ በጣም ከሚታወቁ ጥቅሶች ውስጥ እንዲያውም የበለጠ፣ ሁሉም ሰዎች የሰሙት፣

በብዙ እቃዎች ላይ ተፅፎ የምናገኘው ጥቅስ የዮሃንስ ወንጌል ፡ ነው፡፡

በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ

እንዳይጠፋ እግዚአብሄር አንድያ ልጁን እስከ መስጠት ድረስ ዓለምን እንዲሁ ወዶአልና፤

የዘላለም ማለት ዘላለም ነው፡፡ ማለቂያ የሌለው ማለት ነው፡፡ ኢየሱስ ሲናገር፡

የዘላለም ሕይወት እሰጣቸዋለሁ፤ ከቶ አይጠፉም፤ ከእጄም ሊነጥቃቸው የሚችል ማንም የለም፡፡

መፅሃፍ በዮሃንስ ወንጌል ፡ ላይ እንዲህ ይላል፡ እውነት እውነት እላችኋለሁ በእኔ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፡፡

ስለዚህ በኢየሱስ ክርስቶስ ካመንክ መፅሃፍ ቅዱስ እንደሚናገረው የዘላለም ሕይወት አለህ፡፡

ለዘላለም ትኖራለህ፡፡ ደህንነትህን ልታጣው አትችልም ዘላለማዊ ስለሆነ፤ የዘላለም ህይወት ነው፡፡

አንዴ ከዳንክ በኋላ፣ አንዴ በርሱ ካመንክ በኋላ፣ ለዘላለም ድነሃል፤

በማኝኛውም ሁኔታ ቢሆን ደህንነትህን አታጣም፡፡

ምንም እንኳን ወደውጭ ወጥቼ አንዳንድ አሰቃቂ ሃጢአቶችን ብሰራ፣

እዚሁ ምድር ላይ እያለሁ እግዚአብሄር ይቀጣኛል፡፡ ዛሬ አንድ ሰው ብገድል

እግዚአብሄር ለሰራሁት ሃጢአት ቅጣትን እንዳገኝ ያደርገኛል፤ ወደ እስር ቤት እገባለሁ ወይም የመጨረሻ ቅጣት በሆነው

በስጋዊ ሞት ቅጣት እቀጣለሁ ወይም ደግሞ አለም በምታደርስብኝ በማንኛውም ቅጣት እቀጣለሁ፡፡

እግዚአብሄር ከዚህም በበለጠ ቅጣት እንድቀጣ ሊያደርገኝ ይችላል፡፡ ነገር ግን ወደ ሲኦል አልገባም፡፡

ወደ ሲኦል ሊያስገባኝ የሚችል ምንም ነገር ማድረግ አልችልም፤ ወደ ሲኦል ገባሁ ማለት እግዚአብሄር ዋሽቷል ማለት ነው ምክንያቱም

በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዳለው ቃል ገብቷልና፡፡ በእኔ የሚያምን እና የሚኖር ከቶ አይሞትም ብሎአል፡፡

ለዚህም ነው ከባድ በደል የሰሩ ሰዎች በመጽሃፍ ቅዱስ ውስጥ እንደ ምሳሌ የተጻፉልን፡፡

ሆኖም እነዚህ ሰዎች ለእግዚአብሄር መንግስቱ በቁ፤ እንዴት? በጣም መልካም ሰዎች ስለሆኑ ነው? አይደለም

በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስላመኑ ነው፤ ሃጢአታቸው ተሸሮላቸዋል፡፡ በዚህ ዓለም ዕይታ መልካም ሕይወት የኖሩ

ወይም በእርግጥ ጥሩ የሚባል ሕይወት ኖረው ነገር ግን

በክርስቶስ ያላመኑ ሰዎች ለሃጢአታቸው ቅጣት ሲኦል ይወርዳሉ፡፡

. ክርስቶስ ብቻውን የግል አዳኝህ አድርገህ እመን

ዛሬ ላቀርበው በምፈልገው በዚህ አንድ ሃሳብ እንዳጠቃልል ፍቀዱልኝ፡፡

ከደቀመዛሙርቱ አንዱ ኢየሱስን የጠየቀው ጥያቄ ነበር፡፡ ጥያቄው እንደሚከተለው ነበር፡

የሚድኑት ጥቂት ናቸውን? ጥሩ ጥያቄ ነው፤ አይደል? ብዙ ሰዎች ይድናሉ?

ወይስ የሚድኑት ጥቂቶቹ ናቸው? በዚህ ምድር ካሉ ሰዎች ውስጥ ብዙዎቹ

መንግስተ ሰማይ ይገባሉ ብሎ የሚያስብ ማነው? መልሱ ምን ይመስላችኋሃል? ኢየሱስ በማቴዎስ ላይ መልሶታል፡

ኢየሱስ በማቴዎስ ላይ መልሶታል፡ በጠባቡ ደጅ ግቡ፤ ወደ ጥፋት የሚወስደው ደጅ ሰፊ፣

መንገዱም ትልቅ ነውና፣ ወደ እርሱም የሚገቡ ብዙዎች ናቸው፡፡

ወደ ሕይወት የሚወስደው ደጅ የጠበበ፣ መንገዱም የቀጠነ ነውና፣

የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው፡፡ ቀጥሎም እንዲህ አለ፡ በሰማይ ያለውን የአባቴን ፈቃ የሚያደርግ እንጂ፤

ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ የሚለኝ ሁሉ መንግስተ ሰማያት የሚገባ አይደለም፡፡

በዚያን ቀን ብዙዎች ጌታ ሆይ በስምህ ትንቢት አልተናገርንም፣

በስምህስ አጋንንትን አላወጣንም፣ በስምህስ ብዙ ታአምራት አላደረግንም?

ይሉኛል፤የዚያን ጊዜም፡፡ አላወቅኋችሁም፤

እናንተ ዓመፀኞች ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ፡፡

ከሁሉም በፊት ይህ ዓለም በክርስቶስ እንደሚምን አይናገርም፡፡ ደስ የሚለው፣

ክፍል ውስጥ ያለ አብዛኛው ሰው በኢየሱስ ያምናል፡፡ ነገር ግን አብዛኛው

የዚህ አለም ክፍል በኢየሱስ አያምንም፡፡ ግን እግዚአብሄር እያስጠነቀቀ ያለው ነገር በኢየሱስ እናምናለን

ከሚሉት ሰዎች ውስጥ ብዙዎቹ “እነዚህን ሁሉ

አስደናቂ ስራዎች ሰርተናል፡፡ ለምን አንድንም?” ብለው ሲጠይቁት

“አላወቅኋችሁም ከእኔ ራቁ” ይላቸዋል፡፡ ምክንያቱም ደህንነት በስራ ስለማይገኝ ነው፡፡

የራሳችሁ ስራዎች ያድኑኛል ብላችሁ ካመናችሁ፣

በመጠመቃችሁ ምክንያት መንግስተ ሰማያት እገባለሁ ብላችሁ ካሰባችሁ ወይም

“መቼም እኔ እንደማስበው ለመዳን መልካም ሕይወት መኖር አለብህ፤ ትዕዛዛቱን መጠበቅ አለብህ፤ ቤተ ክርስቲያን መሄድ አለብህ፤

ከሃጢአትህ መመለስ አለብህ…” ብላችሁ ካሰባችሁ፣ የራሳችሁን ስራዎች ካመናችሁ፤

አንድ ቀን ኢየሱስ እንዲህ ይላችኋል፡ “አላወቅኋችሁም ከእኔ ራቁ”

ኢየሱስ በመስቀል ላይ በሰራው ስራ ላይ እምነት ሊኖራችሁ ያስፈልጋል፡፡

ለእናንተ ሲሞት፣ ሲቀበርና ከሞት መነሳቱ ላይ ልታምኑ ይገባል፡፡ ይሄ የመንግስተ ሰማያት መግቢያ ትኬታችሁ ነው፡፡

“እንዴ እኔ በጣም ጥሩ የምባል ክርስቲያን ስለሆንኩና

እነዚህ ሁሉ መልካም ስራዎችን ስለማደርግ መንግስተ ሰማያት እግባለሁ” ብላችሁ ካመናችሁ፤ “ከእኔ ራቁ” ይላችኋል፡፡

ጌታ የተናገረውን ልብ በሉ፡ “አላወቅኋችሁም ከእኔ ራቁ”፤ “አውቃችሁ ነበር” አላለም

ምክንያቱም አስቀድሜ እንደገለጽኩት አንዴ ካወቃችሁ የዘላለም ነው፤ ዘላለማዊ ነው፡፡

አንዴ ካወቃችሁ ለዘላለም ድናቹሃል፡፡

ሲኦል ከገባችሁ የገባችሁበት ምክንያት ፈፅሞ ስላላወቃችሁ ነውና “አላወቅኋችሁም ከእኔ ራቁ” ይላል፡፡

አንዴ ካወቃችሁ አወቃችሁ ነው፤ ልክ ልጆቼ ሁሉ ጊዜ ልጆቼ እንደሚሆኑት ማለት ነው፡፡

ዳግም ስትወለዱ፣ ልጁ ስትሆኑ ሁሉ ጊዜ ልጆችሁ ናችሁ፡፡

ምናልባት አስቸጋሪ ልጅ ትሆኑ ይሆናል፤ በዚህ ምድር ላይ በእግዚአብሄር በከባድ ሁኔታ እየታረመ ያለ ሰው ልትሆኑ ትችላላችሁ፤

በዚህ በታች ያላችሁን ሕይወት ልታበላሹ ትችላላችሁ ነገር ግን የላይኛውን ልታበላሹ አትችሉም፡፡ ድናችኋሃል፡፡

የተጠናቀቀ ነገር ነው፤ ስለዚህ ይህ

ስለ መጨረሻው ዘመን ላቀርብላችሁ የምፈልገው ዋና ነገር ነው፡፡

ስለ ደህንነት ወይም ስለ መጨረሻው ዘመን ጥያቄዎች የተወሰነ ደቂቃ አለን፡፡

ውድ ኢየሱስ፤ ሃጢያተኛ እንደሆንኩ አውቃለሁ፤ ለዚህም የሲኦል ፍርድ እንደሚገባኝ አውቃለሁ፤

ነገር ግን አንተ ለኔ በመስቀል ላይ እንደሞትክልኝ እና እንደተነሳህልኝ አመናለሁ፡፡

እባክህ አሁን አድነኝ፤ የዘላለም ሕይወትን ስጠኝ፡፡ አንተን ብቻ አምናለሁ ኢየሱስ፤ አሜን፡፡

 

 

 

mouseover