"After the Tribulation" full movie with Amharic subtitles

Watch Video

October 12, 2015

"ጉበኛዉ ግን ሰይፍ ሲመጣ ቢያይ መለከቱንም ባይነፋ ህዝቡንም ባያስጠነቅቅ፤

ሰይፍም መጥቶ አንድ ሰዉ ከእርሱ ቢወስድ፣ እርሱ በኋጢአቱ ተወስዶአል፤

ደሙን ግን ከጉበኛዉ እጅ እፈልጋለሁ፡፡" ትንቢተ ሕዝቅኤል ፡

ማክሰኞ ማለዳ አካባቢ ነዉ፤ መስከረም ቀን ዓ.ም፡፡

- ደስ የሚል ማለዳ ነበር፤ አልነበረም እንዴ? ምርጥ የበልግ ማለዳ ነዉ፡፡

በመስከረም ፣ ዓ.ም አለም ተለወጠች፡፡ "የነፃዉ መሬት" አሁን

"የጭቁኑ መሬት" ሆነ፡፡ በአንድ ዘመን ተከብራ የነበረቸዉ የኛ ዩናይትድ ስቴትስ ህዝቦች ለሰላም/ፀጥታ ሲሉ ነፃነታቸዉን ሸጡ፡፡

ነገር ግን ይህ ሁሉ ታስቦበት የተደረገ ነዉ?

"ህዳር ቀን ዓ.ም.፤

ዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ በድንገት ሆን-ተብሎ ጥቃት ደረሰባት፡፡"

በዚያን ቀን፤ በዚያ መጥፎ ቀን በተደረጉ ክስተቶች ዙርያ በርካታ ጥያቄዎች ይነሳሉ፡፡ ነገር ግን በእርግጥ የምናዉቀዉ አንድ ነገር፡

ያልተጠበቀዉ የፒርል ሀርበር ጥቃት በርካታ ክስተቶች እንዲቀጣጠሉ ምክንያት ሆኗል፡፡

ያም በመጨረሻ ወደ አንድ አለም መንግስት ይመራናል፡፡

"ጃፓን ይህንን በክህደት ጦርነት ጀምራለች፡፡ እኛም በድል ማጠናቀቅ ይኖርብናል፡፡"

ከሁለተኛዉ የአለም ጦርነት ፍፃሜ በኋላ የተባበሩት መንግስታት ተቋቋመ፡፡ እናም ወደ አንድ የአለም መንግስት የመሄዱ ነገር

እየተቀላጠፈመጣ፡፡ እያንዳንዱ ጦርነት መጽሐፍ ቅዱስ "የአለም ፍፃም" ወደ ሚለዉ በአንድ እርምጃ ያቀርበናል፡፡

ኬላዎች በየቦታዉ እየተሰሩ ነዉ፤ ፓሊሶች

በዩናይትድ ስተቴስ ህዝቦች ላይ ልጓሟቸዉን በማጠንከር ላይ ናቸዉ፡፡

እናም የመጽሐፍ ቅዱስን ትንቢት ለሚረዱ ቀጥሎ የሚከሰተዉ ነገር እንግዳ አይሆንም፡፡

በመጪዉ ዘመናት ዉስጥ ሰዎች ሁሉ ለመግዛት ወይም ለመሸጥ የግድ ምልክት ማድረግ እንደሚጠበቅባቸዉ

የኪንግ ጀምስ እትም መጽሐፍ ቅዱስ ይገልጻል፡፡ የአሁኑኢኮኖሚያዊ ስርዓታችን ሲወድቅ

እና ቴክኖሎጂ ሲስፋፋ ጥሬ-ገንዘብ ጊዜ ያለፈበት እየሆነ መጥቷል፡፡ ጥሬ-ገንዘብ የማይጠቀምን ህብረተሰብ የምናይበት

ጊዜ ሩቅ አይደለም፡፡ በእርግጥም አሁን ተግባራዊ በመደረግ ላይ ነዉ፡፡ ምንም እንኳን የሃይማኖት መሪዎች ይህንን ቢክዱም፤

የጨለማዉ መንግስት ሰዎች አዲሱን የአለም አገዛዝ ለማምጣት ሌትተቀን በመስራት ላይ ናቸዉ፡፡

መጨረሻዉ በከፍተኛ ፍጥነት መሆኑን ማየት እንችላለን፤ እንዲሁም ለፀረ-ክርስቶስ መምጣት መድረኩ እየተዳለደለ ነዉ፡፡

የእኛን የአሜሪካን ህገ-መንግስት በመናድ ላይ ያሉትን እና ይህንን አለም-አቀፋዊ የአስተዳደር ስርዓት

የሚስተዋዉቁትን አካላት ድምፅ መስማት ይቻላል፡፡ "…አዲስ የአለም ስርዓት…"

እናም ይህ ጉዳይ ከጫፍ በደረሰበት በዚህ ጊዜ ይህ ፊልም ከመቼዉም ጊዜ ይልቅ ጠቃሚ ነዉ፡፡

ሰይጣን ለፀረ-ክርስቶስ ለመዘጋጀት ሲል አንድ የአለም መንግስት እና አንድ የአለም ሃይማኖት ለማቋቋም

በስዉር በመስራት ላይ ይገኛል፤ እንዲሁም ዘመናዊ ወንጌላዊያን ክርስቲያኖችን ለማሳት ችሏል፡፡

ይህም ታላቁ ፈተና ከመምጣቱ በፊት ከዚህች ምድር እንደሚወሰዱ እያሳመናቸዉ ነዉ፡፡

ይህ አስተምህሮ "የቅድመ-ፈተና መነጠቅ" ይባላል፤ እናም ክርስቶስ በማንኛዉም ሰዓት ሊመለስ እንደሚችል ያስተምራል፡፡

እንዲሁም ስለአመጣጡ ምንም አይነት ምልክቶች የሉም ይላል፡፡ ከዚህም ኑፋቄ የተነሳ

በርካታ ክርስትያኖች መጽሐፍ-ቅዱስ ስለሚመጡት ነገሮች ያስጠነቀቀን ጉዳዮች ላይ ምንም አልተዘጋጁም፡፡

ምንም እንኳን መጽሐፍ ቅዱስ በማቴዎስ እና በሌሎች ቦታዎች ላይ መነጠቅ የሚሆነዉ ከመከራዉ በኋላ እንደሆነ

በግልፅ የሚነግረን ቢሆንም ትላልቅ ስም ያላቸዉ ሰባኪዎች፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጆች እንዲሁም እንደ ሌፍት ቢ ሃይንድ ያሉ

ታዋቂ ፊልሞች እንኳን ሳይቀሩ መነጠቅ በማንኛዉም ሰዓት ሊከሰት እንደሚችልና መጠበቅ እንዳለበት ለህዝቡ ያስምራሉ፡፡

እናም ብዙዎቹ ክርስትያኖች በግላቸዉ መጽሐፍ ቅዱስን ሙሉ በሙሉ ካለማንበባቸዉ የተነሳ፤

የቅድመ-መከራ መነጠቅ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የሌለ እና ማጭበርበር መሆኑን የተገነዘቡት ጥቂቶች ናቸዉ፡፡

ነገር ግን ይህ የቅድመ-መከራ መነጠቅ አስተምህሮ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ካልተገለፀ ከየት መጣ?

ከመከራዉ በኋላ

ስሜ ስቴቨን አንደርሰን ነዉ፤ በፌዝፉል ወርድ መጥምቃዊያን ቤተክርስትያን በአሪዞና በሚገኘዉ አጥቢያ ቤተ-መቅደስ መጋቢ ነኝ፡፡

እናም እኔ ስለ ቅድመ-መከራ መነጠቅ ህዝቦችን ለማስተማር በተልእኮ ላይ ነኝ፡፡

ምክንያቱም ይህ በድንቁርና ላይ መሰረት ያደረገ አስተሳሰብ ነዉ፡፡ ስለዚህም ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን ቢያዩና…

ሀቁን ቢመለከቱ መነጠቅ በእርግጥም ከታላቁ መከራ በኋላ መሆኑን የሚረጋግጥ

መደምደምያ ላይ መምጣት አይከብዳቸዉም ብዬ አምናለሁ፡፡

ስሜ ሮጀር ጂሜኔዝ ነዉ፤ በሳክራሜንቶ ካሊፎርኒያ በሚገኘዉ የቬሪቲ መጥምቃዉያን ቤተክርስትያን መጋቢ ነኝ፡፡

ደግኩት በክርስትያን ቤት ዉስጥ ሲሆን ስለ ቅድመ-መከራ መነጠቅ እድሜ ልኬን ስማር ቆይቻለሁ፡፡

ስለዚህም ስለ ጉዳዩ ለመጠየቅ ምንም ምክንያት አልነበረኝም፡፡ ሰባኪዎች የነገሩን ያንን ነዉ፤

እናም እኔም በዚያ ደረጃ ወሰድኩት፡፡ ነገር ግን እኔ ለዚህ አስተምህሮ ተጋልጬ ስለነበረ

ምን ያህል መጽሐፍ ቅዱሳዊ እንዳልሆነ ማየት ጀመርኩ፡፡ ስለዚህም መጽሐፍ ቅዱስን ማስተማር

እና እዉነቱን ማዉጣት እንዳለብን ይሰማኛል፡፡

መጋቢ አንደርሰን፡ የቅድመ-መከራ መነጠቅ አስተምህሮ በጣም አዲስ ነዉ፡፡ ከ ዓ.ም. በፊት

ማንም ይህንን ትምህርት ስለ ማስተማሩ ምንም አይነት ማስረጃ የለም፡፡

መጋቢ ጂሜኔዝ፡ በታሪክ ዉስጥ ዎቹ በጣም የቅርብ ጊዜ መሆኑን መረዳት ይኖርብናል፡፡

ከክርስቶስ ልደት በኋላ በሺህ ለሚቆጠሩ አመታት በተሃድሶ ዉስጥ አልፈናል እንዲሁም በርካታ ነገረ-መለኮታዊያንን አሳልፈናል፤

ምንም እንኳን በእነ ማርቲንሉተር፣ ወይም ጆን ካልቪን ወይም በማንም ሌላ ሰዉ ቢስማሙም ባይስማሙም፤

ዋናዉ ሀቅ ከ ዓ.ም. በፊት በሺዎች የሚቆጠሩ መፃህፍት፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ጥናታዊ-ፅሁፎች

እንዲሁም በርካታ ስብከቶች የተደረጉ መሆኑ ነዉ፡፡

መጋቢ አንደርሰን፡ እናም እኔ እያልኩ ያለሁት ይህንን አስተምህሮ ከሚያስተምር ከየትኛዉም አይነት ክርስትና፣

ከማንኛዉም የሀይማኖት ወገን የተገኘ ምንም አይነት ማስረጃ የለም፡፡

መጋቢ ጂሜኔዝ፡ ታሪካዊ ዳራዉን ስትመለከት ጥያቄዉን ራስህን መጠየቅ አለብህ፡፡

"የቅድመ-መከራ መነጠቅ ስሮች ምንድን ናቸዉ?"

ዶ/ር ሮናልድ ራስሙሴን፡ ከመጀመሪያዎቹ የቅድመ-መከራ አስተሳሰብ ፈጣሪዎች መካከል ጆን ኔልሰን ዳርቢ አንዱ ነዉ፡፡

በዎቹ ዓ.ም. "ሚስጥራዊዉ መነጠቅ" በሚል ይህን አስተምህሮ ማስተማር ጀመረ፡፡

ከዚያም ሙሉ የምዕራፉ ቁጥሮችን አዉጥቶ፣ ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮዎችን አበላሽቶ እና

የኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምፅዓትን በተመለከተ የተቀመጡ ቁልፍ ምንባቦችን ነካክቶ በኋላ የራሱን ትርጉም

መጽሐፍ ቅዱስ ሊያሳትም ይችል ነበር፡፡ ጆን ኔልሰን ዳርቢ "የዘመናዊ ክህደት አባት" ተብሎ የሚታወቅ ሲሆን

የቅድመ-መከራ መነጠቅ ፅንሰ ሃሳቡን በኛዉ መቶ ክፍለ ዘመን ሁሉ አስተዋዉቋል፡፡

በኋላ የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ማተሚያ ቤት የስኮፊልድን ማጣቀሻ መጽሐፍ ቅዱስ

(ይህም የዳርቢን ሚስጥራዊ መነጠቅ የሚሰብክ መጠነኛ ማስታወሻዎችን የያዘ ነዉ) ባሳተመበት ጊዜ

ይህ የቅድመ-መከራ መነጠቅ በመጥምቃዉያን መካከል ሰፋ ያለ ተቀባይነትን አገኘ፡፡ እነዚህ ማስታወሻዎች

በርካታ ክርስቲያኖች ይህንን አስተምህሮ እግዝአብሄር ራሱ የተናገራዉ አድርገዉ እንዲቀበሉት አድርጓቸዋል፡፡

መጋቢ አንደርሰን፡ ዲያብሎስ ይህን የቅድመ-መከራ መነጠቅ አስተምህሮ ለማስፋፋት ከምንም በላይ

የስኮፊልድን የመጽሐፍ ቅዱስ ማጣቀሻ እንደ መሳርያ ተጠቅሞበታል፡፡ ከየት እንደመጣ ማወቅ ትፈልጋላችሁ?

ወደ ቤተ ክርስቲያናት የገባዉ በዚህ መልክ ነዉ፡፡ ይህ መጋቢዎች የተጠመዱበት ቦታ ነዉ፡፡

ከመጽሐፍ ቅዱስ የሚመጣ አይደለም፡፡በእርግጠኝነት ከኢየሱስ ክርስቶስ አንደበት የመጣም አይደለም!

ነገር ግን ከስኮፊልድ አንደበት መጥቷል፡፡ የስኮፊልድ ማስታወሻዎች ወደ ቅድመ-መከራ መነጠቅ ይጠቁማሉ፡፡

እና በእርግጥም በመጽሐፍ ሳይፃፍ እንደተፃፈ አድርገዉ አንባቢዉን ወደ ማሳመን ይመሩታል፡፡

የስኮፊልድ መጽሐፍ ቅዱስ ወደ በርካታ ሴሚነሪዎች እና ኮሌጆች እንዲሁም ወደ

በርካታ ወጣት ሰባኪ ልጆች በመላኩ የተነሳ እነርሱ የቅድመ-መከራ መነጠቅን

እንደ ሃቅ ተቅብለዉ መስበክ ጀምረዋል፡፡

ዶ/ር ሮናልድ ራስሙሴን፡ በአይቀሬዉ መነጠቅ ዙርያ የተሰሩ የልብ-ወለድ ስራዎች

በዶን ቶምፕሰን ፊልሞች አማካኝነት የሰባዎቹን ትዉልድ መድረስ ችለዋል፡፡

"በድንገት እና ያለምንም አይነት ማስጠንቀቂያ በበርካታ ሺህዎች ምናልባትም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች እንዲሁ ተሰዉረዋል፡፡

በእነዚህ መጥፋቶች ዙርያ የተገኙት ጥቂት የአይን ምስክሮች ግልፅ አልነበሩም፡፡

ነገር ግን በአንድ ነገር እርግጠኛ መሆን ይቻላል፡፡ ትናንት ማታ በዚህች ምድር ላይ ሲኖሩ የነበሩ በሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ዛሬ ጠዋት አልተገኙም፡፡

ዶ/ር ሮናልድ ራስሙሴን፡ የቶምፕሰን ሶስት ተከታታይ ልብ አንጠልጣይ ፊልሞች አዲስ የአስርዎችን ታዳጊዎች ትዉልድ በማሳመን በኩል ትልቅ ሚና ተጫዉቷል፡፡

ከመጀመሪያዉ ክፍል አንስቶ ከ ሚሊዮን በላይ ሰዎች "ኤ ቲፍ ኢን ዘ ናይት/ የማታ ሌባ" የሚለዉን አይተዉታል፡፡

በ እ.አ.አ. ቲም ዴልሃዉስ የቲም ላሃዬን እና የጄሪ ጄንኪንስን ራዕያዊ ረዥም ልቦለድ "ሌፍት ቢሃይንድ/ኋላ የቀረ" አሳተመ፡፡

መጋቢ አንደርሰን፡ ይህ ልቦለዳዊ ተከታታይ ፊልም ሲሆን ሁሉም ሰዉ ሲጠፋ እና ማንም ሰዉ የት እንደሄዱ የማይዉቅበትን እሳቤ ያሳያል፡፡

መኪኖች እርስ በእርሳቸዉ ይጋጫሉ፤ አይሮፕላኖች ይጋጫሉ ምክንያቱም አብራሪዉ ተወስዷል፡፡

እናም ይህ የቅድመ-መከራ መነጠቅ ድራማዊ ገለፃ የአሜሪካን ባህል አንዱ አካል ሆኗል፡፡

እናም ሰዎች እዉነት አድርገዉ ይቀበሉታል፡፡ እና….አህ…..

የማይረባ ፊልም ነዉ፡፡

ዶ/ር ሮናልድ ራስሙሴን፡ ሌፍት ቢሃይንድ በመላዉ አለም እስከ ሚሊዮን ቅጂዎች ተሽጧል፡፡

ተከታታይ መፅሀፍትን ወልዷል፤ እንዲሁም እስከ አሁን ሶስት ተቀራራቢ ፊልሞችንም እንዲሁ፡፡

ነገር ግን ሌፍት ቢሃይንድ የልቦለድ ስራ ነዉ፡፡ ስለ መነጠቅ እዉነተኛዉን ነገር ለመማር መፅሀፍ ቅዱስ ራሱን መመርመር አለብን፡፡

መጋቢ አንደርሰን፡ ኛ ተሰሎንቄ ምዕራፍ ቁልፍ የመነጠቅ ምንባብ ነዉ፡፡

እናም በኛ ተሰሎንቄ ምዕራፍ ላይ ምናልባትም ስለ መነጠቅ በጣም ታዋቂ የሆነዉን ፅሁፍ እናገኛለን፡፡

መጋቢ አንደርሰን፡ ማንም ሰዉ ይህ ምንባብ ስለመነጠቅ እንደሚናገር ይስማማል፡፡

ይህ ከመጽሐፍ ቅዱስ ዉስጥ ስለ ኢየሱስ በደመና መምጣት እና እኛም ከእርሱ ጋር ለመገናኘት ወደ ላይ እንደምንነጠቅ የሚናገር በጣም ግልፁ አስተምህሮ ነዉ፡፡

በመጽሐፍ ቅዱስ በቁጥር ላይ እንዲህ ይላል፡

(ኛ ተሰሎንቄ ፡) "ነገር ግን፤ ወንድሞች ሆይ፤ ተስፋ እንደሌላቸዉ እንደሌሎች እንዳታዝኑ፤

አንቀላፍተዉ ስላሉት ታዉቁ ዘንድ እንወዳለን፡፡"

(ኛ ተሰሎንቄ ፡)" ኢየሱስ እንደ ሞተና እንደተነሳ ካመንን እንዲሁም

በኢየሱስ ያንቀላፉትን እግዝአብሄር ከእርሱ ጋር ያመጣቸዋልና፡፡"

መጋቢ አንደርሰን፡ እዚህ ጋር የሚናገረዉ ነገር ምንድን ነዉ፡ ስለ ክርስቲያኖች፣ ስለሞቱት አማኞች፣ በክርስቶስ ስላንቀላፉት፣

ከክርሰቶስ ጋር ለመሆን ቀደመዉ ስለሄዱት ስለእነርሱ አላዋቂ መሆን እንደሌለባቸዉ እየተናገራቸዉ ነዉ፡፡

እንዲህ ይላል፡ ስለ እነዚህ ወንድሞች አላዋቂ እንድትሆኑ አልፈልግም፡፡

ምክንያቱም ተስፋ እንደሌላቸዉ እንድታዝኑ አልፈልግም፡፡

የዳነዉን የምትወዱትን ሰዉ እንደገና እንደምታገኙት እንድታዉቁ እፈልጋለሁ፡፡

እንደገና ታገኛቸዋላችሁ ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ሲመጣ እነርሱንም ይዞ ይመጣልና፡፡

በክርስቶስ ሆነዉ የሞቱት ቀድመዉ ይነሳሉ እናም ሌሎች ነገሮች ይሆናሉ፡፡ ለዚህም ነዉ በቁጥር እንዲህ የሚለዉ፡

(ኛ ተሰሎንቄ ፡) "ስለዚህ እርስ በርሳችሁ በዚህ ቃል ተጽናኑ፡፡"

መጋቢ አንደርሰን፡ ለዚህም ነዉ በጣም ታዋቂ የሆነዉን ይህንን ምንባብ በቀብር ስነ-ስርዓቶች ላይ የምትሰሙት፡፡

እኔ በተገኘሁባቸዉ በርካታ የቀብር ስነ-ስርዓቶች ሰዎች በእነዚህ ቃላት እርስ በእርሳቸዉ ሲጽናኑ አይቻለሁ፡፡

ስለዚህም እነዚህ ያለፉትን ሰዎች ዳግም እንደምናያቸዉ ያስቀመጠዉን እዉነት በእያንዳንዱ ቁጥር ላይ ያወሳናል፡፡

(ኛ ተሰሎንቄ ፡) "በጌታ ቃል የምንላችሁ ይህ ነዉና፤

እኛ ሕያዋን ሆነን ጌታ እስኪመጣ ድረስ የምንቀር ያንቀላፉትን አንቀድምም፤"

(ኛ ተሰሎንቄ ፡) "ጌታ ራሱ በትእዛዝ በመላእክትም አለቃ ድምፅ በእግዚአብሄርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና፤

በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመዉ ይነሳሉ፤"

(ኛ ተሰሎንቄ ፡) ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረዉ፤ ጌታን በአየር ለመቀበል ከእነርሱ

ጋር በደመና እንነጠቃለን፤ እንዲሁም ሁልጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናለን፡፡

(ኛ ተሰሎንቄ ፡) "ስለዚህ እርስ በርሳችሁ በዚህ ቃል ተጽናኑ፡፡"

መጋቢ አንደርሰን፡ ስለዚህ አገባቡን ከተረዳችሁ የምትወዷቸዉን ዳግም እንደምታይዋቸዉ ማፅናኛን ይሰጣል፡፡

እንዲህም ይላል፤ እንደገና ታያቸዋላችሁ ፤ምክንያቱም ኢየሱስ ሞቶ እንደተነሳ ካመናችሁ፤

እንዲሁ ደግም በኢየሱስ ያንቃለፉትን ከእርሱ ጋር ያመጣቸዋል፡፡

እነርሱ በትንሳኤ ይነሳሉ፡፡ በክርስቶስ የሞቱ አስቀድመዉ ይነሳሉ፡፡

እንዲህም ይላል፡ በእነዚህ ቃላት እርስ በእርሳችሁ ተፅናኑ፡፡ በዚህ ክፍል ላይ ከስቃይ በማምለጥ ስለሚገኝ መመቸት አይደለም የሚናገረዉ፡፡

ግድያ አይደርስባችሁም፡፡ በዉጣ ዉረድ ዉስጥ አታልፉም፡፡ ወደ መከራም አትገቡም፡፡

አትሰቃዩም፡፡ ይህ ምንባብ ስለ መከራዉ እንኳን ያነሳል ወይ?

መከራዉን በተመለከተ የተገለፀ ነገር አለ ወይ?

የለም፡፡ በመከራዉ ዉስጥ ስለማታልፉ በዚህ እርስ በእርሳችሁ ተፅናኑ፤

ግድያ ስለማይደርስባችሁ እርስ በእርሳችሁ ተፅናኑ፣ ከመከራዉ በፊት መነጠቅ ስላለ በዚህ እርስ በእርሳችሁ ተፅናኑ አላለም፡፡

እያለ ያለዉ ይሄን አይደለም!

መጋቢ ጂሜኔዝ፡ አሁን ይህን ምንባብ ስንመለከት ስለመነጠቅ በሌሎች ክፍሎች ላይ የተፃፈዉን የሚብራሩልን ጥቂት የመነጠቅ ባህርያት እንዳሉ ማየት እንችላለን፡፡

መነጠቅ በዉስጡ ምን ምን ነገሮች እንደያዘ እንድትረዱ እፈልጋለሁ፡፡

በቁጥር ላይ በዚያዉ ክፍል ብትመለከቱ እንዲህ ይላል፡

"ጌታ ራሱ በትእዛዝ በመላእክትም አለቃ ድምፅ በእግዚአብሄርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና…"፡፡

ሰለዚህ በመጀመርያ ደረጃ ስለመነጠቅ መረዳት ያለብን ነገር ጌታ ራሱ በትእዛዝ በመላእክትም አለቃ ድምፅ በእግዚአብሄርም

መለከት ከሰማይ እንደሚወርድ ነዉ፡፡ እንዲሁም ይህንን ልብ እንድትሉ እፈልጋለሁ፡ "በእግዚአብሄርም መለከት"፡፡

ይህ እንድታዩት የምፈልገዉ የመነጠቅ ሁለተኛ ባህርይ ነዉ፡፡

ጌታ ከሰማይ ይወርዳል የእግዚአብሄርም መለከት ይሆናል እናም መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረዉ" በክርስቶስ የሞቱ አስቀድመዉ ይነሳሉ፡፡

ከዚህም በኋላ እኛ ህያዋን ሆነን የምንቀረዉ…" እነዚህን ቃላት ልብ በሉ፡

"ጌታን በአየር ለመቀበል ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን…"

ስለዚህ በመነጠቁ ወቅት በኛ ተሰሎንቄ ምዕራፍ አማካኝነት የመነጠቁ ባህርያት የሚከተሉት ናቸዉ፡

. ጌታ ይወርዳል . መለከት ይነፋል . እሱን ለመቀበል በደመና መነጠቅ ፡፡

መጋቢ ጂሜኔዝ፡ እኛ ጌታን በአየር ለመቀበል ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፡፡

መጋቢ አንደርሰን፡ ወደ ማቴዎስ ተመለሱና በማቴዎስ ፡- የተቀሱትን ፍፁም አንድ አይነት ተመልከቱ፡፡

ማቴዎስ ፡ን ተመልከቱ "ከዚያች ወራትም መከራ በኋላ…" እናም አንዳንድ ጊዜ ሰዎችን

"በዚህ ምንባብ ላይ በኋላ የሚለዉ ከምን በኋላ ነዉ?" ብዬ መጠየቅ እፈልጋለሁ፡፡

ነገር ግን እንዲህ ይላል፡

[::.] ከዚያች ወራትም መከራ በኋላ ወዲዉ ፀሀይ ይጨልማል፤

ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፤

ክዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፤

[::.] የሰማይትም ኃይላት ይናወጣሉ፡፡ በዚያን ጊዜም የሰዉ ልጅ ምልክት በሰማይ ይታያል፤

በዚያን ጊዜም የምድር ወገኖች ሁሉ ዋይ ዋይ ይላሉ፤

የሰዉ ልጅንም ["የሰዉ ልጅ" ማለት ኢየሱስ በምድር ላይ በነበረ ጊዜ ራሱን ይጠራበት የነበረ ስም ነዉ]

በኃይልና በብዙ ክብር በሰማይ ደመና ሲመጣ ያዩታል፤

[::.] መላእክቱንም ከታላቅ መለከት ድምፅ ጋር ይልካቸዋል፤

ከሰማይትም ዳርቻ እስከ ዳርቻዉ ከአራቱ ነፋሳት ለእርሱ የተመረቱትን ይሰበስባሉ፡፡

መጋቢ አንደርሰን፡ አንድ አይነት ነጥቦች! ኢየሱስ በደመና እየመጣ ነዉ፡፡ መለከት ተነፋ፡፡

እርሱም የመረጣቸዉን ለመሰብሰብ መላእክትን ይልካል፡፡

መጋቢ ጂሜኔዝ፡ ይህንን ለእናንተ ያሳየሁበት ምክንያት በማቴዎስ ፤- የተጠቀሰን መነጠቅ

በኛ ተሰሎንቄ ፡- ከተጠቀሰዉ ጋር ስናወዳድረዉ

አንድ ሆኖ/ገጥሞ እንደምናገኘዉ ነዉ፡፡

መጋቢ አንደርሰን፡ ጣቾቻዉን እዛዉ ላይ አቆዩ እና ወደ ማርቆስ ሂዱ፡፡

አሁን ማርቆስ ከማቴዎስ ጋር በአብዛኛዉ አንድ አይነት ነገር ይናገራል፡፡ "ትይዩ ምንባብ" የምለዉ ማለት ነዉ፡፡

በእነዚህ ሁለት ክፍሎች ላይ አንድ አይነት ስብከት እና አንድ አይነት ትምህርት ታገኛላችሁ፡፡

አጠገብ ለአጠገብ ልታስቀምጧቸዉ ትችላላችሁ፡፡ የምናገሩት አንድ አይነት ነገር ነዉ፡፡

በዚያ ምንባብ ላይ ያህን ለእናንተ ላሳያችሁ፡፡ በቁጥር ላይ እንዲህ ይላል፡

[::.] በዚያን ወራት ግን ከዚያ መከራ በኋላ ፀሀይ ይጨልማል

ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፤

[::.] ክዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፤ የሰማያትም ኃይላት ይናወጣሉ፡፡

[::.] በዚያን ጊዜም የሰዉ ልጅ በብዙ ኃይልና ክብር በደመና ሲመጣ ያዩታል፡፡

[::.] በዚያን ጊዜም መላእክትን ይልካል ከአራቱ ነፋሳትም

ከምድር ዳርቻ እስከ ሰማይ ዳርቻ የተመረጡትን ይሰበስባቸዋል፡፡

መጋቢ አንደርሰን፡ አሁን በዚህ ቦታ እንዲሁ ፀልየን ወደ የቤታችን መሄድ እንችላለን፡፡

መጽሐፍ ቅዱሳችንን ዘግተን ይሄዉላችሁ ሰዎች፤ "ከመከራዉ በኋላ ነዉ" ማለት መቻል አለብን፤

ከዚያም እንዲሁ መጽሐፍ ቅዱሶቻችንን ዘግተን ወደ የቤታችን መሄድ፡፡

ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱሶቻችን እንዲሁ ዘግተን ወደ የቤታችን አንሄድም፡፡ ምክንያቱም ይህ ክፍል ስለመነጠቅ እንደሚናገር

እና ከመከራዉ በኋላ መሆኑን እንደሚያሳይ ላረጋግጥላችሁ እፈልጋለሁ፡፡

መጋቢ አንደርሰን፡ ብዙ ሰዎች ይህንን ክፍል ይጥሉና እንዲህ ይላሉ "ከዚህ ከማቴዎስ ላይ

አስተምሮዎቻችሁን መዉሰድ አትችሉም፤ ምክንያቱም ማቴዎስ የሚናገረዉ ለአይሁዶች ብቻ ነዉ"፡፡

ይህንን ምንባብ እንዲሁ ቆርጠዉ ያልፉና እንዲህ ይላሉ "ኦህ..ይህ እኮ ለአይሁዶች ብቻ ነዉ"፡፡

በአንድ ቦታ የሚገኙ አንዳንድ ምሁራን የማቴዎስ መጽሐፍ ለአይሁዶች፣ የማርቆስ መጽሐፍ ለሮማዉያን፣

የሉቃስ መጽሐፍ ለግሪኮች እንዲሁም የዮሀንስ መጽሐፍ ለአለም ነዉ ብለዉ ወስነዋል፡፡

ኦ ጌታ ሆይ ከአርቱ ወንጌላት ቢያንሰ በአንዱ ዉስጥ ስላካተትከን እናመሰግንሃለን!

ነገር ግን ይህንን ነገር ያመጣዉ ማነዉ? ምናልባትም የማቴዎስ ወንጌል ለአይሁዶች ይበልጥ ይስማማ ይሆናል፡፡

ምናልባትም የሉቃስ ወንጌል ለግሪኮች ይበልጥ ይስማማ ይሆናል፡፡ ምናልባትም የጳዉሎስ መልእክት ለኤፌሶን ለኤፌሶን ሰዎች ይበልጥ ይስማማ ይሆናል፡፡

አይመስላችሁም? ምናልባትም የጳዉሎስ መልእክት ለዕብራዉያን፣ ለዕብራዉያን ይበልጥ ይስማማ ይሆናል፡፡

ምናልባትም የጳዉሎስ መልእክት ለተሰሎንቄ እንዲሁ ለተሰሎንቄ ሰዎች ይበልጥ ይስማማ ይሆናል፡፡

ነገር ግን በመጽሐፍ ቅዱስ ያለዉ እያንዳንዱ ተስፋ የኔ ነዉ! እያንዳንዱ ምዕራፍ፣ እያንዳንዱ ቁጥር፣ እያንዳንዱ መስመር!

የቲቶ መጽሐፍ ለቲቶ ብቻ አልነበረም! ያ ለአጭር ጊዜ ብቻ የቆየ መጽሐፍ ነዉ!

እያንዳንዱ መጋቢ እንዲያነበዉ ጭምር ነዉ፡፡ እያንዳንዱ አማኝ እንዲያነበዉ ጭምር ነዉ፡፡ ይ አዲስ ኪዳን ነዉ!

መጋቢ አንደርሰን፡ ነገር ግን እነርሱ የሚሉት ይህንን ነዉ፡ "አይደለም መጋቢ አንደርሰን፤ አልገባህም፡፡

ይህ ሙሉ ስብከት የተሰበከዉ ስለ አይሁዶች፣ ወደ አይሁዶች፣ ለአይሁዶች ነዉ፡፡

ኢየሱስ ክርስቶስ በኦሊቬት ንግግር (ለዚህ ምንባብ የሰጡት ብልጭልጭ ስነ-መለኮታዊ ስም ነዉ) ላይ ለአይሁዶች ሰበከ፡፡

መጋቢአንደርሰን፤ እሱ እየተናገረ የነበረዉ ለአይሁዶች ነበር! አልገባህም!

በማርቆስ ፡ ከመከራዉ በኋላ ካለ በኋላ በቁጥር ላይ የኢየሱስን በደመና መምጣት ተናግሯል፤

በቁጥር ላይ ደግሞ ከምድር ዳርቻ እስከ ሰማይት ዳርቻ ድረስ የተመረጡት መሰብሰብን ይናገራል፤

እናም ይህን የሚናገረዉ ለአይሁዶች ብቻ ነዉ፡፡" እሺ የማርቆስ ወንጌል ምዕራፍ የመጨረሻዉን ቁጥር ተመልከቱ፡

ለእናንተም የምነግራችሁ ለአይሁዶች ብቻ እላለሁ፡፡

ማንም ሰባኪ ይህ የተፃፈዉ ለሁሉም አማኞች ነዉ እንዲላችሁ አትፍቀዱ፡፡ ይህ ለአይሁዶች ብቻ ነዉ፡፡

በማርቆስ ወንጌል ፡ ላይ የሚለዉ ይህንን ነዉ? አይደለም እንዲህ ይላል፡

[::.] ለእናንተም የምነግራችሁ ለሁሉ እላለሁ፤ ትጉ፡፡

መጋቢ አንደርሰን፡ ያ የምዕራፉ የመጨረሻ ቃል ነዉ፡፡

[::.] ለእናንተም የምነግራችሁ ለሁሉ እላለሁ፤ ትጉ፡፡

መጋቢ አንደርሰን፡ ነገር ግን አሁንም ሰዎች ጀርባቸዉን ይሰጡና "ይህም ዕርፍ የሚናገረዉ ለሁሉም አይደለም፡፡

የሚናገረዉ ለአይሁዶች ብቻ ነዉ" ይላሉ፡፡

ሰዎች ይህን እንደሚሉ ስላወቀ ይመስለኛል በመጨረሻ ላይ እንዲህ ያለዉ፡

ለእናንተም የምነግራችሁ ለሁሉ እላለሁ፤ ትጉ፡፡

ይህ ለሁሉም ነዉ፡፡ እሱ በግልፅ ቁልጭ ብሎ እንዲህ እያለ፡

[::.] "ለእናንተም የምነግራችሁ ለሁሉ እላለሁ፤ ትጉ፡፡ "ይህ ምዕራፍ የሚናገረዉ ለአይሁዶች ብቻ ነዉ ብሎ ማለት የሚያስቅ ነዉ፡፡

መጋቢ ጂሜኔዝ፡ ብዙ ጊዜ ሰዎች የማቴዎስ ወንጌል ፡-ን ይመለከቱ እና እንዲህ ይላሉ,

"ምንም እንኳን ስለመነጠቅ ቢመስልም፤ ምንም እንኳን ስለመነጠቅ የሚያወራ ቢመስልም፤

ስለመነጠቅ አይደለም" እናም ስለመነጠቁ አይደለም ላሉበት ይህንን ምክንያት ያስቀምጣሉ፡

ቁጥር ን ከተመለከታችሁ እንዲህ ይላል "መላእክቱን ከታላቅ መለከት ድምፅ ጋር ይልካቸዋል፤

ይልካቸዋል፤ ከሰማያትም ዳርቻ እስከ ዳርቻዉ ከአራቱ ነፋሳት ለእርሱ የተመረጡትን ይሰበስባሉ፡፡

"እናም ሰዎች ያን ቃል ይመለከቱ እና እንዲህ ይላሉ፡ "ተመልከቱ እዚያ ጋር 'የተመረጡት' የሚለዉ ቃል የሚወክለዉ ክርስቲያኖችን አይደለም፡፡

'የተመረጡት' የሚለዉ እስራኤልን ነዉ፤ ስለዚህ የማቴዎስ ወንጌል ስለመነጠቅ አይደለም፡፡

አይደለም፡፡ የዚህ ሙሉ ምዕራፍ የተቀመጠዉ ለአይሁዶች ነዉ፤ ምክንያቱም እየተናገረ ያለዉ ስለተመረጡት ነዉ" ይላሉ፡፡

እዚያ ጋር ያለዉ ጉዳይ ይህ ነዉ፡ ሁልጊዜም መጽሐፍ ቅዱስ የራሱ መዝገበ ቃላት እንዲሆን መፍቀድ አለብን፡፡

መጋቢ አንደርሰን፡ እዚህ ጋር "የተመረጡት" የሚለዉ ቃል የተጠቀሰበትን ቦታዎች ባጠቃላይ የሚሳይ ዝርዝር አለኝ፡፡

በእያንዳንዱ ላይ አንሄድበትም ምክንያቱም ጊዜ የለንም፡፡ ነገር ግን እኔ "የተመረጡት"…

በተጠቀሰባቸዉ ቦታዎች ሁሉ መሄድ እችላለሁ፤ ከዚያም በእያንዳንዱ በተጠቀሰበት ቦታ ሁሉ ስለዳኑት ሰዎች እንደሚናገር ላሳያችሁ እችላለሁ፡፡

መጋቢ ጂሜኔዝ፡ ሰዎች "የተመረጡት" የሚለዉን ቃል ከ"አይሁዶች" ወይም

"ከእስራኤል" ጋር የሚያያዙበት ምክንያት መጽሐፍ ቅዱስን ከማንበብ እና ከማጥናት ይልቅ…

ማብራርያዎችን እና በሰዎች የተፃፉ መፅሃፍትን ስለሚያነቡ እና

እነዚያ ፀሃፊዎች "የተመረጡት" ለሚለዉ ቃል የሰጡትን ትርጓሜ ስለሚነግሯቸዉ ነዉ፡፡ የስኮፊልድ ማጣቀሻ መጽሐፍ ቅዱስ…

በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ላይ "የተመረጡት" ለሚለዉ ቃል "እስራኤል" እንደሚወክል ማስታወሻ አስቀምጧል፡፡

ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ ራሱን በራሱ ያብራራል፤ እናም ባሉን አስተምህሮዎች ላይ ለሚነሱ ጥያቄዎች ሁሉ መልስ ይሰጠናል፡፡

ስለዚህም "የተመረጡት" የሚለዉን ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ብታጠኑት በቀላሉ ስለአይሁድ እንዳልሆነ ትረዳላችሁ፡፡

መጋቢ አንደርሰን፡ እንዲሁ አጭር ምልከታ ለመስጠት ያህል በተሰሎንቄ ፡ ላይ እንዲህ ይላል፡

(ኛ ተሰሎንቄ :) በእግዚአብሄር የምትወደዱ ወንድሞች ሆይ፤ እንደ ተመረጣችሁ አዉቀናልና፡፡

መጋቢ አንደርሰን፡ …ለተሰሎንቄ ሰዎች እየተናገረ ነዉ፤ እነርሱም አህዛቦች እንደሆኑ ግልፅ ነዉ፡፡ በሮሜ ላይ ይህን እናያለን፡

[::.] እግዚአብሄር የመረጣቸዉን ማን ይከሳቸዋል? የሚያጸድቅ እግዚአብሄር ነዉ፤ የሚኮንንስ ማን ነዉ?

መጋቢ አንደርሰን፡ "የተመረጡት" የሚለዉ ቃል ከተጠቀሰበት ቦታዎች ዉስጥ ሩ…

አማኞችን በአጠቃላይ እንደሚወክል፤ ቱ በተለየ ሁኔታ አህዛብ (አይሁድ ያልሆኑ) የሆኑ አማኞችን ይመለከታል፤

አንዱ አይሁድ የሆነ አማኝ እና ሁለቱ ራሱ ኢየሱስ ክርስቶስን የሚመለከቱ ሲሆን…

አንዱ ደግሞ ያዕቆብን በእግዚአብሄር እንደተመረጠ ሰዉ አድርጎ ይገልጸዋል፡፡

"የተመረጡት" የሚለዉ ቃል "እስራኤል" ማለት እንዳልሆነ በግልጽ የሚያሳይ ጥቅስ እሰጣችኋለሁ፡፡

ምክንያቱም ሰዎች "የተመረጡት? እስራኤልን ነዉ፤ አይሁዶችን ነዉ፡፡" ይላሉ፡፡

(ሮሜ :) እንግዲህ ምንድር ነዉ? እስራኤል የሚፈልጉትን አላገኙትም፤

የተመረጡት ግን አገኙት፤

መጋቢ አንደርሰን፡ ሰለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ እስራኤል እንደሌላት እና የተመረጡት ግን እንዳላቸዉ ይናገራል፡፡

ስለዚህ እስራኤል የተመረጡት ቢሆኑ ኖሮ ይህ ምንም ትርጉም ሊሰጥ አይችልም ነበር፡፡

መጋቢ ጂሜኔዝ፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ዉስጥ ይህ በጣም ግልጽ ነዉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ ራሱን እንዲያብራራ ከፈቀዳችሁ፤

"የተመረጡት" አይዶች አይደሉም፤ "የተመረጡት" አማኞች ናቸዉ፡፡

ከእስያ አናሳዎች፣ ከግሪክ፣ ከባርባርያንስ ወይም ከየትም ሊሆኑ ይችላሉ፡

ኢየሱሰን ከለበሳችሁ፤ አዲሱን ሰዉ ከለበሳችሁ ከተመረጡት ዉስጥ ትሆናላችሁ፡፡

ስለዚህ ወደ ማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ስንመለስ እንዲህ ይላል "መላእክቱንም ከታላቅ መለከት ድምፅ ጋር ይልካቸዋል፤

ከሰማይም ዳርቻ እስከ ዳርቻዉ ከአራቱ ነፋሳት ለእርሱ የተመረጡትን ይሰበስባል፡፡"

ይህ የአማኞችን መነጠቅ በተመለከተ ከምንባቡ ጋር በደንብ ይጣጣማል፡፡

መጋቢ አንደርሰን፡ ይህ አይሁድም ይሁን አህዛብ ወይም ነጭ ይሁን ጥቁር፤ ከዚያ ጋር በፍፁም አይገናኝም፡፡

መጋቢ አንደርሰን፡ ይህ አይሁድም ይሁን አህዛብ ወይም ነጭ ይሁን ጥቁር፤ ከዚያ ጋር በፍፁም አይገናኝም፡፡

አሁን ይህ በኛ ተሰሎንቄ ምዕራፍ ላይ ከተፃፈዉ ጋር አብሮ አይሄድም?

መለከት እንደሚኖር ሲናገር አማኞች ከክርስቶስ ጋር ለመሆን ይሰበሰባሉ፡፡

በዚሁ ምዕራፍ ላይ አለፍ ብላችሁ ስታነቡ እንዲህ ይላል "ስለዚህም ይህ የሚሆንበትን ቀንና ሰዓት ማንም አያዉቅም፡፡"

ይህ የሚሆነዉ በዚህ ዓመት ጥቅምት xx ዉስጥ ነዉ፡፡" ልላችሁ አልችልም፡፡

እንዲሁም አለፍ ብሎ እንዲህ ይላል፡

[::.] በዚያን ጊዜ ሁለት ሰዎች በእርሻ ይሆናሉ፤ አንዱ ይወስዳል አንዱም ይቀራል፤

[::.] ሁለት ሰዎች በወፍጮ ይፈጫሉ፤ አንዲቱ ትወሰዳለች

አንዲቱም ትቀራለች፡፡

[::.] ጌታችሁ በምን ሰዓት እንዲመጣ አታዉቁምና እንግዲህ ንቁ፡፡

መጋቢ አንደርሰን፡ ስለዚህ ይህ መቼ እንደሚሆን እንደማናዉቅ እግዚአብሄር እየነገረን ነዉ፡፡ ነቅተን ልንጠብቀዉ የሚገባ ነገር ነዉ፡፡

በምን ቀን ወይም በምን ሰዓት እንደሆነ አናዉቅም፤ ነገር ግንከመከራዉ በኋላ እንደሆነ በእርግጥ ነገሮናል፤

ምክንያቱም ከመከራዉ በኋላ ፀሀይ እና ጨረቃ እንደሚጨልሙ ተናግሯልና፡፡

ከዚያም ኢየሱስ ክርስቶስ በደመና ይመጣል፡፡ በዚያን ጊዜ ነዉ መለከቱ የሚነፋዉ፡፡

በዚያን ጊዜ ነዉ አማኞች የሚሰበሰቡት፡፡ ስለዚህ ቀኑን ወይም ሰዓቱን አናዉቅም ማለት…

ይህ በማንኛዉም ሰዓት ሊሆን ይችላል ማለት አይደለም፡፡

ብዙ ሰዎች "ቀኑን ወይም ሰዓቱን ማንም አያዉቅም" የሚለዉን ይመለከቱ እና እንዲህ ይላሉ፡ "በማንኛዉም ሰዓት ሊሆን ይችላል"፡፡

ለማንኛዉም መፅሀፉ ሲናገር "ከመከራዉ በኋላ" ብሎ ይዘጋዋል፡፡ ይህ በእርግጥም በማቴዎስ ወንጌል፣

በማርቆስ ወንጌል እና በሉቃስ ወንጌል ይገኛል፡፡ ማቴዎስ በምዕራፍ ፣ ማርቆስ በምዕራፍ ፣ ሉቃስ በምዕራፍ

እንዲሁም ዮሀንስ በዮሀንስ ራዕይ መጽሐፍ ላይ አካተዉታል፡፡ በአራቱም ሽፋን አግኝቷል፡፡

በመጀመሪያ መከራዉ ይመጣል፤ ቀጥሎም ፀሀይ እና ጨረቃ ይጨልማሉ፤

ከዚያም ኢየሱስ በመነጠቁ ጊዜ በደመና ይመጣል፡፡

መጋቢ አንደርሰን፡ሰዎች መነጠቁ ከመከራዉ በፊት ነዉ ብለዉ የሚስቡበት ምክንያት መከራዉን ከእግዚአብሄር ቁጣ ጋር ስለሚያምታቱት ነዉ፡፡

የእግዚአብሄር ቁጣ እና መከራዉ ሁለት የተለያዩ ነገሮች መሆናቸዉን የምናረጋግጥበት አንዱ መንገድ ይህ ነዉ፡

በማቴዎስ ፡ እንዲህ ይላል "ከዚያች ወራትም መከራ በኋላ ወዲዉ ፀሀይ ይጨልማል፤

ጨረቃም ብርሃን አትሰጥም…"፡፡ ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ በማቴዎስ በጣም በግልፅ እንዳስቀመጠዉ

ፀሀይ እና ጨረቃ የሚጨልሙት ከመከራዉ በኋላ ነዉ፡፡

እናም ወደ ዮሀንስ ራዕይ ምዕራፍ ላይ ሄዳችሁ ስለ ፀሀይ እና ጨረቃ መጨለም

(ተኛዉ ማህተም ሲፈታ) ስታነቡ እንዲህ ይላል፡ "…ፀሀይም እንደ ማቅ ጠጉር ጥቁር፤

ጨረቃም በሞላዉ እንደ ደም ሆነ፤

…ልክ በማቴዎስ ላይ እንደሚናገረዉ…

[::.] በለስም በብርቱ ነፋስ ተናዉጣ ቃርያዋን ፍሬ እንደምትጥል

የሰማይ ክዋክብት ወደ ምድር ወደቁ፤

[::.] ሰማይም እንደ መጽሐፍ ተጠቅልሎ አለፈ፤

ተራራዎችና ደሴቶችም ሁሉ ከስፍራቸዉ ተወሰዱ፡፡

[::.] የምድርም ነገሥታትና መኳንነት ሻለቃዎችም ባለጠጋዎችም

ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ

በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ፤

[::.] ተራራዎችንና ዓለቶችንም፡፡ በላያችን ወደቁ በዙፋንም

ከተቀመጠዉ ፊት ከበጉም ቁጣ ሰወሩን፤

[::.] ታላቁ የቁጣዉ ቀን መጥቶአልና፤ ማንስ ሊቆም ይችላል? አሉአቸዉ፡

መጋቢ አንደርሰን፡ ስለዚህ ከዚህ አንፃር የእግዝአብሄር ቁጣ መዝነብ የሚጀምረዉ መቼ ነዉ?

እነሱ "ታላቁ የቁጣ ቀን መጥቷል" የሚሉት ፀሀይ እና ደመና ሲጨልሙ ነዉ፡፡

መጥቷል የሚለዉ የአሁን ጊዜ ሰዋሰዉ ሲሆን ልክ አሁን መምጣቱን ያመለክታል፡

ስለዚህ ማቴዎስ ፀሀይ እና ጨለማ የሚጨልሙት ከመከራዉ በኋላ ነዉ ካለ

እና የእግዝአብሄር ቁጣ ፀሀይ እና ጨለማ ካልጨለሙ በቀር የማይጀምር ከሆነ እንዴት አንድ አይነት ነገር ሊሆኑ ይችላሉ?

ስለዚህ ፀሀይ እና ጨለማ ካልጨለሙ በስተቀር ቁጣዉ አይጀምርም፡፡

አብዛኛዉን ጊዜ ሰዎችን በቅድመ-መከራ መነጠቅ ዙርያ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ እንዲያሳዩዋችሁ ብትጠይቋቸዉ አንድ ጥቅስ እንኳን ሊያሳዩዋችሁ አይችሉም፡፡

እኔ "መከራ" የሚለዉን ቃል የሚጠቀምና የቅድመ-መከራ መነጠቅን የሚደግፍ ጥቅስ ሊያሳየኝ የሚችል ሰዉ ካለ እወራረዳለሁ፡፡

ይህን ሊያደርጉት አይችሉም፡፡ ሊያሳዩዋችሁ የሚችሉት "ቁጣ" የሚለዉን ቃል የሚጠቀሙትን ጥቅሶች ነዉ፡፡

እነርሱ ክርስትያኖች በእግዝአብሄር ቁጣ ስር እንዳልሆኑ የሚያሳዩ ጥቅሶችን ያነሱና ቁጣ ለእኛ እንዳልተገባ…

እና ከቁጣ እንደዳንን የሚናገሩ ጥቅሶችን ያሳዩዋችኋል፡፡

እንዲሁም እንዲህ ይላሉ "ተመልከቱ፣ እዚያ ጋር መጽሐፍ ቅዱስ ወደ መከራ እንደማንገባ ይናገራል"፡፡

ነገር ግን እዚህ ጋር አንድ ጊዜ ቆም ይበሉ፡ መከራ እና ቁጣ ሁለት የተለያዩ ነገሮች ናቸዉ!

ማንኛዉም የቅድመ-መከራ መነጠቅ አማኝ "መከራ" የሚለዉን ቃል የያዘና

የእነሱን አስተምህሮ ሊያረጋግጥ የሚችል ጥቅስ ሊያሳችሁ አይችልም፡፡

ስለዚህም የእግዚአብሄር ቁጣ እና መከራዉ ሁለት ፍፁም የተለያዩ ነገሮች ናቸዉ፡

አብዛኛዉ ክርስቲያኖች በቤተክርስቲያኖቻቸዉ እና በሚያነቧቸዉ መፅሃፍት የተማሩት ሁለቱ ነገሮች አንድ መሆናቸዉን ነዉ፡፡

እናም እነዚህን ሰዎች "ይሀዉላችሁ! አሁን ወደ መከራዉ ልንገባ ነዉ!

ከመከራዉ በኋላ ካልሆነ በቀር መነጠቅ አይመጣም" ካላችኋቸዉ እንዲህ ይሏችኋል፡

"የለም፤ እግዚአብሄር በራሱ ህዝብ ላይ ቁጣዉን አያወርድም፡፡ እኛ ቁጣ አልተወሰነብንም፡፡ እኛ ከቁጣዉ እንተርፋለን፡፡"

ነገር ግን አንዴ ቆም ይበሉ፡ የእግዚአብሄር ቁጣ ከመከራዉ ጋር አንድ ነዉ?

አይደለም፡፡ ስለዚህ ሰዎች "መከራ" የሚለዉን ቃል እንዲረዱ ማድረግ ከቻልን መነጠቁ ከመከራዉ በኋላ እንደሆነ ሊገነዘቡ ይችላሉ፡፡

ሰዎች "መከራ" የሚለዉን ቃል አይረዱትም፡፡

ምክንያቱም በአዕምሮዋቸዉ ዉስጥ ያለዉ መከራ ማለት እግዚአብሄር ቁጣዉን የሚወርድበት፣

እሳትና ዲንን የሚዘንብበት፣ ዉሃን ወደ ደም የሚቀይርበት እንደሁም ሰዎችን በጊንጦች እና

በተለያዩ ወረርሽኞች በከፍተኛ ሁኔታ የሚሰቃይበት የሰባት አመታት ጊዜ ነዉ፡፡

ይህ መከራዉ አይደለም፡፡ ይህንን አይደለም መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረን፡፡

መጋቢ አንደርሰን፡ በ"ቅድመ-መከራ መነጠቅ" የሚምኑ ወይም ከመከራዉ በፊት በሚመጣና በማንኛዉም ጊዜ ሊከሰት የሚችል መነጠቅ፡

እስቲ "ቅድመ-መከራ መነጠቅ" የሚለዉን ቃል ከፋፍለን እንየዉ፡፡

"ቅድመ" ማለት ምን ማለት ነዉ?"በፊት"፡፡

"መከራ" የሚለዉ ቃል ምንን ይገልጻል? "መከራዉን"፡፡

ከዛም "መነጠቅ" የሚለዉ ቃል አለ፡፡

"መነጠቅ" የሚለዉ ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ዉስጥ የለም፡፡ "መነጠቅ" የሚለዉ ፅንሰ-ሀሳብ ግን በመጽሐፍ ቅዱስ ዉስጥ አለ፡፡

ምክንያቱም ኢየሱስ በደመና ሲመጣ እና ሰዎች ወደ እሱ በአየር ሲሰበሰቡ ፣ ወ.ዘ.ተ. እናያለን፡፡

ስለዚህ እዚያ ጋር የመነጠቅ ፅንሰ-ሃሳብ አለ፤ ነገር ግን "መነጠቅ" የሚለዉ ቃል አልተቀመጠም፡፡

"መከራ" የሚለዉ ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ዉስጥ አለ? በአዲስ ኪዳን ላይም ጊዜ ተጠቅሷል፡፡

ስለዚህ አዲስ ኪዳን "መከራ" የሚለዉን ቃል ለ ጊዜ ከተጠቀመ እና ሁሉም በዚህ "ቅድመ-መከራ መነጠቅ" በሚባለዉ አስተምህሮ ላይ…፤

ከቱ ቁጥሮች፣ ወይም ከ ምንባቦች ወይም ምዕራፎች ዉስጥ አንዱ ከመከራዉ በፊት ስለሚመጣዉ መነጠቅ ያስተምራል?

ማናቸዉም ቁጥሮችከመከራዉ በፊት ስላለ መነጠቅ ወይም መሰል ነገሮች ምንም የሚናገሩት ነገር የለም፤

ስለዚህ የቅድመ-መከራ መነጠቅ አራማጆች በብዙ ትርጉሞች ላይ መደገፍ ይኖርባቸዋል፤

እናም ለእናንተ ማብራራት ይኖርባቸዋል እናም ይህ ሁልጊዜም ዉስብስብ ነዉ፡፡

ስለ መጽሐፍ ቅዱስ አንድ ነገር አስተዉያለሁ፡ እግዚአብሄር መጽሐፍ ቅዱስን እንድንረዳዉ ይፈልጋል፡፡

እሱ በእኛ ላይ የማሞኘት ጨዋታ ለመጫወት፣ ግራ ለማጋባት እንዲሁም ነገሮችን ከባድ ለማድረግ እየሞከረ አይደለም፡፡.

እርሱ እዉነቱን እንድናዉቅ ይፈልጋል፡፡ እርሱ ይወደናል፡፡

ብዙ ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስ አንድን ነገር ለመጀመሪያ ጊዜ ሲያመጣ ለእኛ እንደሚያብራራልን እና እንድንረዳዉ እንደሚያግዘን አስተዉያለሁ፡፡

ስለዚህም በዚህ መንገድ ሁለተኛ ጊዜ ስናየዉ፣ ስለምን እያወራ እንደሆነ እናዉቃለን፤

መጽሐፍ ቅዱስ በማቴዎስ ፡ ላይ እንዲህ ይላል፡

"ነገር ግን ለጊዜዉ ነዉ እንጂ በእርሱ ስር የለዉም፤ በቃሉ ምክንያትም መከራ ወይም ስደት በሆነ ጊዜ ወዲያዉ ይሰናከላል፡፡"

በቃሉ ምክንያትም መከራ ወይም ስደት በሆነ ጊዜ ወዲያዉ ይሰናከላል፡፡"

መጋቢ አንደርሰን፡ የ"መከራ"ን ትርጓሜ ምን ሆኖ አገኛችሁት? ስደት፤

እንዲህ ይላል ከቃሉ የተነሳ የሚመጣ "መከራ ወይም ስደት"፡፡ ስለዚህ እነዚህ ሰዎች…

በመከራ ዉስጥ የሚያልፉት በጣም ክፉ ስለሆኑ ነዉ? አይደለም፤

እናም የእግዚአብሄር ቃልን ስለመረጡ ነዉ፤ ምክንያቱም የእግዚአብሄርን ቃል

በፍፁም ደስታ ስለተቀበሉ በመከራ ወይም በስደት ዉስጥ ያልፋሉ፡፡

እኛ በምናምነዉ ነገር ላይ ስር ከሰደድን እና ከተተከልን ልክ ስደት እና መከራ በመጣ ጊዜ እናቋቋመዋለን፡፡

በመጽሐፍ ቅዱስ ዉስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ "መከራ" የሚለዉን ቃል የምናገኘዉ "ስደት" ከሚለዉ ቃል ጋር ተጣምሮ ነዉ፡፡

ያም በአዲስ ኪዳን ዉስጥ "መከራ" የሚለዉ ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠቀሰበት ስፍራ ነዉ፡፡

እናም "መከራ" የሚለዉ ቃል በተጠቀሰባቸዉ በእያንዳንዱ የአዲስ ኪዳን ቦታዎች ብትመለከቱ…

በመቶ በሚሆኑት ቦታዎች ላይ የሚናገረዉ፡ አማኞች በመከራ ሲያልፉ-የዳኑት በመከራ ዉስጥ ሲያልፉ ነዉ፡፡

ሌሎቹ ሁለት ጊዜያት ላይ ስለ ዳኑት ሰዎች የሚናገርበት ክፍል አይደለም፤

ከመጨረሻዉ ዘመን ትንቢት ጋርም ምንም የሚያያዘዉ ነገር የለም፡፡

በመከራ ዉስጥ ስለሚያልፉ ሰዎች በአጠቃላይ የሚናገር ነዉ፡፡ በታሪክ ዉስጥ …

ክርስትያኖች በመከራ ዉስጥ አልፈዋል፤ እናም የእኛ ትዉልድ የተለየ አይሆንም፡፡

ምናልባትም ይህ በህይወት ዘመናችን ሊከሰት ይችላል፤ ምናልባትም ላይከሰት ይችላል፡፡

ነገር ግን ከተከሰተ እንደ አማኞች እናልፈዋለን፡፡ ወይ ክርስቶስን ብለን እንገደላለን

ወይም እንደመታደል ሆኖ ይህንን ጊዜ አልፈን ወደ መነጠቁ እንደርሳለን፡፡

"መከራ" የሚለዉ ቃል ለአምስተኛ ጊዜ የተጠቀሰዉ በአዲስ ኪዳን በዮሀንስ ፡ ላይ ነዉ፡፡

መጋቢ አንደርሰን፡ እርሱ እየተናገረ ያለዉ ለአማኞች ነዉ፡፡ እርሱ ለደቀ መዛሙርቱ እየተናገረ ነዉ፡፡ እንዲህም አለ፡

[::.] በእኔ ሳላችሁ ሰላም እንዲሆንላችሁ ይህን ተናግሬአችኋለሁ፡፡

በአለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ፤ እኔ አለምን አሸንፌዋለሁ፡፡

መጋቢ አንደርሰን፡ መከራን ታጠፋላችሁ አለ? በመከራ ዉስጥ አታልፉም አለ?

"እኔ በጭራሽ ህዝቤን በመከራ ዉስጥ እንዲልፉ አልፈቅድም! በጣም ነዉ የምወዳቸዉ!" ብሏል?

የለም! "መከራ" የሚለዉ ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ በማቴዎስ ላይ ሲጠቀስ ምን ይላል?

ሰዎች ስር ካልሰደዱ እና ካልተተከሉ፤ ከቃሉ የተነሳ ስደት ወይም

መከራ በመጣ ጊዜ ይሰናከላሉ፡፡

ኢየሱስ በዚህ ምዕራፍ ላይ ስለ መከራ ያስጠነቀቀንን ተመልከቱ፤ በቁጥር ላይ፡

(ዮሐንስ ፤) እንዳትሰናከሉ ይህን ተናግሬአችኋለሁ፡፡

መጋቢ አንደርሰን፡ እርሱ ስለዚህ ካልነገራችሁ፤ ስለሚመጡትና በህይወታችሁ

ስለሚያልፉት ስደቶች ፣ መከራዎች እና ፈተናዎች ካላስጠነቀቃቸሁ፤

ልክ ሲከሰቱ እንግዳ እንደሚሆንባችሁ ይናገራል፤ ትሰናከላላችሁ፡፡

እንዲህ ትላላችሁ "መጋቢ አንደርሰን፡ ይህንን ስብከት የምትሰብኩት ለምንድን ነዉ?"

ይህንን ስብከት የምሰብከዉ እንዳትሰናከሉ ነዉ፡፡

"ቆይ አንድ ጊዜ፡ ይህ ስብከት ያሰናክላል!" ልትሉ ትችላላችሁ፤

አይደለም ይህ ስብከት ያስፈለገዉ እንዳትሰናከሉ ነዉ፡፡

ምክንያቱም ኢየሱስ ይህ እንደሚመጣ ካወቃችሁ አትሰናከሉም ብሏልና፡፡ በቁጥር አራት ላይ ተመልከቱ፡

(ዮሐንስ :) "ነገር ግን ጊዜዉ ሲደርስ እኔ እንደነገርኋችሁ ታስቡ ዘንድ ይህን ተናግሬአችኋለሁ፡፡

ከእናንተም ጋር ስለ ነበርሁ በመጀመርያ ይህን አልነገርኋችሁም፡፡"

መጋቢ አንደርሰን፡ ስለዚህም በዚያ ክፍል ላይ እንዲህ አለ፡ እነዚህ ነገሮች ሲከሰቱ እኔ የነገርኳችሁን ነገሮች ታስታዉሳላችሁ፡፡

እናም በዚህ ምሽት የምላችሁ ራሱ ኢየሱስ የተናገረዉን ነዉ፡፡

እነዚህ ነገሮች በህይወታችን መሆን ሲጀምሩ- ምናልባትም ይህ በህይወት ዘመናችን ዉስጥ ሊሆን ይችላል፤

ከ አመታት በኋላም ሊሆን ይችላል፤ ወይም ምናልባትም ከጥቂት አመታት በኋላ ሊሆን ይችላል፤

መጨረሻዉ መቼ እንደሚሆን አናዉቅም፡፡ ነገር ግን ሲከሰት፤ እኔ እንደነገርኳችሁ ታስታዉሳላችሁ፡፡

ከዛ በበለጠ ጠቃሚዉ ነገር፡ እነዚህን ነገሮች እኔ ስላፈጠርኳቸዉ ኢየሱስ እንደነገራችሁ ታስታዉሳላችሁ፡፡

መጋቢ ጂሜኔዝ፡ "መከራ" የሚለዉን ቃል የምታገኙበት ቀጣዩ ክፍል በሐዋርያት ስራ ፤ ላይ ነዉ፤ እናም እንዲህ ይላል፤

[::.] የደቀ መዛሙርትን ልብ እያጸኑ በሃማኖትም ጸንተዉ እንዲኖሩ እየመከሩና፤

ወደ እግዚአብሄር መንግስት በብዙ መከራ እንገባ ዘንድ ያስፈልገናል እያሉ…፤

መጋቢ ጂሜኔዝ፡ ይህ "ወደ እግዚአብሄር መንግስት በብዙ መከራ እንገባ ዘንድ ያስፈልገናል"

የሚለዉ ቃል ደስ የሚል ነዉ- ይህ ቃል ወደ እግዚአብሄር መንግስት ስንገባ በመከራ ዉስጥ አልፈን እንደሆነና፤

ከመከራዉ በፊት ወደ እግዚአብሄር መንግስት እንደማንገባ

በጣም በተለየ ሁኔታ የሚያሳይ አርፍተ-ነገር ነዉ፡፡

መጋቢ አንደርሰን፡ እርሱ እንዲህ አለ እንዴ፡ "በህይወት ያላችሁ ሰዎች፤ ከመከራዉ በፊት ስለምንሄድ በጣም ጥሩ ነዉ!"

የለም፤ እሱ ያለዉ ይህንን ነዉ፡ "ይልቅ ብትፀናላቸዉ ይሻላል፡፡ በአንዳንድ ነገሮች ላይ ብታጠነክራቸዉ ይሻላል፡፡

ብታበረታችሁ ይሻላል ምክንያቱም ወደ እግዚአብሄር መንግስት ለመግባት በብዙ መከራ ዉስጥ ማለፍ እንዳለባቸዉ ቢያዉቁ ይሻላል፡፡"

በቁጥር ላይ የተጠቀሰ ማንኛዉም የቅድመ-መከራ መነጠቅ ሃሳብ አለ?

አይመስለኝም፡፡

መጋቢ ጂሜኔዝ፡ በኛ ቆሮንቶስ ፤ ላይ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፡

(ኛ ቆሮንቶስ ፤) "ስለ እናንተ እምነቴ ታላቅ ነዉ፤ በእናንተ ምክንያት ትምክህቴ ታላቅ ነዉ፤

መፅናናት ሞልቶብኛል፤ በመከራችን ሁሉ ደስታዬ ከመጠን ይበዛል፡፡"

መጋቢ አንደርሰን፡ "በመከራ ዉስጥ ስለማላልፍ ደስታዬ ከመጠን ያልፋል፡፡

ከመከራዉ በፊት ስለምንነጠቅ በጣም ደስተኛ ነኝ!" አላለም፡፡ ያለዉ እንደዚያ አይደለም፡፡

እሱ ያለዉ "በመከራችን ሁሉ ደስታዬ ከመጠን ይበዛል፡፡" የቅድመ-መከራ መነጠቅን በመፅሐፍ ቅዱስ…

የት ላይ እናገኘዋለሁ? የለም፡፡

መጋቢ ጂሜኔዝ፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ዉስጥ "መከራ" የሚለዉን ቃል ስትመለከቱ አማኞች በመከራ ዉስጥ

እንደሚያልፉ የሚያሳዩ በርካታ ማብራራዎችን የማግኘታችሁ ነገር ለእኔ እንዲሁ አስገራሚ ነዉ፡፡

እንዲህ ይላል "…በመከራችን ሁሉ"፡፡ አማኞች የማያልፉበት ነገር አይደለም፡፡

ይህ አማኞች በህይወታቸዉ ሙሉ ሲልፉበት የኖሩት ነገር ነዉ፡፡

በትዉልዶች ሁሉ አማኞች በመከራ ዉስጥ አልፈዋል፡፡

መጋቢ አንደርሰን፡ አስተዉሉ ሰዎች፤ እግዚአብሄር ሊያደናግረን አይደለም፡፡ ግራ ሊያጋባን እየሞከረም አይደለም፡፡

ሰዎች ግራ እያጋቧችሁ ነዉ! ሰባኪዎች ግራ እያጋቧችሁ ነዉ!

የቴሌቪዥን ድራማዎች እና ፊልሞች ግራ እያጋቧችሁ ነዉ (ሌፍት ቢሃይንድ፣ ወዘተ…)

እግዚአብሄር ግራ እያጋባችሁ አይደለም፡፡

መጋቢ ጂሜኔዝ፡ መጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ-ቃላታችን እንዲሆን ከፈቀድን እናም ቃላትን እንዲፈታልን ከፈቀድን፤

"መከራ" የሚለዉ ቃል የእግዚአብሔር ቁጣ እንዳልሆነ እንመለከታለን፡፡

ይህ ቃል ስደት፣ ስቃይ ፣ዉጣ ወረድ ማለት ነዉ፡፡

መጋቢ አንደርሰን፡ ጊዜ ከተጠቀሰበት ቦታዎች ዉስጥ የሆነ ሰዉ አንዱን እንዲያሳይችሁ ታስቡ ነበር፡፡

ከመከራዉ በፊት እንደምንወሰድ የሚናገር አንድ ጥቅስ አሳዩኝ፤ ወይም…

ከመከራዉ በፊት እንደምንሰበሰብ፤ ወይም መነጠቁ ከመከራዉ በፊት እንደሚከናወን የሚናገር ጥቅስ አሳዩኝ፡፡

ነገር ግን እኔ መጽሐፍ ቅዱስ ቃል በቃል ወዲያዉኑ ከመከራዉ በኋላ የሚል ቃል ላሳያችሁ እችላለሁ፡፡

ኢየሱስ በደመና ዉስጥ ይመጣል፤ መለከቱ ይነፋል፤ እንዲሁም የተመረጡት ከእርሱ ጋር በደመና ይሰባሰባሉ፡፡

ያን ያህል ቀላል ነዉ፡፡ በቅድመ-መከራ መነጠቅ የሚያምኑት…

እንዲሁ በሰዎች ረቂቅ ትርጓሜ እና የአስተሳሰብ ዘዬ ላይ የተሞረኮዘ ነዉ፡፡

እንዲሁም "ቀኑን ወይም ሰዓቱን ስለማናዉቅ፤ ስለዚህ በማንኛዉም ሰዓት ሊሆን ይችላል ማለት ነዉ፡፡

በማንኛዉም ሰዓት መሆን ከቻለ ደግሞ ከመከራዉ በፊት መሆን አለበት፡፡"

ወይም ይህን ለማስረዳት የተወሳሰበ ካርታ ይኖራቸዉ ይሆናል፡፡ ነገር ግን እንዲሁ መጽሐፍ ቅዱስ አንስታችሁ

የተፃፈዉን ነገር እንደተቀመጠ ብትቀበሉ- አዲስ ኪዳንን ከማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ጀምራችሁ አንብቡ-

ማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ላይ ስትደርሱ፡ ይኸዉላችሁ እንደ ቀን ብሩህ ሆኖ ታገኙታላችሁ፡ ከመከራዉ በኋላ ኢየሱስ በደመና ይመጣል፡፡

መጋቢ አንደርሰን፡ ዶክተር ኬንት ሆቪንድ በጣም የታወቀ ወንጌላዊ ሲሆን የቅድመ-መከራ መነጠቅን…

ለ ዓመታት ሰብኳል፡፡ አሁን ግን በእስር ቤት ዉስጥ ይገኛል፡፡ በእስር ቤት ዉስጥ እንደመሆኑ መጠን…

መጽሐፍ ቅዱሱን እያነበበ ነበር፡፡ እናም የቅድመ-መከራ መነጠቅ በመጽሐፍ ቅዱስ እንደሌለ ተረዳ፡፡

ስለሆነም ለመቀየር ምን እንዳነሳሳዉ ለማወቅ ልደዉልለት እፈልጋለሁ፡፡

ከመከራዉ በኋላ መሆኑን እንዲረዳ ምን አነሳሳዉ?

ዶ/ር ኬንት ሆቪንድ፡ ስሜ ኬንት ሆቪንድ ይባላል፡፡ ለ ዓመታት በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የሳይንስ መምህር ነበርኩ፡፡

ከዚያም ወንጌላዊ ሆኜ ለ ዓመታት ስለ ስነ-ፍጥረት እና ዝግመተ-ለዉጥ ሳስተምር ቆየሁ፡፡

እናም ስለ መጨረሻዉ ዘመን ያለኝ እይታ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር እንዴት እንደሚገናኝ ማወቅ በጣም አሳሰበኝ፡፡

እናም ከሶስት ዓመታት በፊት እድሜ ልኬን በሙሉ ስማረዉ የነበረዉ ነገር እዉነት እንዳልነበረ አመንኩ፡፡

ለዉጥ ማድረግ ነበረብኝ፡፡ አክራሪ ወንደሞቼን ወደሚያስጨንቃቸዉ ወደ ድህረ-መከራ፤ ቅድመ-ቁጣ

አቋም መምጣት ነበረብኝ፡፡ በመጨረሻዉ ቀናት ያሉ ፌዘኞች

ለዉጥ ማድረግ ነበረብኝ፡፡ አክራሪ ወንደሞቼን ወደሚያስጨንቃቸዉ ወደ ድህረ-መከራ፤ ቅድመ-ቁጣ

መቼም እኔ በአለም ዙርያ ስለ ፍጥረት እና ስለ ጎርፉ ለ ዓመታት ያህል ሳስተምር ቆይቻለሁ፡፡

ነገር ግን ስለሚመጣዉ ፍርድ ከማስተማር ተቆጥቤ ነበር፡፡ ምክንያቱም እኔ እራሴ ስላለገባኝ ነዉ፡፡

ነገር ግን ስለሚመጣዉ ፍርድ ከማስተማር ተቆጥቤ ነበር፡፡ ምክንያቱም እኔ እራሴ ስላለገባኝ ነዉ፡፡

መልስ ይሰጣል፡ የአንተ መምጫ ምልክቱ ምንድን ነዉ? እናም የሚሆነዉ መቼ ነዉ? በማርቆስ ወንጌል ምዕራፍ እና

በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ ላይ አንድ አይነት ታሪክ እናገኛለን፡፡ ስለዚህ ከመጽሐፍ ቅዱስ ሶሰቱንም ገልብጬ…

ጎን ለጎን በትይዩ አስቀመጥኳቸዉ፡፡ እናም ሁሉንም ዝርዝሮች ካነሳችሁ በኋላ…

ቅድመ-መከራ መነጠቅ እዉነት እንዳልሆነ

ይበልጥ ግልፅ እየሆነ ይመጣል፡፡

መጋቢ አንደርሰን፡ ለምን ብዙ ሰዎች በቅድመ-መከራ መነጠቅ የሚያምኑ ይመስልሃል?

ይህ አስተምህሮ ለምን በጣም ታዋቂ ሆነ?

ዶ/ር ኬንት ሆቪንድ፡ ምክንያቱም ይህን አሳፋሪ ጥያቄ ስለሚመልስ ነዉ፡፡ ክርስትያኖች ስለ ዳይኖሰሮች የሚጠየቁ ጥያቄዎችን…

መመለስ አልቻሉም፡፡ የት ዉስጥ ነዉ የሚገቡት? ስለዚህ "የልዩነት ፅንሰ-ሃሳብ"ን ፈጠሩ እናም ተዋጉለት፡፡

የቅድመ-መከራ መነጠቅ አስተሳሰብ ለሚያሳክክ ጆሮ ላላቸዉ ሰዎች መደብ ዉስጥ ይገባል ብዬ አስባለሁ፡፡

መስማት የሚፈልጉት ይህንን ነዉ፡፡

መጋቢ አንደርሰን፡ ትክክል

ዶ/ር ኬንት ሆቪንድ፡ "ሄሎ፣ በመከራ ዉስጥ ማለፍ አይኖርብኝም" የሚል ነገር ነዉ መስማት የሚፈልጉት፡፡

እንግዲህ ኢየሱስ ከአለም መጀመርያ ጀምሮ ያልታየ የመከራ ጊዜ እንደሚመጣ ተናግሯል፡፡

እኔ የምልህ፤ የስፓኒሽ ምርመራ መጥፎ ነበር ብለህ ታስባለህ? ወይም ከናዚ ጋር የሚያይዘዉ የአይሁዶች እልቂት መጥፎ ነበር?

ወይም የክርስቲያኖች በሮማዉያን መሰቃየት?

ከእነዚህ ሁሉ ድምር በላይ ይሆናል!

መጋቢ አንደርሰን፡ ዋዉ፤ አስገራሚ ነዉ፡፡

ዶ/ር ኬንት ሆቪንድ፡ ስለዚህ አለም ቃየን አቤልን በመግደል ጀመረ- መጥፎ ሰዎች ጥሩ ሰዎችን እየገደሉ፡፡

መጋቢ አንደርሰን፡ ትክክል፡፡

ዶ/ር ኬንት ሆቪንድ፡ በታሪክ ዉስጥ ሁሉ የሆነዉ እንደዚህ ነዉ፡፡ እናም ኢየሱስ እንደተናገረን…

ሲገልድሏችሁ ወይም ሲያሳድዷችሁ ደስ ይበላችሁ፤

ምክንያቱም በሰማይ ዋጋችሁ ታላቅ ነዉና፡፡

መጋቢ አንደርሰን፡ "መከራ" የሚለዉን ቃል ትክክለኛ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ፍቺ ከወሰድን (የተሳሳተዉን ትርጉም አይደለም)

በእርግጥም የ"መከራ"ን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትርጓሜዉን ከወሰድን፤

አሁን ራሱ በመከራ ዉስጥ እያለፍኩ ነዉ አትልም ነበር?

ዶ/ር ኬንት ሆቪንድ፡ ኦ…አዎ፡፡ "መከራ" አለም የምታደርግብን ነገር ነዉ፤ እናም

በሺህ ለሚቆጠሩ አመታት ሆኗል፡፡ ኢየሱስ እንዲህ ብሏል፡ "በአለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፡

ነገር ግን አይዞአችሁ እኔ አለምን አሸንፌዋለሁ፡፡" ክርስትያኖች መከራ እንደሚመጣ መጠበቅ ይኖርባቸዋል፤

እናም በትዕግስት ካለፍነዉ ታላላቅ ሽልማቶችን እናገኛለን፡፡

መጋቢ አንደርሰን፡ አሁን ይህ ትምህርት ስለ "ሀይማኖታዊ ፅንፈኝነት" ስለሆነ

ይህ ምናልባትም በአንዳንድ ሰዎች አዕምሮ ዉስጥ ወደ እዛኛዉ ምድብ ዉስጥ ሊገባ ይችላል፤

በቀጥታ ለዚህ አለም መጨረሻ እንደሚኖረዉና በቀጥታ የኢየሱስ ክርስቶስ አካላዊ ዳግም-ምፅዓት እንደሚሆን ያስባሉ፡፡

ለዛም ነዉ እኔ በጥቅሉ ላስረዳችሁ የፈለግሁት- ከመጽሐፍ ቅዱስ በመነሳት የጊዜ ሂደትና እና

እንዴት እነዚህ ሁሉ ነገሮች ወደ ፍጻም እንደሚመጡ አጠር ያለ መግለጫ እሰጣችኋለሁ፡፡

መጋቢ አንደርሰን፡ የዮሀንስ ራዕይን መጽሐፍ የምንረዳበት ቁልፉ ያለዉ እንዴት እንደሚተነተን በመረዳት ዉስጥ እንደሆነ አስባለሁ፡፡

እግዚአብሄር የዮሀንስ ራዕይን መጽሐፍ የሰጠን ያ መገለጥ እንዲሆነን ነዉ፤

ነገሮችን ለመደበቅ ሳይሆን ለመግለጥ ነዉ፡፡ ይህ መጽሐፍ በማስመሰል የሚደብቅ መጽሐፍ አይደለም፡፡

ነገር ግን የመገለጥ መጽሐፍ ነዉ፤ እናም እግዚአብሄር በቀላሉ እንድንረዳዉ ይፈልጋል፡፡

ለእዚያም ነዉ በቀላሉ በምንረዳበት መልክ የሰጠን፡፡ በምዕራፍ አንድ ላይ ማንበብ ስትጀምሩ፡

እናንተ በክርስቶስ ጊዜ ወይም እዛ አካበቢ ላይ ናችሁ፡፡

ምክንያቱም ዮሀንስ ወንጌልን በመስበኩ በፍጥሞ ደሴት ታስሮ ነበር፤

እናም ይህ ከክርስቶስ መምጣት በኋላ ከአንድ ክፍለዘመን በፊት የሆነ ነዉ፡፡ ከዚያም ጌታ ኢየሱስ ክርሰቶስ ተገለጠለት ራዕይንም ተቀበለ፡፡

ከዚያም በምዕራፍ - ላይ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰባት የእስያ ቤተክርስቲያኖች መልዕክትን ሰጠ፡፡

እናም አንደሚታወቀዉ እነዚህ ቤተክርስቲያኖች ከክርስቶስ ልደት በኋላ በመጀመሪያዉ ክፍለ-ዘመን ዉስጥ የነበሩ ናቸዉ፡፡

ከዚያም ከምዕራፍ - በሰማይ የሚሆኑ ነገሮችን የሚናገረዉን ራዕይ እናያለን፡፡

ቀጥሎም ምዕራፍ ላይ በመከራዉ ጊዜ የሚሆኑ ክስተቶችን እንመለከታን፡፡

ምዕራፍ አያሌ ተግባራት በሰማይ የሚሆኑበት ስፍራ ነዉ- በይበልጥም መነጠቁ-

ሁሉም ሀገሮችን እና ተመሳሳይ ህዝቦች በዚህ ቦታ ተወክለዋል፡፡ ከዚያም ከምዕራፍ - እግዚአብሄር

ቁጣዉን በምድር ላይ ሲያወርድ እንመለከታለን፡፡ ቀጥሎም ምዕራፍ ሰባተኛዉ መለከት ከመነፋቱ በፊት ስለሚሆኑ

ጥቂት ነገሮች የሚናገርና የቀደሙትን ይበልጥ የሚብራራ ምዕራፍ ነዉ፡፡ በምዕራፍ ላይ ኛዉ መለከት ይነፋል፡፡

ሲጠቃለል፡ የዮሀንስ ራዕይ መጽሐፍን ስትመለከቱ የመጀመሪያዎቹ ምዕራፎች በሚገባ ትርጉም በሚሰጥ

የጊዜ ቅደም ተከተል የተቀመጡ ናቸዉ፡፡ ከክርስቶስ ዘመን አካባቢ (ከክርስቶስ ጋር አንድ ክፍለ-ዘመን)

ጀምራችሁ እስከ መጪዉ ዘመን ክስተቶች፡ መከራዉ፣ መነጠቁ፣

ከዚያም የእግዚአብሄር ቁጣ መዉረድን ትመለከታላችሁ፡፡

ከዚያም በምዕራፍ ላይ ሰባተኛዉ መለከት ሲነፋ መጨረሻዉ ይሆናል፡፡

እንዲህም ይላል፡ "የአለም መንግስታት በሙሉ የጌታ መንግስታት ይሆናሉ፤ የክርስቶስም ይሆናሉ፡፡

እሱም ከዘላለም እስከ ዘላለም ይነግሳል፡፡" ሆኖም የሚገርመዉ ነገር፡ በምዕራፍ መጨረሻ ላይ ስትደርሱ…

በመደምደሚያዉ ላይ መጨረሻዉ ይመጣል፡፡ከዚያም ወደ ምዕራፍ ትገባላችሁ፡፡

አሁን በዩሐንስ ራዕይ መጽሐፍ ላይ ወሳኝ የማርሽ ለዉጥ ይሆናል፡፡

ምክንያቱም እስቲ ቅድም ያየነዉን የምዕራፍ ትን ቁጥር ተመልከቱ፡፡ እንዲህ ይላል፡

(የዮሐንስ ራዕይ :-) "ታላቅ ምልክትም በሰማይ ታየ ፀሐይን ተጎናጽፋ

ጨረቃ ከእግሮችዋ በታች ያላት በራስዋም ላይ የአሥራ ሁለት ክዋክብት አክሊል የሆነላት አንዲት ሴት ነበረች፡፡

እርስዋም ፀንሳ ነበር፤ ምጥም ተይዛ ልትወልድ ተጨንቃ ጮኸች፡፡"

(የዮሐንስ ራዕይ :) "ሌላም ምልክት በሰማይ ታየ፤ እነሆ ታላቅ ቀይ ዘንዶ፤

ሰባት ራሶችና አሥር ቀንዶችም ነበሩት በራሶቹም ላይ ሰባት ዘዉዶች ነበሩ፤"

(የዮሐንስ ራዕይ :) "ጅራቱም የሰማይን ክዋክብት ሲሶ እየሳበ ወደ ምድር ጣላቸዉ፡፡

ዘንዶዉም ሴቲቱ በወለደች ጊዜ ሕፃንዋን እንዲበላ

ልትወልድ ባላት ሴት ፊት ቆመ፡፡"

መጋቢ አንደርሰን፡ አሁን በቁጥር ላይ ትኩረት አድርጉ፡

(የዮሐንስ ራዕይ :) "አሕዛብንም ሁሉ በብረት በትር ይገዛቸዉ ዘንድ ያለዉን ልጅ ወንድ ልጅ ወለደች፤

ልጅዋም ወደ እግዚአብሄርና ወደ ዙፋኑ ተነጠቀ፡፡

መጋቢ አንደርሰን፡ አሁን በግልፅ እንደሚታወቀዉ ይህ ልጅ እየሱስ ክርስቶስ ነዉ፤ ምክንያቱም በብሉይ ኪዳን እና

በአዲስ ኪዳን መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ ክርስቶስ ይህንን ምድር በብረት በትር እንደሚገዛ ይናገራል፡፡

እናም ይህ ወደፊት የሚመጣዉን የሺህ አመት ዘመነ-መንግስቱን የሚያመለክት ነዉ፡

ስለዚህ በእርግጥ የዮሐንስ ራዕይን መጽሐፍ እንድትረዱ ማድረግ የምችልበት ምርጡ መንገድ፡

ልክ በምዕራፍ ላይ ለሁለት እንድትከፍሉት መንገር ነዉ፡፡ - አንደኛዉ ግማሽ ከሆነ እና - ደግሞ ሁለተኛዉ ግማሽ ይሆናል፡፡

ከዚያም እነዚህን ሁለት ግማሾች ጎን ለጎን ብታስቀምጧቸዉ፤ አንድ አይነት ክስተቶችን ከሁለት የተለያዩ እይታዎች ታያላችሁ፡

መጋቢ አንደርሰን፡ ለምን እግዚአብሄር ይህንን ነገር ያደርጋል? ለምን እግዚአብሄር አንድን ታሪክ በዮሐንስ ራዕይ መጽሐፍ ላይ

ሁለት ጊዜ ይናገራል? እሺ፤ የወንጌልን ታሪክ ለምን አራት ጊዜ በማቴዎስ፣ ማርቆስ፣ ሉቃስ እና ዮሐንስ ወንጌል ነገረን?

ለምን ኛ እና ኛ ሳሙኤልን እንዲሁም ኛ እና ኛ ነገሥትን ሰጠን?

ነገር ግን እንደገናም ኛ እና ኛ ዜናን ሰጠን፤ ይህም ሌላ እይታ፣ ሌላ አተያይ እንዲኖረን ነዉ፡፡

ስለሆነም የነገሥት መጽሐፍትን ከዜና መጽሐፍት ጋር፤ የማቴዎስ መጽሐፍን ከማርቆስ ጋር፤

የማርቆስን መጽሐፍን ከሉቃስ ጋር እንዲሁም የሉቃስ መጽሐፍን ከዮሐንስ ጋር በማወዳደር በጣም ብዙ መማር እንችላለን፡፡

ይህም የተለያዩ እይታዎችን ይሰጡናል፡፡ ስለዚህ የዮሐንስ ራዕይንም መጽሐፍ የምንረዳዉ በዚሁ መልኩ ነዉ፡፡

ያንን የጊዜ ቅደም-ተከተሉን ከተረዳችሁ የዮሐንስ ራዕይ መጽሐፍን እንድትረዱ ይረዷችኋል፡፡

አሁን አንዳንድ ሰዎች የዮሐንስ ራዕይ ባጠቃላይ የጊዜ ቅደም-ተከተልን የጠበቀ አይደለም ብለዉ ያስባሉ፤

ነገር ግን "ከዚህ በኋላ" ወይም "ከእነዚህ ነገሮች በኋላ" የሚለዉ ቃል በየዮሐንስ ራዕይ መጽሐፍ ዉስጥ ጊዜ እናገኘዋለን፡፡

"ከዚህ በኋላ" እና "ከእነዚህ ነገሮች በኋላ" የሚሉትን ቃላት ደግመን ደጋግመን ካየን

እግዚአብሄር የክስተቶቸን ቅደም-ተከተል እየሰጠን ነዉ፡፡

መጋቢ ጂሜኔዝ፡ መጽሐፍ ቅዱስ "ከዚህ በኋላ" የሚለዉን ለመቃወም መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ ወይም

ለመተርጎም መሞከር የቂል መንገድ ነዉ፡፡ "በጊዜ ቅደም-ተከተል አይደለም የተቀመጠዉ፡፡ ይህ ትርጉም አይሰጥም፡፡"…

…ይላሉ ሰዎች፡፡ ሆኖም በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ሁሉ፤ እንደዚያ ነዉ ቃሉን የምታነቡት፡፡

አዝናኝ ምሳሌ፡ በዮሐንስ ፡ ላይ እንዲህ ይላል፡

[::.] "እዉነትን የሚያደርግ ግን ሥራዉ በእግዚአብሄር ተደርጎ እንደ ሆነ…

…ይገለጥ ዘንድ ወደ ብርሃን ይመጣል፡፡"

መጋቢ ጄሜኔዝ፡ ከዚያም ቁጥር እንዲህ ይላል "ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ ይሁዳ አገር መጣ፤"

እናም በቁጥር ላይ "ከእነዚህ ነገሮች በኋላ" እያለ "የለም፤ ቁጥር በእርግጥ ከቁጥር በፊት የተከናወነ ነዉ"

ማለት ለእኔ ቂልነት ይሆንብኛል፡፡

ያንን እንመለከት እና አዎ በእርግጥም የተፃፈዉ እንደዛ ነዉ፤ ትርጉሙም ያዉ ነዉ እንላለን፡፡

ከዚያም ወደ የዮሐንስ ራዕይ መጽሐፍ ስንመጣ እንዳልኳችሁ ጊዜ "ከእነዚህ ነገሮች በኋላ" ወይም "ከዚህ በኋላ"

የሚሉትን ቃላት እናነባለን፡፡ ነገር ግን ሰዎች አሁንም "በጊዜ ቅደም-ተከተል አይደለም የተቀመጠዉ፡፡

ይህ ትርጉም አይሰጥም፡፡" ይላሉ፡፡ ይህ መጽሐፍ ቅዱስን በደደበ ስልት የማንበቢያ መንገድ ነዉ፡፡

መጋቢ አንደርሰን፡ ስለዚህ በጊዜ ቅደመ-ተከተል መቀመጡን ከተረዳችሁ በምዕራፍ ላይ ግን እንደገና እንደሚጀምር እወቁ፡፡

ያም እንድትረዱት ይረዳችኋል፡፡ ጥቂት ምዕራፎችን ብቻ አልፌ

በመጨረሻዉ ዘመን ሰለሚሆኑ ክስተቶች በቅደም ተከተል ላሳያችሁ እፈልጋለሁ፡፡

ይህ ከ ዓመታት በኋላም ሊከሰት ይችላል፡፡ ሁላችንም ከተወሰድን በኋላም ሊሆን ይችላል፤

ነገር ግን በጣም በቅርብ ጊዜ ዉስጥ እንደሚሆን አስባለሁ፡፡

በእርግጥም በተለመደዉ የእድሜ ልክ ከኖርኩና በእኔ እድሜ እነዚህ ነገሮች ካልተከሰቱ በጣም ይገርመኛል፡፡

እኔ ዓመቴ ነዉ፡፡ እናም አሁን ነገሮች በሚሆኑበት ፍጥነት ከሄድን በሚቀጥሉት ዓመታት ዉስጥ ይህ ካልተከሰተ በጣም እደነቃለሁ፡፡

ዛሬ ማታ ወደ መልዕክቱ ስመጣ በጥቅቱም ቢሆን ለምን እንደዛ እንዳልኩ ትረዳላችሁ ብዬ አስባለሁ፡፡

መጀመሪያ ምን እንደሚጀምር ተመልከቱ፡ መከራዉ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ዲያብሎስ ወይም ሰይጣን ከሰማይ እንደሚጣል ይናገራል፡፡

አሁን እንዲህ ልትሉ ትችላላችሁ "አንድ ጊዜ መጋቢ አንደርሰን፤ ይህ ቀድሞ የሆነ ነገር አይደለም እንዴ?" ነገር ግን መልሱ አይደለም ነዉ፡፡

ሰዎች ዲያብሎስ አሁን በሲኦል እንዳለ አድርገዉ ያስባሉ፡፡ ነገር ግን እዉነታዉ ይህ ነዉ፡

ዲያብሎስ ሲኦል ዉስጥ ገብቶም አያዉቅም፡፡

ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ እንዳስቀመጠዉ ዲያብሎስ የሚዉጠዉን ፈልጎ እንደሚያገሳ አንበሳ በምድር ላይ እየዞረ ነዉ፡፡

በመጽሐፍ ቅዱስ ዲያብሎስ እና ሁሉም አጋንንቱ በምድር ላይ ይገኛሉ፡፡

ከምድር ወደ ሰማይ ይመላለሳል፤ እናም ከእግዚአብሄር ጋር ይነጋገራል፡፡

የእዮብን መጽሐፍ ስታነቡ ዲያብሎስ መጥቶ በእግዚአብሄር ፊት ቆመ፤

እንዲሁም ከእግዚአብሄር ጋር ስለ አገልጋዩ እዮብ ተነጋገረ፡፡ ስለዚህ በአሁኑ ሰዓት ዲያብሎስ ይመጣል ይሄዳል፡፡

እናም መጽሐፍ ቅዱስ ዲያብሎስ ከሰማይ እንዴት እንደሚጣል ይናገራል፡

(የዮሐንስ ራዕይ :) "በሰማይም ሰልፍ ሆነ፤ ሚካኤልና መላእክቱ ዘንዶዉን ተዋጉ፡፡

ዘንዶዉም ከመላእክቱ ጋር ተዋጋ፤ አልቻላቸዉምም፤"

(የዮሐንስ ራዕይ :) "ከዚያም ወዲያ በሰማይ ስፍራ አልተገኘላቸዉም፡፡"

(የዮሐንስ ራዕይ :) ዓለሙንም ሁሉ የሚያስተዉ ፤

ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለዉ ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመዉ እባብ ተጣለ፤

ወደ ምድር ተጣለ መላእክቱም ከእርሱ ጋር ተጣሉ፡፡

[::.] ታላቅም ድምፅ በሰማይ ሰማሁ እንዲህ ሲል፡

አሁን የአምላካችን ማዳንና ኃይል መንግሥትም የክርስቶስም ሥልጣን ሆነ፤

ቀንና ሌሊትም በአምላካቸን ፊት የሚከሳቸዉ ወንድሞቻችን ከሳሽ ተጥሎአልና፡፡

እነርሱም ከበጉ ደም የተነሣ ከምስክራቸዉም ቃል የተነሣ ድል ነሡት፤

ነፍሳቸዉንም እስከ ሞት ድረስ አልወደዱም፡፡

ስለዚህ ፤ ሰማይና በዉስጡ የምታድሩ ሆይ፤ ደስ ይበላችሁ፤

ለምድርና ለባህር ወዮላችሁ፤

ዲያብሎስ ጥቂት ዘመን እንዳለዉ አዉቆ በታላቅ ቁጣ ወደ እናንተ ወርዶአልና፡፡

መጋቢ አንደርሰን፡ ሰለዚህ እዚህ ጋር የምናየዉ ምንድን ነዉ? በሰማይ ጦርነት አለ፤

እናም ዲያብሎስ በዉጊያዉ እንደተሸነፈ መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምረናል፡፡

በሰማይ ያለዉን ጦርነት ተሸንፏል፡፡ እናም ጦርነቱን ከመሸነፉ የተነሳ እሱ እና መላእክቱ (የመላእክትን አንድ ሶስተኛ) ያህል ይዞ ወደ ምድር ተጥሏል፡፡

በዋናነት ከሰማይ የተጣለዉ ሰይጣን ነዉ፤ እናም አጭር ጊዜ ብቻ እንዳለዉ ያዉቃል፤

ስለሆነም አማኞችን ሊያሰቃይ ይወጣል፤ ቅዱሳንን ያሰቃያቸዋል ሊያጠፋቸዉም ይሞክራል፡፡

ምዕራፍ ን ተመልከቱ፡፡ ይህ ጦርነቱ የሚጀምርበት ቦታ ነዉ፡

በየዮሐንስ ራዕይ ፡ ላይ ጦርነት ለማድረግ ይወጣል፡፡ እንዴት ነዉ የሚደርገዉ? ዲያብሎስ እንዴት ነዉ

ከቅዱሳን ጋር ጦርነት የሚያደርገዉ?

መጋቢ አንደርሰን፡ በመቀጠል ሲሆን የምታዩት ትንቢታዊ ነገር ታላቁ መከራ ነዉ፡

የታላቁ መከራ ጊዜ በዚህች ምድር ላይ በርካታ አሰቃቂ ነገሮች የሚካሄዱበት ጊዜ ነዉ፡፡

ረሃብ በብዛት ይኖራል፡፡ ወረርሽኞች ይኖራሉ፡፡

ጦርነት ይኖራል - እጅግ በጣም በርካታ ጦርነቶች፡፡

ብዙ ህዝቦች በጠና ይራባሉ በበሽታም ይሞታሉ፡፡ በርካታ አሰቃቂ ነገሮች ይከሰታሉ፡፡

በታላቁ መከራ ወቅት ከሚካሄዱት በርካታ ጦርነቶች እና መቅሰፍቶች ዉስጥ

ነገር ግን የተፈጥሮ አደጋዎች፣ ጦርነት፣ ረሃብ፣ በሰዉ ልጆች የሚከሰቱትን ያካትታል) አንድ ሰዉ ይነሳል፤

(መለኮታዊ መቅሰፍቶች አይደሉም፤ እግዚአብሄር እሳትና ዲን እያዘነበ አይደለም፤

የመላዉ አለም ፈላጭ ቆራጭ ገዢ ይሆናል፤ "የክርስቶስ ተቃዋሚ" በመባልም ይታወቃል፡፡ ይህ ተረት አይደለም፡፡ ይህ በእርግጥ ይፈፀማል፤

ስለሆነም ይህ መፈፀም እየጀመረ መሆኑን አሁን ላይ እንኳን ሆነን ማየት እንችላለን፡

መጽሐፍ ቅዱስ አንድ ወቅት ላይ የአንድ አለም መንግስት እንደሚኖር ይነግረናል፡፡ በአሁኑ ወቅት ብዙ የተለያዩ መንግስታት አሉ፤

ዩናይትድ ስቴትስ አለች፤ ሩስያ አለች፤ ቻይና አለች- እነዚህ ሁሉ የተለያዩ ሊአላዊ ሀገሮች ናቸዉ፤

("ሉአላዊ" የሚለዉን ቃል ከዚህ በፊት ሰምታችኋል ብዬ እገምታለሁ)- ሁሉም የተለያዩ መንግስታት ናቸዉ፡፡

ሆኖም መጽሐፍ ቅዱስ አንድ ቀን እነዚህ ሁሉ መንግስታት እንደሚዋሃዱ

እና አንድ መንግስት እንደሚመሰርቱ ይናገራል፡፡ አንድ መንግስት ከመሰረቱ በኋላ ደግሞ

ሥልጣናቸዉን በሙሉ የአገር መሪ ለሚሆነዉ አንድ ግለሰብ ያስረክባሉ፡፡

እናም ያ ግለሰብ "የክርስቶስ ተቃዋሚ" በመባል ይታወቃል፡፡ ከዚህ ቀደም ስለ ክርስቶስ ተቃዋሚ ሰምቶ የሚዉቅ ማነዉ?

ሁሉም ሰዉ ይህን ቃል ከዚህ ቀደም ሰምቶ ያዉቃል፡፡ "የክርስቶስ ተቃዋሚ" መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል ነዉ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ብዙ ጊዜ

"አዉሬዉ" ወይም "የባህሩ አዉሬ" ወይም "ሰባት ራስና አስር ቀንዶች ያሉት አዉሬ"

ወይም የ "የአመፅ ሰዉ" ወይም "የጥፋት ልጅ" ይለዋል፡፡ ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ "የክርስቶስ ተቃዋሚ" የሚለዉን ቃልም ይጠቀማል፡፡

እኔም "የክርስቶስ ተቃዋሚ" የሚለዉን ቃል መጠቀም እወዳለሁ፡፡ ሰዎች የሚረዱት ቃል ነዉ፤

መጽሐፍ ቅዱሳዊም ቃል ነዉ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ "የክርስቶስ ተቃዋሚ" የሚለዉን ቃል በምን ስፍራ ላይ እንደሚጠቅስ

ላሳያችሁ እወዳለሁ፡፡ ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ አንድ ቀን የክርስቶስ ተቃዋሚ የተባለ ሰዉ እንደሚመጣ ይነግረናል፡፡

ኢየሱስ ክርስቶስ ከመምጣቱ በፊት አታላዩ ነበር፤ ሀሰተኛዉ ክርስቶስ፡፡

የምለዉ ነገር ገብቷችኋል? የክርስቶስ ተቃዋሚ ዳግም የሚመጣዉ ክርስቶስ እኔ ነኝ የሚለዉ ግለሰብ ነዉ፤

ነገር ግን እሱ አስመሳይ ነዉ፡፡ ሆኖም ክርስትያኖች ኢየሱስ በማንኛዉም ሰዓት ሊመጣ ይችላል

ተብለዉ እየተማሩ ስለሆነ፤ ይህ ምርጥ መገጣጠም ነዉ ምክንያቱም ማን ነዉ በእርግጥ የሚገለጠዉ-

የክርስቶስ ተቃዋሚው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ለምን "የክርስቶስ ተቃዋሚ" አለዉ? ምክንያቱም "የክርስቶስ ተቃዋሚ" (ነጠላ) የሚባል ሰዉ ስለሚመጣ ነዉ፡፡

ይህም ሰዉ ኢየሱስ ክርስቶስ ነኝ ይላል፡፡ በታላቁ መከራ ወቅት የክርስቶስ ተቃዋሚ ሲገለጥ እና

"እኔ ኢየሱስ ክርስቶስ ነኝ" ሲል እንደ አዳኛቸዉ አድርገዉ ይቀበሉታል፡፡ ብዙ ሰዎች እንዲህ ብለዉ ያስተምራሉ፡

"ኦ…ኢየሱስ ክርስቶስ በደመናዎች ዉስጥ በሚመጣበት ጊዜ አይሁዶች አዳኛቸዉ እንደነበር ይረዳሉ፤

እናም ይቀበሉታል" አይደለም፤ እነርሱ የሚቀበሉት የክርስቶስ ተቃዋሚ ነዉ!

መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረዉ ይህንን ነዉ፡፡ ኢየሱስ እንዲህ አለ፡

[::.] የዮሐንስ ወንጌል ፡ "እኔ በአባቴ ስም መጥቻለሁ አልተቀበላችሁኝምም፤

ሌላዉ በራሱ ስም ቢመጣ እርሱን ትቀበሉታላችሁ፡፡"

መጋቢ አንደርሰን፡ በቅድመ-መከራ መነጠቅ ላይ ያለዉ የሰይጣን እቅድ ሁሉም ሰዉ ወደ እዚኛዉ አስተሳሰብ፡

"ኢየሱስ ክርስቶስ በማንኛዉም ቅፅበት ሊመጣ ይችላል" እንዲመጣ ነዉ፡"ኢየሱስ ክርስቶስ በማንኛዉም ሰዓት

ይመጣል ብለን እየጠበቅን ነዉ! ዛሬ ሊመጣ ይችላል! ዛሬ እየመጣ ነዉ!"

ነገር ግን የእዉነት እየመጣ ያለዉ የክርስቶስ ተቃዋሚ ነዉ፡፡ እናም የክርስቶስ ተቃዋሚ ሲመጣ…

የአንድ የአለም መንግስት እንዲሁም እርሱ አዳኝ ነኝ የሚልበት የአንድ የአለም ኃይማኖት አለቃ ይሆናል፡፡

በኛ ዮሐንስ ምዕራፍ ቁጥር ላይ እንዲህ ይላል፡

(ኛ ዮሐንስ ፡) ልጆች ሆይ፤ መጨረሻዉ ሰዓት ነዉ፤ የክርስቶስም ተቃዋሚ [ፀረ-ክርስቶስ] ይመጣ ዘንድ እንደሰማችሁ

አሁን እንኳ ብዙዎች የክርስቶስ ተቃዋሚዎች ተነስተዋል፤ ስለዚህም መጨረሻዉ ሰዓት እንደሆነ እናዉቃለን፡፡

መጋቢ አንደርሰን፡ የዚህ ቃል የመጀመሪያዉ መጠቀስ የተገለጸዉ በነጠላ ነዉ ወይስ በብዛት? ስለዚህ

የክርስቶስም ተቃዋሚ (ነጠላ) እንደሚመጣ ሰምተዋል፡፡ ሰለዚህ የሚመጣዉ አንድ የክርስቶስ ተቃዋሚ ነዉ፤

ነገር ግን እስከ አሁንም የክርስቶስ ተቃዋሚዎች የሉም? ጥቅሱ የሚለዉ ያንን ነዉ፡፡ እነዚህ የክርስቶስ ተቃዋሚዎች እነማን ናቸዉ?

(ኛ ዮሐንስ ፡) ክርስቶስ አይደለም ብሎ ኢየሱስን ከሚክድ በቀር ዉሸተኛዉ ማን ነዉ?

አብንና ወልድን የሚክድ ይህ የክርስቶስ ተቃዋሚ ነዉ፡፡

መጋቢ አንደርሰን፡ ኢየሱስ ክርስቶስ አይደለም ብሎ ለማመን መጀመሪያ ክርስቶስ መኖሩን እና

ኢየሱስም አለመሆኑን ማመን አለባችሁ፡፡ "ክርስቶስ" ማለት የቃሉ ትርጉም "መሲህ" ማለት ነዉ፡፡

በዮሐንስ ወንጌል ፡ ላይ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል "መሢሕን አግኝተናል አለዉ፤ ትርጓሜዉም ክርስቶስ ማለት ነዉ"

ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ "ክርስቶስ" የሚለዉን ቃል "መሢሕ" ብሎ ይተረጉመዋል፡፡ ሁለቱ ቃላት የሚተካኩ ናቸዉ፡፡

ስለዚህ ይህን ልጠይቃችሁ፡ አንድ መሢሕ ይመጣል የሚል ሃይማኖት ማሰብ ትችላላችሁ፤

ነገር ግን ኢየሱስ አይደለም- ኢየሱስ እርሱን አይደለም፡፡ የአይሁዶች ሃይማኖት መሢሕ እንዳለ ያስተምራል፤

እሺ፤ ነገር ግን ኢየሱስ አይደለም፡፡ እነርሱ እስከ አሁን ድረስ መሢሑን እየጠበቁ ነዉ፡፡

እነርሱ ኢየሱስ መሢሑ አይደለም ይላሉ፡፡ እናም እስከ አሁን ድረስ መሢሑን እየጠበቁ ነዉ፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ ፀረ-ክርስቶስን እንደ መሢሓቸዉ አድርገዉ እንደሚቀበሉ ይናገራል፡

ኢየሱስ በማንኛዉም ሰዓት ሊመጣ ይችላል ብለዉ የሚያምን ወንጌላዊ ክርስትና፣

ያልዳኑት፣ እዉነቱን የማያምኑት፤ ብዙዎቹ ይታለሉና እንዲህ ብለዉ ያስባሉ፡

"የኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም-ምፅዓት ይህ ነዉ!" በአሁኑ ሰዓት ሙስሊሞች በእርግጥም ከመሐመድ የበለጠ

ታላቅ ነብይ እና ታላቅ መሢሕ ይመጣል ብለዉ እየጠበቁ ነዉ፡፡ ፕሬዝዳንት አህመዲነጃድ፤

የኢራን ፕሬዝዳንት- ከዚህ ቀደም ስለእሱ ሰምቶ የሚያዉቅ? ፕሬዝዳንት አህመዲነጃድ ከአመት ወይም ከሁለት

ዓመት በፊት ለዩናይትድ ስቴትስ ጀነራል አሴምብሊ ንግግር አድርጓዋል፡፡

በንግግሩም ስለ እስልምና አጭር ማብራርያ ሰጥቷል፡፡

ፕሬዝዳንት አህመዲነጃድ፡ የነቢያት መልእክት አንድ እና አንድ አይነት ነዉ፡፡

እያንዳንዱ መልዕክተኛ ከእርሱ በፊት የነበረዉን መልእክተኛ አፅድቆ ቀጥሎ ስለሚመጣዉ ነብይ ደግሞ

መልካም ዜና በመናገር በዚያን ጊዜ በነበረዉ የሰዉ አቅም ልክ የበለጠ ሃይማኖቱን ይበልጥ በተሟላ መልኩ ገልጧል፡፡

ይህ ዝንባሌ የሁሉን-አቀፍ ሃይማኖት ፍጹምነት እስከገለጸዉ የመጨረሻዉ ነብይ ድረስ ቀጥሏል፡፡

ናምሩድ ክቡር አብርሃምን ተቃወመ፡፡ ፈርዖን ክቡር ሙሴን ተቃወመ፤

ስግብግቡ ደግሞ ክቡር ኢየሱስ ክርስቶስን እና ክቡር መሀመድን ተቃወመ፡፡

ለሁሉም ነብያቶቻችን ሰላም ይሁን፡፡

መጋቢ አንደርሰን፡ እናም እንዲህ አለ እስልምና አብርሃም ታላቅ ነብይ እንደነበረ ያምናል፤ ሙሴ ታላቅ ነብይ ነበር፤

ከዚያም ኢየሱስ ነበር እና ከዚያም መሐመድ ነበር፡፡ እናም ሙስሊምዋ

ራሷን በማወዛወዝ መስማማትዋን ገለፀች ስለዚህ ይህንን ትክክል ነበርኩ ማለት ነዉ! እናም በዋናነት አህመዲነጃድ እያለ ያለዉ፡

እነዚህ ሰዎች እያንዳንዳቸዉ ቀድሞ ከመጣዉ ይልቅ የበዛ እዉነትን አምጥተዋል ምክንያቱም ሰዎች ዝግጁ እየሆኑ ሰለመጡ ነዉ፡፡

እነርሱ የበለጠ ማብራራያን፣ የበዛ ዝርዝርን እና የበዛ እዉነትን አምጥተዋል፡፡ እንዲህም አለ፡

ወደፊት ከመሐመድ የበለጠ ሌላ ነብይ ይመጣል፡፡

እና እርሱም የሚቀጥለዉን የመገለጥ ደረጃ ያመጣል፡፡ ስለዚህ እስላም መሢሓዊ ሰዉ እየፈለጉ ነዉ፡፡

ኢማም ማህዲን እየጠበቁ ነዉ፡፡

መሐመድ አህመዲነጃድ፡ ኦ እግዚአብሄር፤ የኢማም ማህዲን መምጣት አፋጥንልን፤ ጤና እና ድልን ስጠዉ፤

እናም እኛን እና ትክክለኛነቱን ለሚያረጋግጡትን ሁሉ ተከታዮቹ አድርገን፡፡

መጋቢ አንደርሰን፡ ቡድሂስቶች አምስተኛዉ ቡድሃ እስኪመጣ እየጠበቁ ነዉ፡፡

በቲቤት የሚገኙ የዳላይ ላማ ተከታዮች፡፡ ዳላይ ላማ፡ ዳላይ ላማ ከሞተ በኋላ በሌላ አካል…

እንደገና ይወለዳል ብለዉ ያምናሉ- ያ የዳላይ ላማ መንፈስ፡፡ እነርሱም የክርስቶስ ተቃዋሚ…

የዳላይ ላማ አዲስ ገፅታ ይሆናል ብለዉ ያምናሉ፡፡ ሙስሊሞች ደግሞ እሱን እንደ ኢማም ማህዲን አድርገዉ ይወስዱታል፡፡

ክርስቲያች እንደ ክርስቶስ ዳግም-ምፅዓት አድርገዉ ይወስዱታል፡፡ አይሁዶች እንደ መሢሑ አድርገዉ ይመለከቱታል፡፡

እነዚህ ዋና ዋና ሃይማኖቶች በእሱ ዙርያ ይሰበሰባሉ፤ ሰዎችም እንዲህ ይላሉ፤

"በመጨረሻ ሁላችንም መዋሃዳችን ታላቅ ነገር አይደል! ልዩነቶቻችን ወደ ጎን እያስቀመጥን ነዉ፤

እና ይህም ሰዉ እጅግ አስደናቂ ነዉ፡፡" እናም ያመልኩታል፡፡ ይህ አስመሳይ፤ የክርስቶስ ተቃዋሚ

ይመጣል፡፡ የአለም መንግስት ይሾመዋል፤ ሙሉ ስልጣንም ይሰጠዋል፡፡

እናም አምላክ ነህ ብለዉ ያዉጁለታል፡፡ የክርስቶስ ዳግም ምፅዓት እንደሆነ አድርገዉም ያዉጃሉ፡፡

በመጀመሪያ ይገደላል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ አደገኛ ቁስል በራሱ ላይ እንደሚወጣ

እናም ይህም አደገኛ ቁስል እንደሚድን ከዚያም እንደገና ወደ ህይወት እንደሚመጣ ይናገራል፡፡

ከዚያ በኋላ የኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምፅዓት ነዉ ተብሎ ይታወጅለታል፡፡ አምላክ በስጋ ተገልጦ ነዉ ተብሎ ይታወጅለታል፡፡

እናም የዚህ አለም መንግስታት ሁሉ ፤ የዚህ አለም ህዝቦች በሙሉ ይህንን ሰዉ ያመልኩታል፡፡

በጥቅሉ እያንዳንዱ ሃይማኖት እንደ መሢሓቸዉ አድርገዉ ይቀበሉታል፡፡

ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ የዳኑት በዚህ ሰዉ እንደማይታለሉ ይናገራል፡፡ የተቀረዉ አለም ግን ያመልኩታል፡፡

እንዲሁም ያምኑታል፡፡ ምክንያቱም ተአምራትን ስለሚያደርግ፤ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረዉ…

ሁሉንም ምልክቶች እና ድንቆች ያደርጋል፤ እናም ወደ እዚህ የአለም መንግስት ያመጣል፡፡

አንዳንድ ጊዜ ስለዚህ የአንድ አለም መንግስት ሰዎችን ለማስጠንቀቅ ትሞክራላችሁ፡፡

ወደ ጥሬ-ገንዘብ-አልባ ማህበረሰብ በመሄድ ሂደት ላይ እየሆኑ ስላሉ አዝማሚያዎች እያነሳችሁ

ልታስጠነቅቋቸዉ ትሞክራላችሁ፡፡ በጣም ብዙ ክርስትያኖች አሉ - ለክርስትያኖች ሰለ አንድ የአለም

መንግስት፤ ወይም ስለ ጥሬ-ገንዘብ-አልባ ህብረተሰብ እና በየቦታዉ እየተሰሩ ስላሉት

ኬላዎችን እንዲሁም የፖሊስ ግዛት ትነግሯቸዋላችሁ፡፡ እነርሱም እናንተን "የሴራ ሀሳባዉያን" ብለዉ ይጠሯችኋል፡፡

ባለፉት አመታት ዉስጥ የሴራ ሀሳባዉያን እንደተባላችሁ እርግጠኛ ነኝ፡፡

ዶ/ር ኬንት ሆቪንድ፡ አዎን፤ ብዙ ጊዜ፡፡

መጋቢ አንደርሰን፡ ነገር ግን አንድ ሰዉ ትክክለኛ መጽሐፍ ቅዱስ-አማኝ ክርስትያን ሆኖ…

አንድ ቀን የአንድ አለም መንግስት እንደሚመጣ መካድ ይችላል?

ዶክተር ኬንት ሆቪንድ፡ መፅሀፍ ቅዱስን ስታነቡ የሰይጣን እቅድ አለምን በአዲስ፣

በአንድ ስልጣን ለመግዛት እንደሆነ ሳትመለከቱ ታልፋላችሁ ብዬ አላስብም፡፡ እሱ አንድ…

የአለም መንግስትን ይፈልጋል፡፡ አምላክ መሆን ይፈልጋል፡፡

መጋቢ አንደርሰን፡ ይህ ሰዉ መላዉ አለምን በሚገዛበት ጊዜ ሁሉም ሰዉ

"የአዉሬዉን ምልክት" የሚባለዉን እንዲቀበሉ ያዝዛል፡፡ ስለ አዉሬዉ ምልክት ሰምቶ የሚያዉቅ ማን አለ?

መፅሀፍ ቅዱስ የአዉሬዉ ምልክት በቀኝ እጅ ወይም

በፊት ግንባር ላይ የሚደረግ ነገር እንደሆነ እንዲሁም ማንም ሰዉ ምልክቱ ሳይኖረዉ መግዛት ወይም መሸጥ እንደማይችል ይነግረናል፡፡

ምናልባትም ሰዎች ይህንን ከጥቂት መቶ አመታት በፊት አንብበዉ "ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል?

እንዴት ምልክቱ የሌላቸዉን ሰዎች እንዳይገዙ እና እንዳይሸጡ ማድረግ ይቻላል? ጥሬ ገንዘብ መጠቀም አይችሉም?" ብለዉ ይሆናል፡፡

ቴክኖሎጂዉ ያለበትን ሁኔታ አስቡ፡፡ ይህ በእጄ የያዝኩት ገንዘብ፤

የፌደራል የገንዘብ ኖት፤ ወረቀት ነዉ፡፡ ዋጋ የለዉም፡፡ ምንም አይነት እዉነተኛ ዋጋ የለዉም፡፡

የጥሬገንዘብ-አልባ ማህበረሰብ ይበልጥ እያደገ እያደገ

እንደመጣ ስታዩ ጥሬ ገንዘብ ከመጠቀም እየራቅን ነዉ፡፡

ሰዉየዉ በቲቪ፡ የሚጨበጥ ጥሬ ገንዘብ የሚጠፋበት ጊዜ አለ፡፡

ዜና አንከር፡ የወረቀት ገንዘብ የቀድሞ ዘመን ባህል ነዉ?

ሰዉየዉ በቲቪ፡ በአሁኑ ጊዜ አሜሪካን ሀገር ዉስጥ ከሚደረጉ ግብይቶች መካከል በመቶ እና ከዚያ በላይ የሚሆኑት…

ከጥሬ ገንዘብ ወይም ሳንቲሞች ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የላቸዉም፡፡

አዲስ ሴት፡ አንድ ቀን ይህ የሚበጨበጠዉ ጥሬ ገንዘብ ይቀር ይሆን ብላችሁ አስባችሁ ታዉቃላችሁ?

አንዳንዶች ይህን መቀበል ያለብን እዉነታ ነዉ ይላሉ፡፡ ዶላር እና ሳንቲሞች የማይመቹ እየሆኑ ነው፡፡

አፍሪካን ኦፊሻል፡ መርሁ ከጥሬ-ገንዘብ ኢኮኖሚ ወደ

ጥሬ-ገንዘብ-አልባ ኢኮኖሚ ማስተላለፍ ላይ ነዉ፡፡ ይህ ባንኮቹን ይመለከታል፡፡ ይህ የቴሌኮሚኒኬሽን ድርጅቶችን ይመለከታል፡፡

ይህ ኤቲኤም እና ፖስ አቅራቢዎችንም የሚመለከት ነዉ፡፡ የባህል ለዉጥንም ይጠይቃል፡፡

ዜና አንከር፡አሁን አሁን ገንዘብን ምንድን ነዉ የምትሉት? የሳንቲሞች እና የኖቶች ስብስብ ነዉ?

ወይስ ካርዶች ናቸዉ እየተተኩ ያሉት? እናም አንዳንድ የገንዘብ አይነቶች ወደ መጨረሻቸዉ እየመጡ ነዉ፡፡

ዶክተር ኬንት ሆቪንድ፡ እንበልና በእርሶ መንደር አካባቢ ያሉት ሱቆች በሙሉ "ጥሬ ገንዘብ መቀበል አቁመናል" ይላሉ

እና ምናልባትም "ቼኮች ወይም ክሬዲት ካርዶችን እንኳን ሳይቀር መቀበል አቁመናል…

ምክንያቱም በጣም ብዙ ማጭበርበር አለ- በጣም በርካታ የተሰረቁ ክሬዲት ካርዶች እና የተጭበረበሩ ቼኮች አሉ፡፡"

እሰቲ እንጋፈጠዉ፡፡ የወረቀት ገንዘብ ምንም አይነት ዋጋ የለዉም፡፡

ብጣሽ ወረቀት ነዉ፡፡ ምናልባትም ይህ አንድ አይነት ገንዘብ ሊሆን ይችላል፡፡ ወርቅ አይደለም፡፡

ብርም አይደለም፡፡ እዉነተኛ ዋጋ የለዉም፡፡ ስለዚህ መጀመርያ ዋጋ የሌላቸዉን

ብጣሽ ወረቀቶች መጠቀም እንድንለምድ አደረጉን፡፡ ዛሬ ይህን የወረቀት ብጣሽ ተጠቅሜ እቃዎችን እና አገልግሎቶች ማግኘት እችላለሁ፡፡

ነገር ግን አንድ ሰዉ ነገ"ያ ገንዘብ ምንም ዋጋ የለዉም" ካለ…

ምንም ዋጋ ላይኖረዉ ይችላል፡፡ የኮንፌደሬት አሜሪካን መንግስት ታስታዉሳላችሁ?

የኮንፌደሬትን ገንዘብ ታስታዉሳላችሁ? ሰዎች የኮንፌደሬቱን ገንዘብ ከፍራሻቸዉ ስር አስቀምጠዉ ነበር፡፡

እስቲ ገምቱ፤ ምንም ዋጋ አልነበረዉም፡፡ እንዲሁም እነርሱ እንዲህ አይነት ነገር ሊያደርጉ እና እንዲህም ሊልዎት ይችላሉ፡

"የወረቀት ገንዘብዎ ጥቅም አይሰጥም፡፡ አሁን ሁሉም በአካዉንትዎ በኩል ነዉ፡፡ ከፌስቡክዎ፣ ከዩትዩብ ቻናልዎ

እንዲሁም ከጂሜልዎ ጋር የተቆራኘ ነዉ፤የማንነት ስርቆት ስለሌለ በጣም አሪፍ ነዉ፡

የኪስ ቦርስዎን እቤት ረስቻለሁ ብለዉ መጨነቅ አይኖርብዎትም፡፡

ክሬዲት ካርድዎን ተስርቄያለሁ ብለዉ መጨነቅ አይኖርብዎትም፡፡ ሙሉ በሙሉ ጥሬገንዘብ-አልባ ነዉ፡፡" እፅን መቆጣጠር እንችላለን

ምክንያቱም የጥሬ ገንዘብ ግብይት ማድረግ የሚቻልበት መንገድ የለም፡፡ ይህ ወንጀልን ለመከላከል ነዉ፡፡

የዜና አቅራቢዋ ሴት፡ ፍጥነት እና ምቾትን በአንድ ላይ ያጣመረዉ ይህ የሳይንሳዊ-ልቦለድ ቴክኖሎጂ የመክፈያ ጣቢያዎች ዉስጥ ሊገባ ነዉ፡፡

የመጨረሻዉን ማንነቶን ለመስጠት ከተስማሙ…

ከዳቦ እስከ ቢራ ማንኛዉንም ነገር ከሱቅ መግዛት ይችላሉ፡፡

የኤሲኤልዩ ሰዉዬ፡ በጣም ያስፈራኛል፡፡

የዜና አቅራቢዋ ሴት፡አንድ ጊዜ የሸቀጣ-ሸቀጥ ሱቅዎ ስካን ከተደረገ በኋላ አሁን ምን ያደርጋሉ? በሌባ ጣትዎ…

የምስል ማንብበያዉን ይነካሉ፤ ከዚያም የእጅ ጣትዎን ብቻ በመጠቀም በ ሰኮንዶች ዉስጥ ይከፍላሉ፡፡

ይህ ባዬሜትሪክስ ይባላል፤ ልዩ የሆኑትን ባዮሎጂካዊ ባህርያቶን በመጠቀም…

ማንነቶን የማወቂያ አዉቶማቲክ ዘዴ ነዉ፡፡

የኤሲኤልዩ ሰዉዬ፡ ከአገልግሎቱ ምቾት የተነሳ በዚህ እንዳይሸጡ፡፡

የቀድሞ የኪዉቲ ሰራተኛ፡ አያችሁ፤ ዛሬ የጣት አሻራ ነዉ፤ ነገ ደግሞ ማይክሮቺፕ፡፡

ምናልባትም የአዉሬዉ ምልክት አስተባባሪዎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

የዜና አቅራቢዋ ሴት፡ በክዊክ ትሪፕ የምቾት ሱቅ ሰንሰለት ሰራተኛዉ ይህን ሰዉ ሲወጣ እና

ሲገባ ጣቱን እንዲያስነካ ሲጠይቀዉ ይህ ሰዉ በዛዉ ድርጅት ዉስጥ የነበረዉን የስራ አመራር ስራ አቆመ፡፡

የቀድሞ ኪዉቲ ሰራተኛ፡ ምንም እንኳን ዛሬ የግድ ባይሆንም ስለ ነገ ማን ያዉቃል፡፡

የዜና አቅራቢዋ ሴት፡ ኤክስፐርቶች ባዬሜትሪክስ በእያንዳንዱ የኢኮኖሚ እና

እለት ህይወት ላይ በሰፊዉ ዘልቆ እደሚፋፋ ይናገራሉ፡፡

የቴሌቭዥኗ ሴት፡ ጣትዎችዎን በዚያ ላይ ያስቀምጣሉ፤ ከዚያም ስሜ ይመጣል፡፡ እንዲሁም ሙሉ መረጃዬን ታገኛለች፡፡

የዜና አቅራቢዋ ሴት፡ያን ያል ፈጣን ነዉ?

የቴሌቭዥኗ ሴት፡ በጣም ፈጣን ነዉ፡፡

ወደድሽዉ? ወደድኩት፡፡

የዜና አቅራቢዋ ሴት፡ በአለም ዙርያ ያሉ ሰዎች ባዮሜትሪክስን ቀደም ብለዉ እየተጠቀሙ ይገኛሉ፡፡ የአሜሪካን መንግስት፣ አየር መንገዶች፣

ነዳጅ ማደያዎች- የዋልት ዲስኒ ወርልድ እንኳን ሳይቀሩ በቀን እንቅስቃሴዎች ምትክ የእንግዶችን የደም ስሮች…

ማንበብ የሚችል ቴክኖሎጂ ይጠቀማሉ፡፡

መጋቢ አንደርሰን፡ ይህ የአንድ አለም መንግስት በዚህች ምድር ላይ ማንም ሰዉ የአዉሬዉ ምልክት ሳይኖረዉ…

መግዛት ወይም መሸጥ እንዳይችል የሚከልክልበት

ከፍተኛ ስልጣን ይኖረዋል፡፡ ደስ የሚለዉ ነገር የኪንግ ጀምስ መፅሀፍ ቅዱስ

የአዉሬዉ ምልክት ይለዋል- ይህ ምልክት ለመግዛት

ወይም ለመሸጥ የሚስፈልግዎ ነዉ- ምልክቱም በቀኝ እጃቸዉ ወይም በፊት ግንባራቸዉ ላይ የሚደረግ ነዉ፡፡ ይህ የሆነ አይነት ተቀባሪ…

ቺፕ ሊሆን ይችላል፤ ስለዚህም ለመግዛት ወይም ለመሸጥ የሚጠበቅብዎ ይህንን ቺፕ ስካን ማድረግ ብቻ ነዉ፡፡

አንድ ቀን ይሆናል የሚሉት ምንድን ነዉ፡ "ይህ የወረቀት ገንዘብ- ያ በኪስዎ ዉስጥ ያለዉ

አንድ መቶ ዶላር- ዋጋ የለዉም፡፡ አሁን ሁሉም ነገር ኤሌክትሮኒክ ሆኗል፡፡

ወደ ሸቀጥ ሱቅ ይሄዳሉ፤ ግዢዎችዎ ይሰበሰቡና ከዚያ *ቢፕ* ብቻ፡፡

እጅ ከሌልዎት ምንም ችግር የለዉም፤ በግንባርዎ ላይ ልናረገዉ እንችላለን ምክንያቱም ሁሉም ሰዉ ራስ አለዉ!

እርስዎ እንዲሁ *ቢፕ* አድርገዉ በመክፈያዉ ላይ ይከፍላሉ፡፡ ሁሉም ገንዘብ ወደ ኤሌክትሮኒካዊ ፎርማት ይቀየራል፤

አሁን እራሱ ወደዛ በማምራት ላይ ነዉ፡፡ የሞባይል ስልኮች ስካነሮችን ማካተት ጀምረዋል፡፡

እስቲ እንበልና በሁለት ሰዎች መካከል የእቃና የአገልግሎት ልዉዉጥ አለ፡፡ እሺ እሱም $. ዶላር ነዉ፡፡

ስለዚህ እስቲ በስልኬ/ስማርትፎን/ ስካን ማድረግ እንድችል ቀኝ እጅህን ስጠኝ፡፡ *ቢፕ*

እሺ ልክ አሁን ከእሱ አካዉንት ገንዘቡን ወሰድኩኝ፡፡ ኦ ለልጄ የፒያኖ ትምህርት ሰጥተሀዋል፡፡

ልክፈልህ፡ *ቢፕ* እስቲ አሁን አስቡት፡ በስልክ/ስማርትፎን/ የአዉሬዉን ምልክትን

ስካን ማድረግ ይቻላል፤ እናም ያለ እርሱ መግዛት ወይም መሸጥ አትችሉም፡፡

ዜና አቅራቢዋ ሴት፡ ዛሬ ምሽት የህክምና ዜና ላይ የሩዝ ጥሬ የሚያክል ቺፕ ህይወቶን ሊያተርፍ እንደሚችል ተገለፀ፡፡

የአንከር ዜና፡ ዓመተ ምህረቱ እ.ኤ.አ. ነዉ፡፡ ራስዎን ስተዉና ምንም መታወቂያ ወይም የህክምና ታሪክ

ባልያዙበት ሁኔታ ወደ ሆስፒታል በፍጥነት እየተወሰዱ ነዉ፤ ከቆዳዉ ስር ላለዉ ማይክሮቺፕ ምስጋና ይግባዉና ሁሉ ነገር በዚያ ላይ ይገኛል፡፡ ከሀያ አመት በፊት…

ሳይንሳዊ ልቦለድ የነበረ፤ አሁን በባዮሜትሪክ አማካኝነት እዉነታ ሆኗል፡፡

ፕሮፌሰር፡በዚህ አስር ዓመት ዉስጥ ሰዎች ከኪስ ቦርሳዎቻቸዉ እና ከቁልፎቻቸዉ ነፃ መሆን የሚፈልጉ ከሆነ…

ባዮሜትሪክ ቴክኖሎጂ ይህንን ፍላጎት እዉን ያደርገዋል ብዬ አስባለሁ፡፡

ዜና አንከር፡ ተግዳሮቱ በዚህ ደፋርና አዲስ አለም ግላዊነታችንን መጠበቅ ነዉ፡፡

ዜና አንከር፡ አዲሱ የማይክሮቺፕ ቴክኖሎጂ

የድንገተኛ ህክምና ክፍል ሰራተኞች አንድ የኮምፒዉተር ቁልፍን በመጫን ብቻ የህክምና ታሪክዎን ማወቅ እንዲችሉ አድርጓል፡፡

የሃርቫርድ ዶክተር፡ በጣም በርካታ የድንገተኛ ህክምና ዶክተሮች ያለምንም መረጃ ኦፕራሲዮን ያደርጋሉ፡፡

የወሰዷቸዉን መድሃኒቶች እና ያሉቦትን አለርጂዎች ሳናዉቅ የሕክምና ዉሳኔዎች ማድረግ አለብን፡፡

ዜና አንከር፡ የሃርቫርዱ ዶክተር እንደተናገረዉ ከሆነ ይህ የራዲዮ ሞገድመታወቂያ ቺፕ ይህንን ችግር ሊፈታ ይችላል ይላል፡፡

ይህን በቀኝ ክንዱ ላይ አስቀብሮታል፡፡ ስካነሩ የመታወቂያ ቁጥሩን ያነባል፡፡

እነዚህ ዲጂቶች የሕክምና ታሪኩ ወደተቀመጠበት የተጠበቀ ድረ-ገፅ ይገባሉ፡፡

የኢኤምቲ ሰራተኛ ቺፑ የድንገተኛ ሰራተኞችን ሊረዳ እንደሚችል ተናግሯል፡፡

ኢኤምቲ ሰራተኛ፡ በአደጋ አእምሮአቸዉን ስተዉ…

ታካሚዎች ሲመጡ የሚያጋጥመዉ ትልቁ ችግር መረጃቸዉን ወይም የህክምና ታሪካቸዉን ሊነግሩህ አለመቻላቸዉ ነዉ፡፡

ዜና አንከር፡ የሃርቫርድ ዶክተር ጥቅሞቹ ግልፅ እንደሆኑ ይናገራል፡፡

የሃርቫርድ ዶክተር፡ እኔ የተራራ መዉጣት ስፖርተኛ ነኝ፡፡ እናም ከአንድ ገደል ላይ ብወድቅ ራሴን ስቼ እደምታገኙኝ አዉቃለሁ፡፡

ስለዚህም ስካን ተደርጌ ማንነቴን ማወቅ መቻሉ…

ከግላዊነት ስጋቴ ይልቅ ያመዝናል፡፡

ዜና አንከር፡ ቺፑ በማይሰበር መስታወት ዉስጥ የታሸገ ሲሆን መጠኑም የሩዝ ጥሬን የሚያክል ነዉ፡፡

ሄደቱ የሚካሄደዉ በማደንዘዣ ሲሆን በአንጻሩ ከህመም ነጻ ነዉ፡፡

የሃርቫርድ ዶክተር፡ ከቆዳዎ በታች የመስፊያ መርፌ እንደማስቀመጥ ነዉ፡፡

ዜና አንከር፡ ነገር ግን ከዚህ አንጻር የሆነ ነገር ከቆዳዎ ስር ማድረግ ጥሩ ነገር ነዉ ይላል፡፡

ዜና አንከር ወንድ፡ ሲጀመር እንደዚህ ነዉ፡ እዚህ ጋር ድመት አለች እናም ከአምስት አመታት በኋላ እንደተመለሰች አይተናል፡፡

ከዚያም አንድ ሰዉ እንዲህ አለ፡ “ታዉቃላችሁ…ለድመት ጥሩ ሆኖ ከተገኘ፤

እማሚ እና አባቢ እቤት ስላሉ ምናልባት እንድ ነገር ከተፈጠረ ይጠቅም ዘንድ ማይክሮቺፕን…

ከህክምና መረጃ ጋር እናስቀብር ይሆናል፡፡ ደስ ይላል፡፡“

እናም ከዚያ አንድ ሰዉ እንዲህ ይላል “ለድመቴ፣ ለቅድም አያቴ (ወንድ እና ሴት)

ጥሩ ከሆነ፣ ለልጄስ?” ቢጫ የማስጠንቀቂያ ደዉል መጠቀም አበቃ፡፡

ልጅ ተጠለፈ ብሎ መጨነቅ በጭራሽ አይገባም፡፡ ከዚያም እንዲህ እንላለን “እሺ፣ ምን እንደሆነ ታወቃላችሁ? ምናልባትም እኛ ማድረግ ሊኖርብን ይችላል፡፡

እናም ያንን ቺፕ በመጠቀም ሁሉንም ነገር ማግኘት እንችላለን፤ ክሬዲት ካርዶችን፣ የመንጃ ፈቃድ፡፡

አስቡበት የሜትሮ ካርድ፣ የኪስ ቦርሳ አይኖርም፡፡ እስቲ አስቡበት ከዛ በኋላ ቁልፍ መሸከም አይኖርብዎትም፡፡

ስለዚህ በዚህ ቤት ያላችሁትን ሰዎች ሁሉ መጠየቅ የምፈልገዉ ነገር ይህ ነዉ፡ ይህ ጥሩ ሀሳብ ነዉ?

ምክንያቱም በቀጣይ እኛም እየሄድን ያለዉ ወደዚያ ነዉ፡፡

ዜና አንከር ሴት፡ ይህ ለእኔ በጣም የሳይንስ-ልቦለድ ነዉ፤ እዉነቱን ለመናገር፡፡

ዜና አንከር ወንድ፡ እዚህ ነዉ! እዚህ ነዉ፡፡

ዜና አንከር ሴት፡ እዚህ እንደሆነ አዉቃለሁ፤ እናም ለቤት እንስሶች ነዉ ለሰዎች ግን በተገደበ መልኩ…

ዜና አንከር ወንድ፡ነገር ግን እናንተ ህጻን ናችሁ…

ዜና አንከር ሴት፡ እናንተ ህጻናት ናችሁ…እኔ የምለዉ ና….

ስቲቨን አንደርሰን፡ ባለፈዉ ዘመናት የነበሩ ሰዎች እነዚህ ጥያቄዎች ተፈጥረዉባቸዉ ይሆናል፡ “ይህ እንዴት ሊተገበር ይችላል?

ምልክት ከሌላቸዉ ሰዎች እንዴት እንዳይገዙ ወይም እንዳይሸጡ ማድረግ ይቻላል?“

ነገር ግን እያደገ ያለዉ ቴክኖሎጂ ማንም ሰዉ ያለምልክቱ መግዛት

ወይም መሸጥ እንዳይችል ለማድረግ በጣም ቀላል ያደርገዋል፡፡ እናም እሰቲ ገምቱ?አብዛኛዉን ሰዎች በቤታቸዉን ያለዉ ምግብ ለሰባት ቀናት ወይም

ለአስር ቀናት የሚበቃ ብቻ ነዉ ስለ መሸጥ ወይም መግዛት ካልቻላችሁ…

የህመም አለም ዉስጥ ነዉ የምትሆኑት፡፡ እናም በመሰረቱ የክርስቶስ ተቃዋሚውን ካላመለካችሁ ትገደላላችሁ

የሚል ህግ እንደሚወጣ መፅሀፍ ቅዱስ ይነግረናል፡፡

ይህ ሰዉ ትልቅ ሰዉ ነዉ፤ እሱ በርካታ ታላላቅ ነገሮችን እያደረገ ነዉ፤ ሰዎችንም አንድላይ እያቀራረበ ነዉ፡፡

በአንድ ነገር ብቻ ተያዘ፡ መቀበል ወይም መሞት፡፡ እናም ስለእዛ ጉዳይ ስትሰሙ እሱን ስታዩ…

ምናልባትም “እሺ፣ በዚያ መሰረት እኛ አማኞች ሁላችን የምንሞት ይመስለኛል፤

በክርስቶስ የምናምን ሁሉ፡፡ እኛ ሁላችን አንገታችን ይቀላል ብዬ እገምታለሁ፡፡

መፅሀፍ ቅዱስም ስለ እኛ መታረድ ይናገራል፡፡ እኛን ሁላችን የምንታረድ ነዉ የሚሆነዉ፡፡ “ ልትሉ ትችላላችሁ፡፡

ነገር ግን ጉዳዩ ይህ ነዉ፡ ይህ እንዲቀጥል ከተፈቀደ ትክክል ናችሁ፤ ሁሉም አማኞች ይገደላሉ፡፡

ምክንያቱም አስቡበት፣ ቴክሎጂዉን ተመልከቱ፣ በሁሉም ስፍራ የተተከሉትን የጥበቃ ካሜራዎች ተመልከቷቸዉ፤ ሳተላይቶች፡፡

አሁን ፖሊሶች ካሜራ የታጠቁ ድሮኖችን በመጠቀም እየዞሩ መብረር እና ስለእርስዎም መሰለል ይችላሉ፡፡

ስለ እርሱ አይተዋል? የቁጥጥር ድሮኖች፡፡ የምትሉትን ነገር ለመስማት እንዲያስችላቸዉ አሁን…

በመንገድ ዳርቻዎች ላይ ማይክራፎኖችን እየገጠሙ ይገኛሉ፡፡

እናም ይህ እንደ ዳይስቶፒክ ረዥም ልቦለድ “” አይነት ነዉ፡፡ይህ ሀገራችን እየሄደችበት ያለዉ መንገድ ነዉ፤

ሙሉ በሙሉ ቁጥጥር ወደሚደረግበት ማህበረሰብ፡፡እንዲሁ ወደ አዉሮፕላን የምትገቡበት ዘመን ቀርቷል፡፡

አሁን በቲኤስኤ መደረግ ይኖርብዎታል፡፡ አሁን በእርቃን አካል ስካነር ዉስጥ ማለፍ ይኖርብዎታል፡፡

አሁን ስካን መደረግ ይኖርብዎታል፡፡ መሸፈን አለብዎት፡፡

መታወቂያዎን ሁልጊዜ መያዝ ይኖርብዎታል እንዲሁም ፖሊሶች ያለማቋረጥ “መታወቂያህ የታለ? ወረቀቶች የታሉ?

ወረቀቶችህ ቅደም-ተከተላቸዉን አልጠበቁም!“ እናም አሁን እየኖርንበት ያለዉ ሀገር ይህ ነዉ፡፡

እናም ይህ ነገር ከዚህች እስር-ቤት ከሆነች ፕላኔት ማምለጥ በጣም ከባድ እስከሚሆንበት ሁኔታ ድረስ የሚቀጥል ይሆናል፡፡

ነገር ግን ይህንን ነገር ልናገር፡ በስህተት እንዳትረዱኝ ሁላችንም አንገደልም፡፡ ብዙዎች ይገደላሉ፡፡

በርካታ ክርስቲኖች ለክርስቶስ ብለዉ አንገታቸዉን ይቀላሉ፤ ይገደላሉ፡፡

ነገር ግን ይህን እላለሁ፡ ይህ ጊዜ ስለሚያጥር ሁላችንም አንሞትም፡፡ እንዲሁም መፅሀፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፡

[::.] እነዚ ቀኖችስ ባያጥሩ ሥጋ የለበሰ ሁሉ ባልዳነም ነበር፤ ነገር ግን እነዚያ ቀኖች ስለ ተመረጡት ሰዎች ያጥራሉ፡፡

መጋቢ አንደርሰን፡ እናም መፅሀፍ ቅዱስ አንደሚናገረዉ በዚህ መሀል ኢየሱስ ክርስቶስ ይመለሳል፡፡

ቅድም ስለ ክርስቶስ ዳግም-ምፅዓት የተነጋገርነዉን አስታዉሱ፡፡ እርሱ ይመለሳል፡፡

ልክ ክርስትናን አሸንፈናል ብለዉ ሲያስቡ፤ አለም-አቀፋዊ መንግስታቸዉን ሲያገኙ፣ ሰይጣን ከላይ ዋናቸዉ ሆኖ የአንድ አለም መንግስትን ሲያገኙ ኢየሱስ ክርስቶስ በደመናዎች ዉስጥ ይመጣል፡፡

እናም ያኔ ነው መነጠቅ ሲሆን የሚሆነው እንዲሁም እግዚአብሄር

ቁጣዉን ማውረድ የሚጀምረዉ በዚያን ጊዜ ነዉ፡፡ ስለዚህ ድርጊት በዮሀንስ ራዕይ መፅሀፍ ላይ ማንበብ ትችላላችሁ፡፡

ዉሃን ወደ ደም ይቀይራል፡፡ ዛፎችና ሳርን በእሳት ይለበልባል፡፡

በጅራታቸዉ ላይ ባለ መውጊያ ሰዎችን እንደ ጊንጥ የሚናደፉ አንበጣዎችን ከሲኦል ይልካል፡፡

የራዕይ መፅሀፍን ካላነበባችሁ እንድታነቡ አበክሬ አበረታታችኋለሁ፡፡

እናም ኤንአይቪዉን (አዲሱ መደበኛ ትርጉምን) አታንብቡ፡፡ የኪንግ ጀምስ እትም አንብቡ፤ እሺ? ለማንበብ ጊዜ የምትወስዱ ከሆነ…

…ለምን ትክክለኛዉን ነገር አታነቡም? ተመሳሳይ ነገርን አትቀበሉ፡፡ ምዕራፍ ቁጥር ን ተመልከቱ:

(የዮሀንስ ራዕይ ፡) አንድም አዉሬ ከባህር ሲወጣ አየሁ፤

አሥር ቀንዶችና ሰባት ራሶች ነበሩት፤ በቀንዶቹም ላይ አሥር ዘዉዶች ላይ በራሶቹም

ላይ የስድብ ስም ነበር፡፡

(የዮሀንስ ራዕይ ፡) ያየሁትም አዉሬ ነብር ይመስል ነበር፤

እግሮቹም እንደ ድብ እግሮች፤ አፉም እንደ አንበሳ አፍ ነበሩ፡፡

ዘንዶዉም ኃይሉንና ዙፋኑን ትልቅም ስልጣን ሰጠዉ፡፡

መጋቢ አንደርሰን፡ ስለዚህ በዚህ የተገለፀዉ ይህ አዉሬ፤ መፅሀፍ ቅዱስ እንደሚናገረዉ

ዘንዶዉ ነዉ ሀይሉንና ዙፋኑን እንዲሁም ሥልጣኑን የሚሰጠዉ፡፡ በቁጥር ላይ ተመልከቴ፡

(የዮሀንስ ራዕይ ፡) ከራሶቹም ለሞት አንደ ታረደ ሆኖ አንዱን አየሁ፤

ለሞቱ የሆነዉም ቁስል ተፈወሰ፡፡ ምድርም ሁሉ አዉሬዉን እየተከተለ ተደነቀ፤

ለዘንዶዉም ሰገዱለት፤ ለአዉሬዉ ሥልጣንን ሰጥቶታልናለ ለአዉሬዉም፡፡

አዉሬዉን ማን ይመስለዋል፤ እርሱንስ ሊዋጋ ማን ይችላል? እያሉ ሰገዱለት፡፡

ታላቅንም ነገርና ስድብን የሚናገርበት አፍ ተሰጠዉ፤ በአርባ ሁለት ወርም እንዲሰራ ሥልጣን ተሰጠዉ፡፡

መጋቢ አንደርሰን፡ አሁን አርባ እና ሁለት ወራት ከጊዜ ጋር ደዉልን ይደዉላሉ፤ እና ጊዜዓትና እና ገሚሱ ጊዜ እና

አንድ ሺህ ሁለት መቶ እና ስድስት ቀናት? እነዚህ ነገሮች እንዴት እንደተያያዙ ተመልከቱ? በቁጥር ላይ አንዲህ ይላል፡

(የዮሀንስ ራዕይ ፡) እግዚአብሄርንም ለመሳደብ ስሙንና ማደርያዉንም

በሰማይ የሚያድሩትን ሊሳደብ አፉን ከፈተ፡፡

መጋቢ አንደርሰን፡ ይህንን ተመልከቱ፡ ቁጥር ሰባት፡፡ ቁልፉ ይህ ነዉ፡

(የዮሀንስ ራዕይ ፡) ቅዱሳንንም ይዋጋ ዘንድ ድልም ያደርጋቸዉ ዘንድ ተሰጠዉ፤

በነገድና በወገንም በቋንቋም በሕዝብም ሁሉ ላይ ሥልጣን ተሰጠዉ፡፡

መጋቢ አንደርሰን፡ አሁን የዘንዶዉ ግብ በክርስቶስ በሚያምኑትና የእግዚአብሄርን ትዕዛዛት የሚጠብቁትን መዋጋት መሆኑን

በምዕራፍ ቁጥር ላይ አላየንም?

እዚህ ላይ ከቅዱሳን ጋር እንዲዋጋ ተሰጠዉ ይላል- ተመልከቱ - ሊያሸንፋቸዉ፡፡

በቅዱሳን እና በዲያብሎስ መካከል በዚህ ምድር ላይ በሚደረገዉ ጦርነት አሸናፊዉ ማነዉ? ዲያብሎስ

እሱ ከቅዱሳን ጋር ጦርነት እንደሚያደርግና ድል እንደሚያደርጋቸዉ ይናገራል፡፡

የዮሐንስ ራዕይ ፤ የየክርስቶስ ተቃዋሚው አላማ ከቅዱሳን ጋር ጦርነትን ማድረግ ነዉ፡፡

ስለዚህም ክርስቲያኖች ስቃይን/ጭፍጨፋን ለማስወገድ የአዉሬዉን ምልክት እንዲቀበሉ አይፈልግም፡፡ ሁሉም ክርስቲያኖች

እንዲሞቱ ይፈልጋል፡፡ “ኦ ይህ የሚያስጨንቅ ነዉ” ልትሉ ትችላላችሁ፡፡ እሺ እስከ መፅሀፉ መጨረሻ ድረስ አንብቡና

ከዚያም በመጨረሻ ማን እንደሚያሸንፍ ታያላችሁ፡፡ ይህ በምዕራፍ ላይ የተቀመጠዉ ጊዜያዊ መሰናክል ብቻ ነዉ፡፡

ነገር ግን በቁጥር ላይ እንዲህ ይላል

(የዮሀንስ ራዕይ ፡-) ቅዱሳንንም ይዋጋ ዘንድ

ድልም ያደርጋቸዉ ዘንድ ተሰጠዉ፤ በነገድና በወገንም በቋንቋም በሕዝብም ሁሉ ላይ ሥልጣን ተሰጠዉ፡፡

ከዓለምም ፍጥረት ጀምሮ በታረደዉ በግ ሕይወት መጽሐፍ

ስሞቻቸዉ ያልተፃፉ በምድር የሚኖሩ ሁሉ ይሰግዱለታል፡፡

መጋቢ አንደርሰን፡ ስለዚህ ይህ አዉሬዉ የተባለዉ ሰዉ

በሁሉም መንግስታት፣ ነገዶችና ቋንቋዎች ላይ ስልጣን አለዉ፡፡ ግቡም ከቅዱሳን ጋር ጦርነት ማድረግ ነዉ፡፡

እናም መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረዉም በዚህ ምድር ያሉ ሁሉ ያመልኩታል፡፡ እዚህ ጋር ቆም ይበሉ፡፡ አይደለም፤ እንደሱ አይደለም፡፡

የሚለዉ ይህንን ነዉ፡ ከዓለምም ፍጥረት ጀምሮ

በታረደዉ በግ ሕይወት መጽሐፍ ስሞቻቸዉ ያልተፃፉ በምድር የሚኖሩ ሁሉ ይሰግዱለታል፡፡ ስለዚህ ይህንን ጥያቄ ልጠይቃችሁ፡

ስማቸዉ በህይወት መዝገብ ላይ የተጻፉ ያመልኩታል? የለም፡፡ ሆኖም መፅሀፍ ቅዱስ እንደሚናገረው…

የተመረጡትን ማሳት እስኪችል ድረስ በጣም ሊያምኑት የሚችል እና የረጋ ይሆናል፤

ነገር ግን እግዚአብሄር የዳኑ ሁሉ በዚህ ሰዉ እንዲታለሉ አይፈቅድም፡፡ ስለዚህ ሁሉም የእዉነት የዳኑ ሁሉ…

በቅድመ-መከራ መነጠቅ የተያዙትንም እንኳን ሳይቀር

እነዚህ ነገሮች እየሆኑ ሲያዩአቸዉ ወይም እንደመታደል ሆኖ ይህንን ዶክመንተሪ ያዩና “እስቲ ቆይ አንዴ፤

ይህ ነገር እየተፈጸመ ነዉ፤ ይህ የክርስቶስ ተቃዋሚው ነዉ፡፡ ይህንን ማድረግ አልችልም፡፡ ይህንን ሰዉ ማምለክ የለብኝም፡፡

ይህ እዉተኛዉ ክርስቶስ አይደለም፡፡“ ብለው ማሰብ ይጀምራሉ ስለዚህ የማያመልኩት ሁሉ ይገደላሉ፡፡

እንዲሁም የማያመልከዉ ማንኛዉም ሰዉ መግዛት ወይም መሸጥ አይችልም፡፡

እንዲሁ ዝም ብላቸዉ ወደ ዋልግሪን ሄዳችሁ የአዉሬዉን ምልክት አትቀበሉም፡፡ ይህ እንዲሁ ፖስታ ቤት የምታሳዩት ነገር አይሆንም፡፡

“እሺ፣ መግዛት ወይም መሸጥ እችል ዘንድ ቺፕ ማግኘት እችላለሁ? “የለም፤ መፅሀፍ ቅዱስ ግልፅ ነዉ፡፡

ቺፑን ለመቀበል የግድ የክርስቶስ ተቃዋሚውን ማምለክ የግድ ነዉ፡፡

አሁን ከበርካታ አስርት አመታት በፊት እንኳን የዉሸት መመርመርያዎች ነበሩ፡፡ አሁን የአእምሮ ስካነር አይነት ቴክኖሎጂዎችን እየሰሩ ናቸዉ፡፡

ምናልባትም የአዉሬዉን ምልክት ለማግኘት

የክርስቶስ ተቃዋሚውን ማምለክ እና ለፀረ-ክርስቶሱ ታማኝ ለመሆን ቃል-ኪዳን መግባት ያስፈልጋል ብዬ አምናለሁ፡፡

እናም እሱ እዉነት እየተናገራችሁ መሆናችሁን ያዉቃል፡፡

ዜና አንከር፡ ሳይንሳዊ-ልቦለድ ይኸዉ፡፡ ነገ እዚህ ነዉ፡፡

መጋቢ አንደርሰን፡ ይህ ብቻ አይደለም፤ ካሰባችሁበት ግን ትራንስፖርቱ አሁን በጣም በቁጥጥር ዉስጥ ነዉ፡፡

በአዉራ ጎዳናዎች ላይ ለመንዳት ስትሞክሩ ኬላዎች አሉ፡፡

ከዚያም በአዉሮፕላን መሄድ ስትፈልጉ ደግሞ ቲኤስኤ የእርቃን አካል መፈተሻ ዉስጥ ያሳልፋችኋል፡፡

ለአዉሬዉ ሰግዳችሁና አዉሬዉን አምልካችሁ ምልክቱን ካልተቀበላችሁ

በህብረተሰቡ ዉስጥ መኖር እንዳችሉ

የቁጥጥር መረቡ በቦታው ላይ የተቀመጠ ይመስላል፡፡

ኬንት ሆቪንድ፡ በጣም ትክክል፡፡ እናም እኛ ተንኮል ይደረግብናል፡፡

ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱ በስሙ የተነሳ እንደሚጠሉ በጣም በግልጽ ተናግሯል፡፡

እየቀረጹ ያሉትን አስደናቂ የዚህ አዲስ የአለም አገዛዝን የማይደግፍ ማንኛዉም ሰዉ እንደ ጠላት ይታያል፡፡

ለምሳሌ የነርሰሪ ክፍል ተማሪ ልጅዎን ወደ ትምህርት ቤት ሲወስዱ

ልጆችዎ ካልተከተቡ ወደ ትምህርት ቤት መምጣት አይችሉም ይሏችኋል፡፡ እሺ፣ ምናልባት እርስዎ

የክትባት ጥላቻ ቢኖርብዎትና እንዲህ ቢሉስ “ምናልባትም ኦቲዝም/የአእምሮ ዝግመት የሚያመጣዉ ይህ ይሆናል ብዬ አስባለሁ፡፡

ይህ የበርካታ ነገሮች መነሻ ሊሆን ይችላል፡፡ አላዉቅም፤ ነገር ግን እድሌን መዉሰድ አልፈልግም፡፡

እናም በርካታ መጠንን ለመቋቋም ጥቂት መርዝ ወደ ሰዉነቶ በመርፌ በኩል ከሚወጋ ክትባት ጋር የሚመጣን ነገር

በመፅሀፍ ቅዱስ ዉስጥ አላየሁም፡፡”

መጋቢ አንደርሰን፡ ትክክል፤ ትክክል፡፡

ኬንት ሆቪንድ፡ ሃቁ ምንድን ነዉ፡ ትምህርት ቤቱ ካልተከተባችሁ መምጣት አትችሉም አለ፤ ስለዚህ አሁን ምርጫ አለችሁ፡፡

በፀና እምነታችሁ ትቆማላችሁ ወይስ

ሰግዳችሁ ለምቾት ስትሉ ልጆዎን ለክትባት አሳልፈዉ ይሰጣሉ? ከአዉሬዉ ምልክት ጋር አንድ ነዉ የሚሆነዉ፡፡

ከ ዓመት በፊት እንደተጀመረዉ የሶሻል ሲኪዩሪቲ ቁጥር ጋር አንድ ነዉ፡፡ ሰዎች ቁጥር እንዲኖራቸዉ አይፈልጉም ነበር፡፡

“ኦ…እኔ ስም ነኝ፡፡“ እናም አሁን ሁሉም

ሰዉ ኖርዎት ስለ እዚህ ማሰብ እንኳን አቁመዋል፡፡ ይህ አንድ የአለም መንግስት ወደማቋቋም

የመጨረሻዉ ግብ የሚያዲርሱ እርምጃ አንድ፣ ሁለት ወይም ሶስት ይሆኑ?

መጋቢ አንደርሰን፡ ሰይጣን ከሰማይ ተጥሏል፡፡ አጭር ጊዜ እንዳለዉም ያዉቃል፡፡

ከአማኞች እና ከቅዱሳን ጋር ዉጊያን ያደርጋል፡፡ እናም ምን ያደርጋል? ይህንንም የሚያደርገዉ

አንድን ሰዉ በሥልጣን ላይ በማስቀመጥ ነዉ፤ አላደረገም እንዴ? ዘንዶዉ ሀይሉን ሰጥቶታል፡፡ አንድን ሰዉ

በመላዉ አለም ላይ፣ በሁሉ ነገድ ላይ፣ በሁሉ ቋንቋ ላይ ባለስልጣን አድርጎ ያስቀምጣል፡፡ እናም ይህ ሰዉ ከቅዱሳን ጋር የሚደረገዉን የዲያብሎስ ጦርነት ያስፈፅማል፡፡

መፅሀፍ ቅዱስ በቁጥር ላይ እንዲህ ይላል፡

(የዮሐንስ ራዕይ :-) ሌላም አዉሬ ከምድር ሲወጣ አየሁ፤

የበግ ቀንዶችን የሚመስሉ ሁለት ቀንዶችም ነበሩት እንደ ዘንዶም ይናገር ነበር፡፡ በፊተኛዉም አዉሬ ሥልጣን

በእርሱ ፊት ሁሉን ያደርጋል፡፡ ለሞቱ የሆነዉም ቁስል ተፈወሰለት

ለፊተኛዉ አዉሬ ምድርና በእርሱ የሚኖሩት እንዲሰግዱለት ያደርጋል፡፡

መጋቢ አንደርሰን፡ ስለዚህ በዚህ ቦታ ላይ ይህ ሰዉ አምልኮን እየጠየቀ ነዉ፡፡ በቁጥር ላይ እንዲህ ይላል፡

(የዮሐንስ ራዕይ :-) እሳትን እንኳን

ከሰማይ ወደ ምድር በሰዉ ፊት እስኪያወርድ ድረስ

ታላላቆችን ምልክቶች ያደርጋል፡፡ በአዉሬዉም ፊት ያደርግ ዘንድ ከተሰጡት ምልክቶች የተነሣ በምድር የሚኖሩትን ያስታል፤

የሰይፍም ቁስል ለነበረዉና በሕይወት ለኖረዉ ለአዉሬዉ ምስልን እንዲያደርጉ

በምድር የሚኖሩትን ይናገራል፡፡

[::.] የአዉሬዉ ምስል ሊናገር እንኳ

ለአዉሬዉም ምስል የማይሰግዱትን

ሁሉ ሊያስገድላቸዉ፤ ለአዉሬዉ ምስል ትንፋሽ እንዲሰጠዉ ተሰጠዉ፡፡

መጋቢ አንደርሰን፡ እንዲህ ትላላችሁ “በአለም ውስጥ ለአዉሬዉ ምስል ህይወት የሰጠዉ ምንድነው?“

ወደ እዚህ በጣም እየተጠጋንና እየተጠጋን ስንመጣ

ቴክኖሎጂዉን በበለጠ እየተረዳነዉ እንመጣለን ብዬ አስባለሁ፤ ስለዚህ ምን አይነት ምስል እንደሚሆን በትክክል አላወቅኩም፡፡

ነገር ግን መናገር የሚችል እና

የማያመልኩትን ሁሉ ሊያስገድል የሚችል የሆነ የአዉሬ ምስል ነዉ፡፡ አሁን እነዚህ ነገሮች

ዳንኤል ምዕራፍ ን ያስታዉሱኛል፡፡ በዚያን ጊዜ በሰለጠነዉ አለም ላይ ንጉስ የነበረዉን ናቡከደነፆርን ታስታዉሱታላችሁ?

እንዴት ትልቅ ምስል እንደሰራ እና እንዲያመልኩት እንዳደረገ ታስታዉሳላችሁ?

እናም ያንን ምስል ካላመለኩ ምን ይመጣል? ይገደላሉ፤ አይደል? እዚህ ጋር ከምናየዉ ጋር ተመሳሳይ አይደለም?

ያ የክርስቶስ ተቃዋሚው ምስል ነዉ፡፡ ቁጥር ን ተመልከቱ፡፡ ቁልፉ ይኸዉ፡

(የዮሐንስ ራዕይ :-) ታናናሾችና ታላላቆችም ባለ ጠጋዎችና ድሆችም

ጌታዎችና ባርያዎችም ሁሉ በቀኝ እጃቸዉ ወይም በግምባራቸዉ ምልክትን እንዲቀበሉ፤

የአወሬዉም ስም ወይም የስሙ ቁጥር ያለዉ ምልክት የሌለበት ምንም

ሊገዛ ወይም ሊሸጥ እንዳይችል ያደርጋል፡፡ ጥበብ በዚህ አለ፡፡

አእምሮ ያለዉ የአዉሬዉን ቁጥር ይቁጠረዉ፤ ቁጥሩ የሰዉ ቁጥር ነዉና፤ ቁጥሩም ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት ነዉ[]፡፡

መጋቢ አንደርሰን፡ ይህ ሰይጣን አማኞችን ለማሰቀየት ከሚጠቀምባቸዉ መሳሪያዎች መካካል አንዱ ነዉ፡፡

የአዉሬዉ ምልክት ከቅዱሳን ጋር ጦርነት ለማድረግ የሚጠቀምበት መሳርያ ነዉ፡፡ ምክንያቱም

መግዛት ወይም መሸጥ ካልቻላችሁ በዘንድሮዉ አለም ላይ መኖር በጣም ከባድ ነዉ፤

አይደለም እንዴ? ወይም በማንኛዉም አለም፡፡

ስለዚህ የክርስቶስ ተቃዋሚውን የማታመልኩ ከሆነ ትገደላላችሁ የሚል ህግ ማዉጣት ብቻ ሳይሆን እዚህም እራሱ ስቃይ ነዉ፡፡

ያም ከቅዱሳን ጋር መዋጋት ነዉ፡፡ እሱ ደግሞ ቅዱሳን የአዉሬዉ ምልክት ስለሌላቸዉ መግዛት

ወይም መሸጥ እንዳይችሉ ያደርጋል፡፡

እንዲሁም የአዉሬዉ ምልክት የሚሰጠዉ አዉሬዉን ለሚያልኩ ብቻ ነዉ፡፡ እናም የዳኑት፤

ቅዱሳን አዉሬዉን አያመልኩትም፡፡ መፅሀፍ ቅዱስ ስለዚህ ጉዳይ

በማቴዎስ እና በሌሎች ቦታዎች ላይ በግልፅ አስቀምጦታል፡፡ ስለዚህ መግዛትም ወይም መሸጥ አይችሉም፡፡

እንዲሁም እንደሚሞቱ የተረጋገጠ ነዉ፡፡ አሁን እስቲ ራሳችሁን በአንድ አለም ላይ አስቡት -

በአንድ መንግስት ዉስጥ አላልኩም፤ በአንድ ሀገር ዉስጥ አላልኩም፤ እኔ ያልኩት በአንድ አለም ዉስጥ ነዉ- መግዛት

ወይም መሸጥ በማትችሉበት እና ለመሞት ማረጋገጫ ደርሶት ባለበት ሁኔታ፡፡

በእንደዚህ አይነት አለም ዉስጥ መተረፍ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ መገመት ትችላላችሁ? እሱ ብቻ አይደለም፤

እየገቡ ያሉትስ የቁጥጥር ካሜራዎች? የፈቃድ ሰሌዳ ማንበቢያ ካሜራዎችስ?

የእርቃነ አካል ስካነሮችስ? በየኬላዎች የመታወቂያህን አሳየኝ ጥያቄዎችስ?

ባቡር ዉስጥ ለመግባት መታወቂያህ አሳየኝስ? ወደ አዉሮፕላን ዉስጥ ለመግባት መታወቂያህ አሳየኝስ? እናም ም መሰላችሁ

በጣም በቅርቡ ሌላ ነገር ማሳየት ይኖርባችኋል፡፡ “እስቲ ቀኝ እጅህን ልየዉ፡፡

እሺ ማለፍ ትችላለህ፡፡ መልካም ቀን ይሁንልህ” ይህ በአጠቃላይ የማይሆን ነገር አይደለም፡፡

ከጥቂት መቶ አመታት በፊት ሰዎች ይህንን ሲያነቡ እኛ እንደምናየዉ አያዩትም፡፡

እኛ ስናየዉ በትንሹ ስጋ ለብሷል፤ አይደለም እንዴ?

ለእዚህም ነዉ ይህ ቅርብ ሊሆን እንደሚችል የማስበዉ፡፡ የዘንድሮ ክርስትያኖች ለዚህ በጭራሽ ዝግጁ አይደሉም፡፡

በፍጹም ዝግጁ አይደሉም፡፡ ምን ማድረግ እንዳለባችሁ ታዉቃላችሁ? በመንፈሳዊ ነገር ራሳችሁን ማዘጋጀት

እና ዝግጁ መሆን አለባችሁ፡፡ ስለዚህ በኋላ “ምን እየሆነ ነዉ?” አትሉም፡፡ ዝግጁ መሆን አለባችሁ፡፡

መዘጋጀት አለባችሁ፡፡ ለዚህም ነዉ እግዚአብሄር በተደጋጋሚ የሚያስጠነቅቀንና የሚስጠነቅቀንና የሚስጠነቅቀንና…

የሚስጠነቅቀን፡፡ ስለዚህም ነዉ ጳዉሎስ በጊዜዉ የነበሩትን ህዝቦች ያስጠነቀቃቸዉ፡፡

እነርሱ የታላቁን መከራ ቀናት እያሳለፉ እንዳልሆነ ግልፅ ነዉ፡፡ ነገር ግን ማንኛዉም አማኝ በመከራ ዉስጥ እንደሚያልፍ

እነርሱም በራሳቸዉ መከራዎች ዉስጥ አልፈዋል፡፡ እንዲህ አላቸዉ፡ “እኛ አስጠነቀቅናችሁ፡፡ እኛ ከእናንተ ጋር

በነበርን ጊዜ፤ እዉነት እኛ መከራን እንደምንቀበልና እንደሚልፍ እንድታዉቁት ቀድመን ነግረናችኋል፡፡”

ስለሆነም መንቃት እና መረዳት አለብን ከዚያ

መቋቋም እንድንችል፡፡

ሮናልድ ራስሙሴን፡ በአሁኑ ጊዜ ክርስትያኖች በታላቁ መከራ ጊዜ ስለሚሆኑ ክስተቶች እንዲጠነቀቁ እየተደረገ አይደለም፡፡

በምትኩ በአሜሪካ ዙርያ የሚገኙ መጋቢዎች

የክርስቶስ ተቃዋሚው በቅዱሳን ላይ ጦርነት ከማድረጉ በፊት መነጠቁ እንደሚሆን እና

መነጠቅ በእግዚአብሄር ትንቢታዊ አጀንዳ ዉስጥ የመጀመርያ ነዉ ብለዉ ለህዝቦቻቸዉ ያስተምራሉ፡፡

ይህ አስተምህሮ አይቀሬ ይባላል፤ ክርስቶስ በማንኛዉም ሰዓት በደመናዎች ዉስጥ ተመልሶ ሊመጣ ይችላል እንዲሁም ስለ መምጣቱም…

ምንም አይነት ምልክቶች አይኖሩም ብሎ ያስተምራል፡፡ ሆኖም መፅሀፍ ቅዱስ የክርስቶስ ምፅዓት

ዝምብሎ የሚሆን እንዳልሆነ እና በቅድሚያ መሆን ያለባቸዉ ሌሎች ክስተቶች እንዳሉ ያስተመራል፡፡

መጋቢ አንደርሰን፡ ምናልባትም ኢየሱስ ዛሬም ሊመጣ ይችላል የሚለዉን አስተምህሮ ሰምታችሁ ሊሆን ይችላል፡፡

ይህንን ከዚህ ቀደም የሰማ ማነዉ? ይህ ግልፅ ያልሆነ የክርስቶስ ምፅዓት ይባላል፡፡

ሰዎች ኢየሱስ በማንኛዉም ሰዓት ይመጣል ሲሉኝ

እኔ ደግሞ ብዙ ጊዜ ይህንን ጥያቄ እጠይቃቸዋለሁ “መፅሀፍ ቅዱስ ምን ላይ ነዉ እንደዛ የሚለዉ?”፡፡

እናም ያለ ምንም ጥርጣሬ የሚመልሱልኝ ነገር “መፅሀፍ ቅዱስ የመምጫዉን ቀን ወይም ሰዓት ማንም አያዉቅም ይላል“ የሚለዉን ነዉ፡፡

በጣም ብዙ ጊዜ ሊያሳዩአችሁ አይችሉም፤ ሰለዚህም እንዲያገኙት ልትረዷቸዉ ይገባል፡፡

እና እንዲህ አለ “ኦ…ፊት ለፊቴ የለም፡፡ ምዕራፉን በትክክል አላዉቀዉም፡፡

ነገር ግን ኢየሱስ ቀኑን ወይም ሰዓቱን ማንም አያዉቀዉም ብሎ እንደተናገረ አዉቃለሁ፡፡”

እኔም “እኔ እንድረዳህ ፍቀድልኝ፡ እሱ የተናገረዉ በማቴዎስ ወንጌል ፡ ላይ ነዉ” አልኩት፡፡ መፅሀፍ ቅዱስ ምን እንደሚል ላንብብልህ

ምክንያቱም ይህ እንዴት ኢ-መፅሀፍ ቅዱሳዊ እንደሆነ ላሳያችሁ እፈልጋለሁ፡፡ ምክንያቱም ይህ እጅግ አስፈላጊ ክርስትና ነዉ፡፡

ልክ አሁን ወደ ክርስቲያን መፃህፍት መደብር ብትወርዱ የተለያዩ አይነት መፅሃፍትን እና ቪድዮዎችን ይኖሯቸዋል፡፡

“ሌፍት ቢሃይንድ?”/ “ወደኋላ ቀርተዋል?” ስለተሰኘዉ ፊልም ሰምቶ የሚያዉቅ ማነዉ? ሙሉ በሙሉ ተረት፡፡

ከመፅሀፍ ቅዱስ ጋር ምንም አይገናኝም፡፡ ሙሉ በሙሉ ኢ-መፅሀፍ ቅዱሳዊ ነዉ፡፡ እናም መፅሀፍ ቅዱስ በማቴዎስ ወንጌል ፡ ላይ እንዲህ ይላል፡

[::.] ስለዚያች ቀንና ስለዚያች ሰዓት ግን ከአባት ብቻ በቀር

የሰማይ መላዕክትም ቢሆኑ ልጅም ቢሆን የሚያዉቅ የለም፡፡

መጋቢ አንደርሰን፡ ስለዚህ ሰዎች ያንን ጥቅስ ይወስዱና እንዲህ ይላሉ፡ “እዚህ ጋር ተመልከትህ? ማንም ሰው

ቀኑን ወይም ሰዓቱን አያዉቅም፡፡ ይህም ማለት በማንኛዉም ቅፅበት ሊሆን ይችላል፡፡” ነገር ግን አስተዉሉ

እርሱ ያለዉ፡ “ማንም ቀኑን ወይም ሰዓቱን አያዉቅም፡፡” ስለዚህ ጥያቄዉ የሚሆነው፡

“የትኛዉ ቀን?” የሚለዉ ነዉ፡፡ ስለእሱ ልክ አዉርቶ የጨረሰዉ ቀን ነዉ፡፡ ነገሩ ይህ ነዉ፡

በቁጥር ላይ ተመልሰን ስናይ ቀኑ ከመከራዉ በኋላ እንደሆነ ይናገራል፡፡ በቁጥር ላይ እንዲህ ይላል፡

ልክ ከመከራዉ በኋላ

መጋቢ አንደርሰን፡ የሚሆኑትን ክስተቶች ያብራራል፡፡ ከዚያም እንዲህ ይላል፡

[::.] ስለዚያች ቀንና ስለዚያች ሰዓት ግን ከአባት ብቻ በቀር የሰማይ መላዕክትም ቢሆኑ ልጅም ቢሆን የሚያዉቅ የለም፡፡

መጋቢ አንደርሰን፡ ስለዚህ ቀኑን ወይም ሰዓቱን አናዉቀዉም፡፡ አንድ ነገር በእርግጥ የምናዉቀዉ ግን

ከመከራዉ በኋላ እንደሆነ ነዉ፡፡ በቅድመ-መከራ መነጠቅ የሚያምኑ ሰዎች

እነዚህን የአእምሮ ጂምናስቲኮች ይሰራሉ በዚያም ልታሳይዋቸዉ ትሞክራላችሁ “ተመልከቱ ከመከራዉ በኋላ ይላል” ብላችሁ፡፡

እነሱ ድግሞ እንደዚህ ይሏችኋል፡ ”ያ ስለ መነጠቅ አይደለም፤ ያኛዉ መነጠቅ አይደለም ”::

እናንተም ”እሺ፣ እንዴት አወቅህ?” ትላላችሁ ”ምክንያቱም ከመከራዉ በኋላ ስለሆነ ነዉ፡፡

እናም በእርግጥ መነጠቁ ከመከራዉ በኋላ እንደሆነ እናዉቃለን፡፡”

ከዚያም “እሺ በየትኛዉ ክፍል ላይ ነዉ መፅሀፍ ቅዱስ መነጠቁ በማንኛዉም ቅፅበት ሊሆን ይችላል?“

ብላችሁ ትጠይቋቸዋላችሁ “እሺ እዛዉ ጋር ማንም ቀኑን ወይም ሰዓቱን አያዉቅም ይላል“

“ቀደም ብለህ ይህ ስለ መነጠቅ አይደለም ብለህ ነበር፡፡“ ስለዚህ ከመከራዉ በኋላ ሲል…

ማቴዎስ ወንጌል ስለ መነጠቅ አይደለም፡፡ ነገር ግን ማንም ቀኑን ወይም ሰዓቱን አያዉቅም ሲል

አሁን በድንገት የማቴዎስ ወንጌል እንደገና ሰለ መነጠቅ ሆነ፡፡ ቀጥሎ ምን ይላል፡ ሁለት ሰዎች በሜዳ ላይ ነበሩ፡

አንዱ ይወሰዳል አንዱ ይቀራል፤ እሺ ያም ስለ መነጠቅ ነዉ እንደገና፡፡

ዝም ብለህ የተባልከዉን አድርግ፡፡ ዝም በልና በቅድመ-መከራ መነጠቅ እመን ምክንያቱም እኔ ብያለሁና“

“ለሁለቱም አቋሞች ቦታ ስጥ፤ ፍትሃዊ ሁን፤ ለሁለቱም ስጥ“፡፡ “እሺ ሌላኛዉ ጎራ ይህን ይመስላል፡“

“ዝም በልና እንድትል የነገርኩህን ነገር እመን እናም ጥያቄዎች መጠየቅ አቁም፡፡

ዝም በል እና እመን ምክንያቱም እኔ ብያለሁና“፡፡ ይህ ቅድመ-መከራ መነጠቅ አስተምህሮ ጎራ ነዉ፡፡ እዉነት ነዉ፤

ምንም የያዙት ነገር የለም፡፡ እኔ በቃል ላይ ቃል በጥቅስ ላይ ጥቅስ ይዣለሁ፤ እነርሱ ግን ምንም የላቸዉም፡፡

ቢያንስ ቢያንስ ሌሎቹ የዉሸት አስተምህሮዎች ከአንድ የመፅሀፍ ቅዱስ ጥቅስ ላይ ተነስተዉ ነዉ የሚያጣምሙት

እናም ሰዎች አንድ ጥቅስ ወስደዉ ከአገባቡ ዉጪ ይተረጉሙት እና ያጣምሙታል፡፡

የቅድመ-መከራ መነጠቅ አንድ ጥቅስን እንኳን የሚያጣምም አይደለም፡፡ ምንም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ የላቸዉም፡፡

ከመከራዉ በፊት ስለሚሆን መነጠቅ የሚናገር የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የለም፡፡

ይህ በየትኛዉም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ ያልተመሰረተ አስተምህሮ ነዉ፡፡

በልማድ ላይ የተመሰረተ ነዉ፡፡ ይህ የሆነ ሰዉ ባነበበዉ መፅሀፍ ወይም ካርታ ላይ የተመሰረተ ነዉ፡፡

በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሰረተ አይደለም፡፡ ከመጽሐፍ ቅዱስ የመጣ አይደለም፡፡ ምንም መጽሐፍ ቅዱሳዊ መነሻ የለዉም፡፡

ይህንን ለተቀመጡ ሰዎች በገለፅኩ ቁጥር ይህንን አስተምህሮ የመረዳት ችግር እንደሌለባቸዉ አስተዉያለሁ፡፡

ፑልፒት ላይ ያሉ ሰዎች ናቸዉ ይህንን አስተምህሮ የማይጋፈጡት፡፡

ለምን እንደሆነ እነግራችኋለሁ፡፡ የቅድመ-መከራ መነጠቅ የታወቀ አስተምህሮ ነዉ፡፡

ታዋቂ መሆን ከፈለጋችሁ የምትሰብኩት ቅድመ-መከራ መነጠቅን ነዉ፡፡

መነጠቁ የሚመጣዉ ከመከራዉ በኋላ ነዉ ብላችሁ መስበክ ስትጀምሩ ግን ትገለላላችሁ፤

ትወገዛላችሁ፤ ከህብረት ትገፋላችሁ፤ ምክንያቱም

ይህን አስተምህሮ መቀየር አይፈልጉም፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት የዚህ አስተምህሮን እዉነታ ማንም እንዳይሰማ ለማድረግ አጀንዳ ይዘዉ የሚንቀሳቀሱ ሰዎች ስላሉ ነዉ፡፡ እዉነት ነዉ፡፡

እናም ይህን አስተምህሮ በጨለማ ዉስጥ የሚያቆዩበት መንገድ በፍርሃት እና በዛቻ ነዉ፡፡

እኔ ከመጋቢዎች ጋር አወራለሁ፡፡ በዚህ ዙርያ ላይ ያለዉን እዉነት አሳያችኋለሁ፡፡ ከእኔም ጋር ይስማማሉ፡፡

ነገር ግን ፑልፒታቸዉ ላይ ሄደዉ ይህንን አስተምህሮ አይሰብኩም፡፡ ምክንያቱም ሁሉም የመጋቢ ጓደኞቻቸዉ እንዳይነሱባቸዉ ነዉ፡፡

በዚህ ጉዳይ ላይ የንግግር መድረኮች አይኖሯቸዉም፡፡ ከዚያን በኋላ በእነዚህ ቤተክርስትያች ላይ…

የመስበክ እድል አይኖራቸዉም፡፡ ምክንያቱም ወደ እነሱ ስብስብ ዉስጥ ለመግባት የቅድመ-መከራ መነጠቅ አራማጅ መሆን አለባችሁ፡፡

የቅድመ-መከራ መነጠቅ ተከታይ ካልሆናችሁ በስብስቡ ዉስጥ አይደላችሁም፡፡

ብዙዉን ጊዜ አይቀበሉትም፤ ምክንያቱም በእነዚህ አመታት ሁሉ ስህተት ሲሰብኩ ስለኖሩ ደቼ መብላት አይፈልጉም፡፡

ይህንን ማመን አይፈልጉም፡፡ የመፅሀፍ ቅዱስ ኮሌጃቸዉ

ስህተት እንዳስተማራቸዉ ማመን አይፈልጉም፡፡ ስህተት እንደሰሩ ማመን አይፈልጉም፡፡

ሁሉም ሰዉ ይሳሳታል፡፡ ሁላችንም እናድጋለን፤ አዳዲስ ነገሮችንም እንማራለን፡፡

በአንድ ነገር ላይ ትክክል ካልሆናችሁ፤ መታረም አለባችሁ፡፡ መፅሀፍ ቅዱስ በገላቲያ ፡ እንዲህ ይላል፡

[::.] ሰዉን ወይስ እግዚአብሄርን አሁን እሺ አሰኛለሁን? ወይም ሰዉን ደስ ላሰኝ እፈልጋለሁን?

አሁን ሰዉን ደስ ባሰኝ የክርስቶስ ባርያ ባልሆንሁም፡፡

መጋቢ አንደርሰን፡ እነዚህ ሰባኪዎች ታዋቂዉን ነገር በመስበክ ሰዉን ማሰደሰት በእርግጥ…

ይበልጥ ጠቃሚ ነዉ ወይ ብለዉ መወሰን አለባቸዉ፡፡ የቅድመ-መከራ መነጠቅን በመስበክ ምክንያቱም

ያን ነዉ ሰዉ ሁሉ መስማት የሚፈልገዉ፡፡ ፊልሙን ስለወደዱት ቪድዮ ጌሙንም፣

የሰሌዳ ጌሙንም እናም ዲቪዲዉን አገኙ፡፡ ወይም መፅሀፍ ቅዱስ በእርግጥ ከሚናገረዉ ጋር አብሮ መሄድ እና

መነጠቁ ከመከራዉ በኋላ እንደሚመጣ መስበክ፡፡ ይሄ ክስተት እግዚአብሄር የሚናገረዉን ትተዉ ሰዎች ሰዉ የሚናገረዉን…

የሚናገሩበት አይነተኛ ምሳሌ ነዉ፡፡ ይህ መጽሐፍ ቅዱስን የመጨረሻዉ ባለስልጣን አለማድረግ አንዱ ምሳሌ ነዉ፡፡

እናም እንዲሁ በልማድ መመራት፤ በተማራችሁት ነገር መራመድ፤ ሰዎች በሚሉት መሄድ

መጽሐፍ ቅዱስ ከሚለዉ ጋር መሄድ ትቶ ከወጀቡ ጋር መወሰድ፡፡

መጋቢ ጂሜኔዝ፡ በቅድመ-መከራ መነጠቅ አምን ነበር፡፡ ከልጅነቴ ጀምሮ የተማርኩበትም እሱን ነዉ፡፡

የተነገራችሁን ነገር ብዙ ጊዜ አትጠይቁምና፡፡ ነገር ግን ወደ እዉነቱ እየተጋለጥኩ ስመጣ

የመፅሀፍ ቅዱስ ክፍሎችን እና በእርግጥ መጽሀፍ ቅዱስ ምን እንደሚያሰተምር ማየት ጀመርኩ፡፡

ከዚያም መግባባት ካለብኝ ተግባብቼ እንድሄድ ወይም ከወጀቡ ጋር እንዲሁ መሄድ ካለብኝ እንድሄድ…

የግል ምርጫ ማድረግ ነበረብኝ፡፡ ወይም ላመንኩት ነገር መቆም ካለብኝ…

እዉነት እንደሆነ ለማዉቀዉ ነገር መቆም አለብኝ አልኩ፡፡ በግል ህይወቴ ዉጊያ ደርሶብኛል..

በቅድመ-መከራ መነጠቅ ላይ ካለኝ አቋም የተነሳ ሰለ እኔ ክፉ የሚያወሩ ሰዎች አጋጥመዉኛል፡፡

ነገር ግን ይህንን እያዳመጣችሁ ወይም እየተመለካትቸሁ ከሆነ ከዚህ አንፃር ያለዉን እዉነት ማየት

ትጀምራላችሁ ከዚያም በእምነት ወጥታችሁ አቋም ትይዛላችሁ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

እና ምናልባትም ይህንን ኢ-መፅሀፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮ ነቅሎ ለመጣል ትረዱን ይሆናል፡፡

እርሱም የቅድመ-መከራ መነጠቅ ነዉ፡፡

ኬንት ሆቪንድ፡ ሌላዉ ያገኘሁት ቁልፍ ጥቅስ ኛ ተሰሎንቄ ፡- ነበር፡፡

(ኛ ተሰሎንቄ :-) ነገር ግን፤ ወንድሞች ሆይ፤ ስለ ጌታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ መምጣትና

[ስለዚህ እዚህ ጋር ስለ ጌታ ኢየሱስ መምጣት እየተናገረ ነዉ] ወደ እርሱ [ሰለመነጠቅ ይመለከታል]

ስለ መሰብሰባችን፤ በመንፈስ ወይም በቃል ወይም ከእኛ እንደመጣ በመልእክት፡፡

የጌታ ቀን [አሁንም መነጠቁን ይመለከታል] ደርሶአል ብላችሁ፤ ከአእምሮአችሁ ቆሎ እንዳትናወጡ እንዳትደነግጡም እንለምናችኋለን፡፡

ማንም በማናቸዉም መንገድ አያስታችሁ፤ ክህደቱ አስቀድሞ ሳይመጣና የዓመፅ ሰዉ እርሱም የጥፋት ልጅ ሳይገለጥ፤ አይደርስምና፡፡

መጋቢ ጂሜኔዝ፡ “ልብ በሉ ጊዜው አልደረሰም፤ በቀጣዩ ጊዜ

የሚከሰት አይደለም፡፡” ይላል፡፡ “ማንም በማናቸውም መንገድ አያስታቹ

(ሁላችንም ስለምንሰበስብበት ቀን ይናገራል፡፡) ክህደቱ አስቀድሞ ሳይመጣና

የአመጽ ሰው እርሱም የጥፋት ልጅ ሳይገለጥ አይደርስምና፡፡” ስለዚህም

ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አብረን የምንሰበሰብበት ቀን

ክህደቱ አስቀድሞ ሳይመጣ እና የአመፅ ሰው ሳይገለጥ እንደማይደርስ የእግዚአብሄር ቃል ያረጋግጥልናል፡፡ አንድ

ሊቀር የማይችል ሃቅ የክርስቶስ ተቃዋሚው እንደሚመጣ ነው፡፡

መጋቢ አንደርሰን፡ ስለዚህም መጽሃፍ ቅዱስ የክርስቶስ ቀን አለመድረሱን ግልጽ በሆነ መንገድ ይነግረናል፡፡

ማንም ቢሆን ክርስቶስ መጥቷል ብሎ ከነገራችሁ ያ ሰው

እያታለላችሁ ነው፡፡ እንዲሁም ውሸታም ነው፡፡ በመንፈስ ወይም

በቃል ወይም ከእኛ እንደሚመጣ በመልዕክት፣ የጌታ ቀን ደርሶአል በሚል መልዕክት

ማንም በማናቸውም መንገድ አያታልላችሁ፡፡ ይህ ቀን መጀመሪያ

መሆን ያለበት ነገር ለምሳሌ ኤክስ፣ ዋይ፣ ዜድ ሳይፈፀም አይመጣም፡፡ መነጠቅ በቀላሉ በማንኛውም ጊዜ ሊሆን አይችልም፡፡ መከራው

መጀመሪያ መፈጸም አለበት፤ አስቀድሞ የክርስቶስ ተቃዋሚው ስልጣን መያዝ አለበት፤ ፀሃይና ጨረቃ

ታላቁና አስፈሪው የጌታ ቀን ከመምጣቱ በፊት ይጨልማሉ፡፡ መጽሃፍ ቅዱስ

እውነተኛና ግልፅ ነው፡፡ ያ ቀን ክህደት አስቀድሞ ሳይመጣና የዓመፅ ሰው

ሳይገለጥ አይደርስምና፡፡ የክርስቶስ ተቃዋሚ ይገለጣል፣ እኔ እግዚአብሄር ነኝ ብሎ

አዋጅ እየነገረ በእግዚአብሄር ቤተ መቅደስ ይቀመጣል፡፡ መነጠቅ ከመድረሱ በፊት የክርስቶስ ተቃዋሚ ስልጣን ይይዛል፡፡

ነገርግን በሉቃስ ላይ ብትመለከቱ ከማቴዎስ ቀድሞ የሚመጣ ክፍል ነው፡፡

ምክንያቱም ማቴዎስ ከሉቃስ ጋር ተጓዳኝ የሆነ ክፍል ነው፡፡ ስለዚህ በሉቃስ

ላይ ስለዚህ አስተምህሮ ክርስቶስ ለደቀመዛሙርቱ ያስተማረውን

የመጀመሪያ ክፍል እናነባለን፡፡ መጽሃፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፡

[::.] በኖህ[ኖህ] ዘመን እንደሆነ እንዲሁ

በሰው ልጅ ዘመን (ኢየሱስ ክርስቶስ) ደግሞ ይሆናል፡፡

መጋቢ አንደርሰን፡ ብዙ ሰዎች ይህን ክፍል ይወስዱና ሰዎች

በኖህ ዘመን እንደነበረው ክፋት አድራጊ ይሆናሉ ይላሉ፡፡ እንዲሁም

በሎጥ ዘመን እንደ ሆነ በሰው ልጅ ዘመን መምጣት ላይ ደግሞ እንዲሁ ይሆናል፡፡

እናም ብዙ ሰዎች ይህን ክፍል በተለመከት እንዲህ ይላሉ “በሰዶም እና ገሞራ ዘመን እንደነበረው ክፋት ይሆናል”፤

እንዲሁም በማህበረሰባች ውስጥ እየተደረጉ ያሉት ነገሮች አውጥተው በማሳየት

በሰዶም እና ገሞራ ያለው ገፅታ ነፀብራቅ እንደሆነና በዚያን ዘመን እንደነበረው ክፋት እና አመፅ ነው ብለው ይናገራሉ፡፡

በሰዶም እና ገሞ ወይም በኖህ ዘመን እንደነበረው ክፋት እና አመፅ ይሆናል ብለው ይናገራሉ፡፡

ነገር ግን በእርግጥ ኢየሱስ እየተናገረው ያለ ሃሳብ ይህ አይደለም፡፡

መጋቢ ጂሜኔዝ፡ በቁጥር ላይ እንዲህ ይላል፡

(ሉቃስ :-) እንዲሁም በሎጥ ዘመን እንደ ሆነ ይበሉ ይጠጡም

ይገዙም ይሸጡም ይተክሉም ቤትም ይሠሩ ነበር፤ ሎጥ ከሰዶም በወጣበት ቀን ግን

ከሰማይ እሳትና ዲን ዘነበ ሁሉንም አጠፋ፡፡

መጋቢ ጂሜኔዝ፡ ከዚህ ክፍል የምንማረው ሎጥ ከሰዶም መውጣቱ

የመነጠቅ ምሳሌ ነው፡፡ ወደ ሰዶም የሄዱት ሁለቱ መላዕክት

ምድርንና የእግዚአብሄር ቁጣ በምድር ላይ ከመንደዱ በፊት አማኞችን ሰብስበው ከምድር ማውጣትን ይወክላሉ፡፡

የራዕይ መፅሃፍ ይህንኑ ተመሳሳይ ሃሳብ ያስተምራል፡፡ የእግዚአብሄር ቃል

በዮሃንስ ራእይ ላይ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ መልአክቱን በመላክ አማኞችን ሰብስቦ…

ከምድር ላይ እንደሚወስዳቸው ይናገራል፡፡ የራዕይ መፅሃፍ በቀጥታ እንደሚነግረን ከተነጠቅን አጋማሽ ሰእት ካለፈ

በኋላ እግዚአብሄር ቁጣውን ማውረድ ይጀምራል፡፡

መጋቢ አንደርሰን፡ ይህ “ኋላ መቅረት” ፅንሰ-ሃሳብ ሁሉም ሰው ጠፍቶ ሌሎቹ የቀሩት ህዝቦች…

“ሁሉም የት ነው ያሉት?” አይሉም፤ ሰዎች የሚናገሩት ይህን አይደለም ምክንያቱም

በምንነጠቅብት በዚያው ቀን እግዚአብሄር…

ፍርዱን እና ቁጣውን ያወርዳል፡፡ እሳትና ዲን በዚህች ምድር ላይ ያወርዳል፡፡

ሰዎች የሆነ ነገር ሊከሰት እንደሆነ ይረዳሉ ስለዚህም ከለላን ለማግኘት ይሮጣሉ፡፡

ከሚወርደው ቁጣ፣ ከእሳትና ዲን የተነሳ ሰዎች ተራሮች በላያቸው ላይ ወድቀው እንዲሸሽጓቸው ይለምናሉ፡፡

እኛ አማኞች በምንነጠቅበት በዚያን ቀን

እግዚአብሄር የቁጣውን ፅዋ ያፈሳል፡፡ ለዚህም ነው

ፀሃይ እና ጨረቃ ሲጨልሙ መፅሃፍ ቅዱስ ታላቁ የቁጣው ቀን እንደደረሰ እና

በእርሱ ፊት ማንስ መቆም ይቻላል? ብሎ የሚናገረው፡፡ ምክንያቱም በዚያኑ ቀን፤ ከአጋማሽ ሰአት በኋላ እግዚአብሄር

እሳትና ዲን ማውረድ ይጀምራል፡፡ ስለዚህ በራዕይ ምዕራፍ ስድስት ላይ ፀሃይና ጨረቃ ይጨልማሉ፡፡ ምዕራፍ ሰባት ላይ

እጅግ ብዙ አማኞች በሰማይ ላይ ይታያሉ፡፡ ምዕራፍ ስምንት፣ ቁጣውን

ማውረድ ይጀምራል፡፡ ይህም መጽሃፍ ቅዱስ በማቴዎስ ላይ እንደሚያስተምር ነው፡፡ ፀሃይ እና ጨረቃ ይጨልማሉ በመቀጠልም

መነጠቅ ይሆናል፡፡ ልክ እንደዚህ ግልፅ ነው፡፡ የቅድመ-መከራ መነጠቅ ከሚያምኑ ሰዎች ጋር ስነጋገር…

አብዛኛውን ጊዜ ከሁለት አንዱን ይነግሩኛል፡፡

መነጠቅ በራዕይ ላይ ጭራሹን አልተገለፀም የሚሉኝ አሉ ነገር ግን ይህ በጣም እንግዳ ነገር ነው፡፡

የራዕይ መፅሃፍ የመጨረሻውን ዘመን ክስተቶችን በዝርዝር ስለሚያሳይ ይህ እንግዳ የሆነ ነገር ነው፡፡

ኢየሱስ ክርስቶስ በደመና ሲመጣና

በሁሉም ዘመን ነበሩ አማኞች በደመና ሊቀበሉት ሲነጠቁ …

ይህ በጣም ወሳኝ ክስተት ነው፡፡ ይህን ሁሉ በራዕይ መፅሃፍ ላይ ጭራሽኑ አልተገለጸም ብሎ መናገር

በራዕይ መፅሃፍ ላይ በሙሉ አልተጻፈም ማለት ነው፡፡ ይህ ደግሞ ፈፅሞ የማታሰብ ነው ምክንያቱም

ንጥቀት በራዕይ መፅሃፍ ላይ ጭራሹን አይገኝም ማለት ትልቅ ስህተት ነው፤ ብዙ ሰዎች

ብዙ ሰዎች መነጠቅ ከመከራው በፊት ነው የሚል ሐሳብ ለመደገፍ የሚያስችላቸውን

ቃል ለማግኘት ሞክረዋል፡፡ እናም በተደጋጋሚ የምሰማው ይሄን ነው፡

ደግሞ ደጋግሞ - ራዕይ : የሚለው፡

(ራዕይ :) ከዛም በኋላ አየሁ እነሆም በሰማይ የተከፈተ ደጅ

እንደ መለከትም ሆኖ ሲናገረኝ የሰማሁት ፊተኛው ድምፅ፡- ወደዚህ

ውጣና ከዚህ በኋላ ሊሆን የሚያስፈልገውን አሳይሃለው አለ፡፡

መጋቢ አንደርሰን፡ ስለዚህ ይህ ድምፅ እንደ መለከት ነው፡፡ በዚህ ጥቅስ ውስጥ

ለዮሃንስ “ውጣ እና (ነጠላ፣ አንድ ግለሰብ)

መሆን ያለበትን ላሳይህ“ ብሎ የሚናገር መለከት አይደለም፡፡ ስለዚህም እንዲህ ይላሉ “አየህ ይህ ነው መነጠቅ“

የአንድ ሰው ተነጠቀ ይላሉ፡፡ ይሄ የማይመስል ነገር

የሆነበት ምክንያት ቁጥር ላይ ያለውን እንኳን አያነቡም

(ራዕይ :) ወዲያው በመንፈስ ነበርኩ እነሆም ዙፋን

በሰማይ ቆማአል በዙፋኑም ላይ ተቀማጭ ነበረ፤

መጋቢ አንደርሰን፡ መነጠቅ መንፈስ ወደ ሰማይ መወሰድ ማለት አይደለም፤ መነጠቅ የትንሳኤን አካል ለብሶ መነሳት ነው፡፡

በአካል አየር ላይ ጌታን ለመቀበል መነጠቅ ነው፡፡ እንዲያው

መንፈስ ወደላይ መነሳት ማለት አይደለም፡፡ መፅሀፍ ቅዱስ መነጠቅ ቀጥተኛ እንደሆነ ግልፅ አድርጎታል፡፡

መጀመሪያ በክርስቶስ አምነው ያነቀላፉት ሰዎች አስቀድመው የማይበሰብሱ ሆነው ይነሳሉ እኛም በህይወት ያለነው

እና የቀረነው አማኞች እንለወጣለን ጌታን በአካል ለማግኘት አብረናቸው እንነጠቃለን፡፡ ስለዚህ የዮሃንስ ወደላይ በመንፈስ መውጣት

በትክክል መነጠቅ ማለት አይደለም፡፡ ይህ መነጠቅ ባለችሁ ካሰባችሁ

በእርግጥ ትክክለኛ ትርጉሙን አላገኛችሁትም፡፡ በጣም የሚገርመው ነገር

በቅድመ- መከራ የሚያምኑ ሰዎች የመፅሃፍ ቅዱስ ጥሬ ፍቺውን እንደሚተረጉሙ ያውጃሉ

ሆኖም በራዕይ ውስጥ ስለ መነጠቅ የሚናገረውን ክፍል አሳዩኝ ስትሏቸው ወደ ራዕይ

: አንድ ወደሰማይ ስለተወሰደ ሰው ይነግሯቹሃል፡፡ ቁጥር አያነቡላችሁም፡

“ወዲያው በመንፈስ ነበርኩ እነሆም ዙፋን በሰማይ ቆማአል በዙፋኑም ላይ ተቀማጭ ነበረ፤“ ዮሃንስ

በስጋው ወደሰማይ አልሄደም፤ አካሉ ፍጥሞ በምትባል ደሴት ነበር፡፡ በክርስቶስ የሞቱ

አስቀድመው ይነሳሉ ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረው

ጌታን በአየር ለመቀበል በደመና እንነጠቃለን፡፡ ይህ እንደ መንፈስ አይነት ክስተት አይደለም፤ ይህ

አካላዊ ክስተት ነው፡፡ ይህ መነጠቅ ነው የምንለው ነው፡፡

አነዚህ ሰዎች ራዕይ : መነጠቅ ነው ማለት አለባቸው፡፡

ምክንያቱም በራዕይ መፅሃፍ ውስጥ ከመከራ በፊት ስለመነጠቅ ያወራል ብለው የሚቀበሉት ብቸኛ ሃሳብ ስለሆነ ነው፡፡

ይህ በቂ አይደለም፤ በእኔ ግምት ሌላ ነገር መፈለግ ይኖርባቸዋል፡፡ የቅድመ-መከራ መነጠቅ አስተምህሮ

በመማር ነው ያደግኩት፡፡ ካደግኩ በኋላ ይህ አስተምህሮ

በራዕይ መፅሃፍ ላይ እንዳልተገለፀ ተረዳሁ፡፡ ሁሉጊዜ ይህ አስተምህሮ የሆነ

ችግር እንዳለበት አስብ ነበር… ስለ መጨረሻው ዘመን የሚናገር

መጽሃፍ አላችሁ፣ እና የዮሃንስ ራዕይ አልገለጸውም?

ይህ ትርጉም አይሰጥም፡፡ ስለመነጠቅ እንደልጅ ሁሌም አስብ የነበረው

በህይወታችሁ ትሄዱበት ከነበረበት ስፍራ በድንገት መሰወር ነበር፡፡ ነገር ግን ከዚህም ያለፈ ነው

ምክንያቱም ቃሉ ሲናገር ሁሉም አይን ያየዋል፡፡ ፀሃይ

እና ጨረቃ ይጨልማሉ፡፡ ቃሉ በሉቃስ ላይ እናንተ ይህ ሁሉ መሆኑን ስታዩ

መዳናችሁ መቅረቡን ተመልከቱ ይለናል፡፡

ፀሃይ ስትጨልም፣ ጨረቃ ስትጨልም፣ ከዋክብት ሲወድቁ

ምን ሊመስል እንደሚችል እንደሚችል አስቡ፤ ወደላይ እንመለከትና ጊዜው መድረሱን እና መነጠቃችንን እንመለከታለን፡፡

ልክ እንደ ሆሊውድ መግቢያ፣ ከማንኛውም ቦታ ታዋቂ

ሰው ሲገባ የካሜራዎች ፍላሽ ብርሃን፣ድምፅ

ጭሽ እና ሌላም ነገር ይታያል፡፡ የሰውን ትኩረት ለመሳብ“ይሀው ተመልከተኝ“ ይፈልጋሉ፡፡

የዮሃንስ ራዕይ ምዕራፍ ወይም ማቴዎስ ካነበባችሁ ሁለቱም ክፍሎች

ፀሃይ እና ጨረቃ እንደሚጨልም ይገልፃሉ፡፡ ስትመለከቱት በጣም አስደናቂ ነው፤ ፀሃይ

እና ጨረቃ መጨለም በምድር ላይ ያሉትን የሁሉንም ሰዎች ትኩረት የሚስብ ይሆናል፡፡

መሬት መንቀጥቀጥም ይሆናል፡፡ ማየት የማይችሉ ቢሆኑ እንኳን

አሁንም ይህ ትኩረትዎን ይስባል፡፡

መጋቢ አንደርሰን: ሙሉ ጨለማ በሚሆንበት በዚያን ጊዜ

ኢየሱስ ክርስቶስ በደመና፣ ሙሉ ሰማይ ላይ በብርሃን ይመጣል፡፡ ቃሉ እንደሚናገረው

መብረቅ ሰማይን ከዳር እስከዳር እንደሚያበራ እንዲሁ ይታያል፡፡ በዚያን ጊዜ ወደላይ ተመልክተን

ኢየሱስ ክርስቶስ በደመና መምጣቱን እንመለከታለን፡፡ በዚያን ቅፅበት እርሱን

ለመቀበል መነጠቃችንን እንረዳለን፡፡ ያንን ቀን ላይ በህይወት እንደምቆይ ተስፋ አደርጋሁ፡፡

በህይወት ዘመናችን ይሆን እንደሆነ ባላውቅም በህይወት እንዳለሁ እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

ስደትን እና መከራን እቋቋማለሁ፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ በደመና በሚመጣበት ቀን

ህያው ሆኖ መገኘት እንዴት ደስ ይላል

እንድናምን ካደረገን ነገር በላይ የላቀ ነው፡፡

ኬንት ሆቪንድ፡ ጌታ ሲመጣ መጀመሪያ ሚስጥር ሆኖ ቆይቶ

ሰዎች በኋላ ምን እንደተከሰተ የሚደርሱበት ነገር ነው የሚል ሃሳብ ትክክል አይደለም፡፡

ጌታ ኢየሱስ በዚህ አስደናቂ ክስተት የሁሉንም ትኩረት ይስባል፡፡

መጋቢ አንደርስን፡ በጣም ትክክል ነህ፤ ራዕይ ላይ እንዲህ ይላል፡“እነሆ

ከደመና ጋር ይመጣል ዓይንም ሁሉ የወጉትም ያዩታል” ልብ በሉ “ይመጣል” የሚለው ባሁን ጊዜ ውስጥ ያለ ነው፡፡

ይህም ቀጣይ በሚመጣበት ወቅት ከደመና ጋር እንደሚመጣና ሁሉም አይን እንደሚያየው ነው፡፡

ይሄ በጣም ግልፅ ነው፡፡ ላልዳኑት በጣም አስፈሪ ነገር ነው፡፡ መፅሃፍ ቅዱስ

እንደሚናገር ሲመለከቱት ዋይ ዋይ ይላሉ

ያለቅሳሉ እስከሞት ድረስ ይፈራሉ፡፡ ነገር ግን

እኛ አማኞች ግን የእርሱን መገለጥ ስንመለከት እጅግ ደስ ይለናል፡፡ ሃሴትን እናደርጋለን፡፡

ይህ መሆኑን ማወቃችን እጅግ አስደናቂ ስሜት ይፈጥርልናል፡፡

መጋቢ ጂሜኔዝ፡ እኔ በበኩሌ ይህ ፊልም ስኬታማ እንዲሆን እፈልጋለሁ፡፡ ይህ ፊልም

ሰዎች እውነትን እንዲመለከቱ እግዚአብሄር አይኖቻቸውን ለመክፈት የሚጠቀምበት እንዲሆን እወዳለሁ፡፡

ወደቃሉ መመለስ እንዳለብን አስባለሁ፡፡ ትዝ ይለኛል ታዳጊ እያለሁ እና

እያደግኩም እያለ የዮሃንስ ራዕይ መፅሃፍን ማንበብ አልወድም ነበር ምክንያቱም

ልረዳው አልችልም ነበር ወይም በማነብበት ጊዜ ሁሉ እንዲህ ብዬ እጠይቃለሁ

“በእርግጥ ይህ እየተናገረ ነው? በእርግጥ ይህን ለማለት ፈልጎ ነው?” ስለመነጠቅ ትክክለኛ

እውነታውን መማር መጀምር ስችል ጥቅሶቹ ተገለጡልኝ፡፡

አሁን የራዕይ መፅሃፍን ማንበብ እወዳለሁ፡፡ አብዝቼ ባነበብኩት ቁጥር የበለጠ ትርጉም ይሰጠኛል፡፡ እኔ እንደማስበው

የክርስትና እንቅስቃሴን፣ ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴን

የመጥመቃውያንን እንቅስቃሴ መድረስ ከቻልን እና በዚህ ጉዳይ አይኖቻቸውን መክፈት ከቻልን

ምናልባት የእግዚአብሄር ቃል መውደድ እና በቃሉ መነቃቃት፣

የእግዚአብሔር ቃል ጥናት ተሃድሶ በሀገራች ባሉ መድረኮቻችን ማምጣት እና

የእግዚአብሄርን ታላቅ ስራ ማየት እንችላለን፡፡

መጋቢ አንደርሰን፡ ይህንን ፊልም ያዘጋጀንበት ምክንያት የአስተምህሮ ስሮችን ለመከፋፈል አይደለም ወይም ደግሞ

አንድ ሰው በመፅሃፍ ቅዱስ ትንቢቶች ላይ ከእኛ በጥቂቱ ለየት ያለውን አመለካከቱን ለማረም አይደለም፡፡

ይህ አላማችንም አይደለም፡፡ እነዚህ ድርጊቶች እውነተኛ የሚፈፀሙ ናቸው፡፡ መፅሃፍ ቅዱሰ

አለም ሁሉ አንድ መንግስት እንደሚሆን ይነግረናል፡፡ አንድ የአለም ሃይማኖት ይሆናል፡፡

አንድ የአለም መገበያያ ይሆናል፡፡ ይህ ሰዎች ውድቅ የሚችሉት ፍልስፍና አይደለም፤ እነዚህ ድርጊቶች

በእርግጥ የሚፈፀሙ ናቸው፡፡ በርካታ ህዝቦች ይገደላሉ፡፡

ረሃብ ይሆናል፡፡ በሽታ፣ ወረርሽን ይመጣል፡፡ ስቃይ እና መከራ ይሆናል፡፡

አለም አይታ የማታውቀው ታላቅ መከራ ይሆንባታል እንደዚህም ሆኖ ክርስቲያኖች

ምንም አልተዘጋጁም ምክንያቱም በቅድመ መከራ መነጠቅ ተረት ስለሚያምኑ

መነጠቅ መጽሃፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮ ነው፤ ነገር ግን

ከመከራው በኋላ የሚሆን ነው፡፡

መጋቢ ጂሜኔዝ፡ “መጋቢ ጂሜኔዝ ይህ ለምን አሳሳቢ ሆነ?” ትሉኝ ይሆናል፡- አሳሳቢ የሆነበት ምክንያት

የቅድመ-መከራ መነጠቅ አስተምህሮ በምናደረገው ድርጊት ላይ

ትኩረት የማያደርግ እንደሆነ ስለማምን ነው፤ ምክንያቱም በዚህ አስተምህሮ መሰረት፡- እንደ አረጋዊ በሰላም ባንቀላፋ፣

ወይም በሕይወት እየኖርኩ የእረፍት ጊዜዬን እየወሰድኩ፣ ኬ እያወጣሁ፣

ጥር የሚባል ኑሮ እየኖርኩ ሳለ መጥፎ ነገር ከመከሰቱ በፊት አንድ ቀን እነጠቃለሁ፤ ብለን እንድናሰብ ያደርገናል፡፡

ይህ ትምህርት በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ሰዎች ተሰጥቷል፡፡ እንደኔ እምነት

ይህ በጣም ሰነፍ እና አሁን ባለን የክርስትና ገፅታ ደስተኞች እንድንሆን ያደርገናል፡፡ ወንጌልን መመስከር አለብን

መውጣት አለብን፡፡ ህዝቡን ማስተማርና “ተመልከቱ መከራ እና ስደቱ እየመጣ ነው“ ብለን መናገር አለብን፡፡

ጥቂት የመዝናኛ ጊዜ አሳልፉ እንዲሁም ማድረግ ያለባችሁን ነገሮች አድርጉ ነገር ግን ከዚህ በበለጠ

ውስጣዊ ሰውነታችሁን ማጠንከር ይኖርባቹሃል፡፡ የእግዚብሄርን ቃል መማር መጀመር አለባችሁ፤

ከእግዚአብሄር ጋር መጓዝ እና እርሱን ማወቅ መጀመር አለባችሁ፤ የእግዚብሄርን ቃል ጥናት መጀመር አለባችሁ፤

ምክንያቱም መፅሃፍ ቅዱሳችሁን የሚቀሟችሁበት ጊዜ ሊመጣ ይችላል፡፡

ዛሬ አብረን እንድንሰበሰብ፣ መፅሃፍ ቅዱሳችንን እንድንከፍት፣ ቃሉን እንድንሰብክ ነጻነት ተሰጥቶል፡፡ ነገር ግን

አንድ ቀን ስብስባችን የማይፈቀድበት፣ መፅሃፍ ቅዱስ የሚከለከልበት

አሁን የምናደርገው ሁሉ የማይፈቀድበት ጊዜ ሊመጣ ይችላል፡፡ ለእግዚአብሄር የሚታዘዝ

ልብ ካለን ሰዎችን በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል እንደርሳለን፡፡

መጋቢ አንደርሰን፡ እነዚህ ነገሮችን የሰበኳችሁ

እንዳትሰናከሉ ነው፡፡ መከራው ሲመጣ፣ የአውሬውን ምልክት

በቀኝ እጃችሁ ወይም ግንባራችሁ እንድትቀበሉ ስትጠየቁ ይህንን ስብከት ታስታውሳላችሁ፡፡

ምናልባት በእናንተ የህይወት ዘመን ሊፈፀም ወይም ላይፈፀም ይችላል፡፡ ነገር ግን ከተፈፀመ ይህንን ስብከት ታስታውሳላችሁ፡፡

ለዚህ ነው ኢየሱስ የተናገረው እና እኔም የምናገረው፡፡ “እንድንፈራ ነው?” አይደለም!

መከራ እንደሚደርስብን ቃሉ ይነግረናል፡፡ ስለዚህ አንዘን ይልቁንም ጌታ የነገረን

በዚህ ምድር ሳላችሁ መከራ ይደርስባችኋል ነገር ግን አይዞአችሁ ደስ ይበላችሁ “እኔ አለም አሸንፊያለሁ” ብሎ ነው፡፡

ተፅናኑ ፣ ተስፋ አትቁረጡ፣ ከስብከቱ ጥላችሁ አትውጡ “ኦ ሰውዬ የምርህን ነው?

መታረድ? መታሰር? ረሃብ? በሽታ? የምርህን ነው?” አይደለም ደስ ይበላችሁ

እርሱ አለምን አሸንፏል፡፡ ምናልባት በእኛ ዘመን ይፈፀማል ወይም አይፈፀምም ሆኖም

በማንኛውም መንገድ ቢሆን አግዚአብሄር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል? ኢየሱስ ክርስቶስን አመስግኑት ራሳችንን ዝቅ እናድርገን

እንጸልይ፡፡ አባት ሆይ በቃልህ ውስጥ ስላለው ግልፅ እውነት እናመሰግንሃለን፡፡

ይመራን ዘንድ ቅዱሱን መንፈስህን ስለሰጠኸን እናመሰግንሃለን፡፡ ይህን መረዳት

በዙሪያዬ ካሉ ከእነዚህ ሰዎች

እና ከስኮፊልድ ላገኘው አልችልም ነበር፡፡ ነገር ግን በዚያ ክፍል ውስጥ ስላለው ቅዱስ መንፈስህ ተመስገን፡፡

ከብዙ አመት በፊት በአእምሮዬ ውስጥ የሚመላለሱ እና የሚቀጣጠሉ ሶስት ቃላት አሉ፡፡

ከማቴዎስ ላይ እንደ አመት ልጅ በአእምሮዬ ይቀጣጠሉ የነበሩት እነዚህ ሶስት ቃላት ናቸው፡ ከታላቁ መከራም በኋላ

በዚህ ምሽት እነዚህ ቃሎች በሁሉም ሰዎች ልብና አእምሮ ውስጥ ሰርፀው እንዲገቡ እፀልያለው፡፡

እንወድሃለን፣ እናመሰግንሃለን በኢየሱስ ስም አሜን፡፡ ከመሄዳች በፊት

አብረን አንድ አጭር መዝሙር እንዘምር፡፡

መዝሙር: ከነፍሴ ጋር ሰላም ነው

መጋቢ ጂሜኔዝ፡ ይህ በጣም የምወደው መዝሙር ነው እናም የምወደውን ክፍል አሁን

አብረን እንዘምረዋለን፡፡ አብዛኛውን ጊዜ መዝሙሮችን ስትዘምሩ ቀጥታ ወደ መዘመር ነው የምትሄዱት

ስለ ቃሎቹ እና እየተናገረው ስላለው ነገር አታስቡም፡፡ የመዝሙሩን ሶስተኛ ስንኝ ተመልከቱ፤

እንደዚህ ይላል “ሃጢያቴ…ኦ የዚህ ሀሳብ ክቡር ደስታው” እንዲህ ትላላችሁ

“ስለ ሃጢያት ማሰብ ምን ያስደስታል?” ነገር ግን ምን እያለ እንደሆነ ተመልከቱ፤

“በመስቀል ላይ ተንጠልጥሏል፤ ከዚህን በኋላ አልሸከመውም፡፡ ኦ ነፍሴ ጌታን አክብሪ፤ ጌታን አክብሪ፡፡”

እስቲ ስትዘምሩ ስለነዚህ ቃላት አስቡ፡፡ ዘምሩት፣ ከዚያም

ለዚህ ስብከት ዝግጁ እንሆናለን፡፡

ሃጢያቴ…ኦ የዚህ ሀሳብ ክቡር ደስታው! ሃጢያቴ በከፊል ሳይሆን በሙሉ፤

በመስቀል ላይ ተንጠልጥሏል ከዚህ በኋላ አልሸከመውም ነፍሴ ጌታን አክብሪ ጌታን አክብሪ!

ከነፍሴ ጋር ሰላም ነው ሰላም ነው ከነፍሴ ጋር ሰላም ነው፡፡

እምነቴ ሲታይ ጌታ ቀኑን ያስቸኩለዋል

ደመናት እንደ ብራና ይጠቀለላል፤ መለከት ያስተጋባል

ጌታም ይወርዳል፤ ቢሆንም እንኳ ከነፍሴ ጋር ሰላም ነው፡፡

ከነፍሴ ጋር ሰላም ነው ሰላም ነው ከነፍሴ ጋር ሰላም ነው፡፡

በደህንነት ላይ መፅሃፍ ቅዱስ ግልፅ ነው፡፡ ጥሩዎች ስለሆናችሁ አይደለም፡፡ ብዙ ሰዎች

ራሳቸውን መልካም እንደሆኑ አድርገው ያስባሉ በዚህም መንግስተ ሰማይ እንደሚገቡ ያስባሉ፡፡

ነገር ግን መጽሃፍ ቅዱሰ እንዲህ ይላል “ሁሉም ሃጢአትን ሰርተዋልና የእግዚአብሄርም ክብር ጎድሎአቸዋል፡፡”

መጽሃፍ ቅዱሰ እንዲህ ይላል “እንዲህ ተብሎ እንደተፃፈ ፃድቅ የለም አንድ ስንኳ” እኔ ጻድቅ አይደለሁም፡፡

እናንተ ጻድቃን አይደላችሁም፡፡ መልካም ስራችን መንግሰተ ሰማያት

የሚያስገባን ቢሆን ኖሮ ማንም አይገባም ነበር፡፡

.ሃጢአተኛ መሆናችሁን እመኑ

ደግሞም የእግዚአብሄር ቃል ራዕይ ፡ ላይ እንዲህ ይላል፡

(ራዕይ ፡ ) “ነገር ግን ፈሪዎች፣ የማያምኑ፣ ርኩሶች፣ ነፍሰ ገዳዮች፣ አመንዝሮች፣

አስማተኞች፣ ጣኦት አምላኪዎች፣ ውሸተኞች ሁሉ ዕጣ ፈንታቸው

በዲንና በእሳት ባሕር ውስጥ መጣል ይሆናልና፡፤ ይህም ሁለተኛው ሞት ነው፡፡”

እኔ ከዚህ በፊት ዋሽቻለሁ፤ ሁሉም ሰው ከዚህ በፊት ዋሽቷል፡፡ ሁላችንም ሃጢአትን ሰርተናል፡፡

ከውሸት የበለጡ ክፋቶችን አድርገናል፡፡ እንጋፈጠው ሁላችንም ገሃነም ነበር የሚገባን፡፡

.የሃጢአት ቅጣት ምን እንደሆነ እንረዳ

ነገር ግን የእግዚአብሄር ቃል እንዲህ ይላል፡

(በሮሜ ፡) እንዲህ ይላል፡ “ነገር ግን ገና ኀጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ

ስለ እኛ ሞተ፤ ይህም እግዚአብሄር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያሳያል፡፡”

ስለዚህ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለወደደን ወዲዚህ አለም መጣ፡፡ የእግዚአብሄር ቃል ሲናገር በስጋ የተገለጠ አምላክ ነበር፡፡

እግዚአብሔር የሰውን አምሳል ወሰደ፡፡ ሃጢአት የሌለበትን ህይወት ኖረ፤ ምንም ዓይነት

ሃጢአት አልሰራም፡፡ እርግጥ ነው መቱት፣ ተፉበት፣ በመስቀል ላይ ሰቀሉት፡፡

ቃሉ እንደሚናገር በመስቀል ላይ በነበረበት ጊዜ የሁላችንም ኃጢአት በስጋው ተሸከመ፡፡

ስለዚህ ማንኛውም እኔና እናንተ የሰራነው ሃጢአት በክርስቶስ ላይ ሆኖ ለእኛ ተሰቀለ፤ ስለእኛ ሃጢአት ተቀጣ፡፡ እርግጥ ነው በመስቀል ላይ ሲሞት

አካሉን ወሰዱትና በመቃብር ውስጥ አኖሩት፡፡ ነፍሱ ለ ቀን እና

ለ ሌሊት በሲኦል አደረ፡፡ ከሶስት ቀን በኋላም ከሞት ተነሳ፡፡

ለደቀመዛሙርቱ በምስማር የተቸነከሩትን የእጆቹን ምልክት አሳያቸው፡፡ ኢየሱስ ለሁሉም የሰው ዘር

እንደሞተ ቅዱስ ቃሉ ይነግረናል፤ ይህም ለእኛ ሃጢአት ብቻ ሳይሆን ለሰው ልጆች ሁሉ ሃጢአት እንደሞተ ይናገራል፡፡

ነገር ግን ለመዳን ማድረግ ያለብን ነገር አለ፡፡ ይህን ጥያቄ መጽሃፍ ቅዱስ ላይ አለ፡-

የሐዋ.ስራ ፡ “እናንት ሰዎች፤ እድን ዘንድ ምን ላድርግ?” አላቸው፡፡ እነርሱም፣

(የሐዋ.ስራ ፡-) “በጌታ በኢየሱስ እመን፤ አንተም ቤተ ሰቦችህም ትድናላችሁ” አሉት፡፡

ይኸው ነው፡፡ “ቤተ ክርስቲያንን ተቀላቀልና ትድናለህ፣ ተጠመቅና

ትድናለህ፣ ጥሩ ሕይወት ኑርና ትድናለህ፣ ሁሉንም ሃጢአትህን

ተናዘዝና ትድናለህ ” አላለውም፡፡ ያለው “እመን” ነው፡፡

.ኢየሱስ ላንተ እንደሞተ፣ እንደተቀበረ፣ ከሞትም እንደተነሳ እመን፡፡

መጽሃፍ ቅዱስ ውስጥ ካሉ በጣም ከሚታወቁ ጥቅሶች ውስጥ እንዲያውም የበለጠ፣ ሁሉም ሰዎች የሰሙት፣ በብዙ እቃዎች ላይ

ተፅፎ የምናገኘው ጥቅስ የዮሃንስ ወንጌል ፡ ነው፡፡

[::.] በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ

እንዳይጠፋ እግዚአብሄር አንድያ ልጁን እስከ መስጠት ድረስ ዓለምን እንዲሁ ወዶአልና፤

የዘላለም ማለት ዘላለም ነው፡፡ ማለቂያ የሌለው ማለት ነው፡፡ ኢየሱስ ሲናገር፡

የዘላለም ሕይወት እሰጣቸዋለሁ፤ ከቶ አይጠፉም፤

ከእጄም ሊነጥቃቸው የሚችል ማንም የለም፡፡

መፅሃፍ በዮሃንስ ወንጌል ፡ ላይ እንዲህ ይላል፡

[::.] እውነት እውነት እላችኋለሁ በእኔ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፡፡

ስለዚህ በኢየሱስ ክርስቶስ ካመንክ መፅሃፍ ቅዱስ እንደሚናገረው የዘላለም ሕይወት አለህ፡፡

ለዘላለም ትኖራለህ፡፡ ደህንነትህን ልታጣው አትችልም ዘላለማዊ ስለሆነ፤ የዘላለም ህይወት ነው፡፡

አንዴ ከዳንክ በኋላ፣ አንዴ በርሱ ካመንክ በኋላ፣ ለዘላለም ድነሃል፤

በማኝኛውም ሁኔታ ቢሆን ደህንነትህን አታጣም፡፡ ምንም እንኳን ወደውጭ ወጥቼ አንዳንድ አሰቃቂ ሃጢአቶችን ብሰራ፣

እዚሁ ምድር ላይ እያለሁ እግዚአብሄር ይቀጣኛል፡፡ ዛሬ አንድ ሰው ብገድል

እግዚአብሄር ለሰራሁት ሃጢአት ቅጣትን እንዳገኝ ያደርገኛል፤ ወደ እስር ቤት እገባለሁ ወይም የመጨረሻ ቅጣት በሆነው

በስጋዊ ሞት ቅጣት እቀጣለሁ ወይም ደግሞ አለም በምታደርስብኝ በማንኛውም ቅጣት እቀጣለሁ፡፡

እግዚአብሄር ከዚህም በበለጠ ቅጣት እንድቀጣ ሊያደርገኝ ይችላል፡፡ ነገር ግን ወደ ሲኦል አልገባም፡፡

ወደ ሲኦል ሊያስገባኝ የሚችል ምንም ነገር ማድረግ አልችልም፤ ወደ ሲኦል ገባሁ ማለት እግዚአብሄር ዋሽቷል ማለት ነው ምክንያቱም

በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዳለው ቃል ገብቷልና፡፡

በእኔ የሚያምን እና የሚኖር ከቶ አይሞትም ብሎአል፡፡

ለዚህም ነው ከባድ በደል የሰሩ ሰዎች በመጽሃፍ ቅዱስ ውስጥ እንደ ምሳሌ የተጻፉልን፡፡

ሆኖም እነዚህ ሰዎች ለእግዚአብሄር መንግስቱ በቁ፤ እንዴት? በጣም መልካም ሰዎች ስለሆኑ ነው? አይደለም

በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስላመኑ ነው፤ ሃጢአታቸው ተሸሮላቸዋል፡፡ በዚህ ዓለም ዕይታ መልካም ሕይወት የኖሩ

ወይም በእርግጥ ጥሩ የሚባል ሕይወት ኖረው ነገር ግን

በክርስቶስ ያላመኑ ሰዎች ለሃጢአታቸው ቅጣት ሲኦል ይወርዳሉ፡፡

. ክርስቶስ ብቻውን የግል አዳኝህ አድርገህ እመን

ዛሬ ላቀርበው በምፈልገው በዚህ አንድ ሃሳብ እንዳጠቃልል ፍቀዱልኝ፡፡

ከደቀመዛሙርቱ አንዱ ኢየሱስን የጠየቀው ጥያቄ ነበር፡፡

ጥያቄው እንደሚከተለው ነበር፡ የሚድኑት ጥቂት ናቸውን? ጥሩ ጥያቄ ነው፤ አይደል? ብዙ ሰዎች ይድናሉ?

ወይስ የሚድኑት ጥቂቶቹ ናቸው? በዚህ ምድር ካሉ ሰዎች ውስጥ ብዙዎቹ

መንግስተ ሰማይ ይገባሉ ብሎ የሚያስብ ማነው? መልሱ ምን ይመስላችኋሃል? ኢየሱስ በማቴዎስ ላይ መልሶታል፡

(ማቴዎስ ፡-) በጠባቡ ደጅ ግቡ፤ ወደ ጥፋት የሚወስደው ደጅ ሰፊ፣ መንገዱም ትልቅ ነውና፣

ወደ እርሱም የሚገቡ ብዙዎች ናቸው፡፡

ወደ ሕይወት የሚወስደው ደጅ የጠበበ፣ መንገዱም የቀጠነ ነውና፣ የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው፡፡

ቀጥሎም እንዲህ አለ፡

(ማቴዎስ ፡-) በሰማይ ያለውን የአባቴን ፈቃ የሚያደርግ እንጂ፤ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ የሚለኝ ሁሉ

መንግስተ ሰማያት የሚገባ አይደለም፡፡ በዚያን ቀን ብዙዎች

ጌታ ሆይ በስምህ ትንቢት አልተናገርንም፣

በስምህስ አጋንንትን አላወጣንም፣ በስምህስ ብዙ ታአምራት አላደረግንም? ይሉኛል፤የዚያን ጊዜም፡፡

አላወቅኋችሁም፤ እናንተ ዓመፀኞች ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ፡፡

ከሁሉም በፊት ይህ ዓለም በክርስቶስ እንደሚምን አይናገርም፡፡ ደስ የሚለው፣

ክፍል ውስጥ ያለ አብዛኛው ሰው በኢየሱስ ያምናል፡፡ ነገር ግን አብዛኛው የዚህ አለም ክፍል በኢየሱስ አያምንም፡፡

ግን እግዚአብሄር እያስጠነቀቀ ያለው ነገር በኢየሱስ እናምናለን

ከሚሉት ሰዎች ውስጥ ብዙዎቹ “እነዚህን ሁሉ

አስደናቂ ስራዎች ሰርተናል፡፡ ለምን አንድንም?” ብለው ሲጠይቁት

“አላወቅኋችሁም ከእኔ ራቁ” ይላቸዋል፡፡ ምክንያቱም ደህንነት በስራ ስለማይገኝ ነው፡፡

የራሳችሁ ስራዎች ያድኑኛል ብላችሁ ካመናችሁ፣

በመጠመቃችሁ ምክንያት መንግስተ ሰማያት እገባለሁ ብላችሁ ካሰባችሁ ወይም

“መቼም እኔ እንደማስበው ለመዳን መልካም ሕይወት መኖር አለብህ፤ ትዕዛዛቱን መጠበቅ አለብህ፤ ቤተ ክርስቲያን መሄድ አለብህ፤

ከሃጢአትህ መመለስ አለብህ…” ብላችሁ ካሰባችሁ፣ የራሳችሁን ስራዎች ካመናችሁ፤

አንድ ቀን ኢየሱስ እንዲህ ይላችኋል፡ “አላወቅኋችሁም ከእኔ ራቁ”

ኢየሱስ በመስቀል ላይ በሰራው ስራ ላይ እምነት ሊኖራችሁ ያስፈልጋል፡፡

ለእናንተ ሲሞት፣ ሲቀበርና ከሞት መነሳቱ ላይ ልታምኑ ይገባል፡፡ ይሄ የመንግስተ ሰማያት መግቢያ ትኬታችሁ ነው፡፡

“እንዴ እኔ በጣም ጥሩ የምባል ክርስቲያን ስለሆንኩና

እነዚህ ሁሉ መልካም ስራዎችን ስለማደርግ መንግስተ ሰማያት እግባለሁ” ብላችሁ ካመናችሁ፤ “ከእኔ ራቁ” ይላችኋል፡፡

ጌታ የተናገረውን ልብ በሉ፡ “አላወቅኋችሁም ከእኔ ራቁ”፤ “አውቃችሁ ነበር” አላለም

ምክንያቱም አስቀድሜ እንደገለጽኩት አንዴ ካወቃችሁ የዘላለም ነው፤ ዘላለማዊ ነው፡፡

አንዴ ካወቃችሁ ለዘላለም ድናቹሃል፡፡

ሲኦል ከገባችሁ የገባችሁበት ምክንያት ፈፅሞ ስላላወቃችሁ ነውና “አላወቅኋችሁም ከእኔ ራቁ” ይላል፡፡

አንዴ ካወቃችሁ አወቃችሁ ነው፤ ልክ ልጆቼ ሁሉ ጊዜ ልጆቼ እንደሚሆኑት ማለት ነው፡፡

ዳግም ስትወለዱ፣ ልጁ ስትሆኑ ሁሉ ጊዜ ልጆችሁ ናችሁ፡፡

ምናልባት አስቸጋሪ ልጅ ትሆኑ ይሆናል፤ በዚህ ምድር ላይ በእግዚአብሄር በከባድ ሁኔታ እየታረመ ያለ ሰው ልትሆኑ ትችላላችሁ፤

በዚህ በታች ያላችሁን ሕይወት ልታበላሹ ትችላላችሁ ነገር ግን የላይኛውን ልታበላሹ አትችሉም፡፡ ድናችኋሃል፡፡

የተጠናቀቀ ነገር ነው፤ ስለዚህ ይህ

ስለ መጨረሻው ዘመን ላቀርብላችሁ የምፈልገው ዋና ነገር ነው፡፡

ስለ ደህንነት ወይም ስለ መጨረሻው ዘመን ጥያቄዎች የተወሰነ ደቂቃ አለን፡፡

ውድ ኢየሱስ፤ ሃጢያተኛ እንደሆንኩ አውቃለሁ፤ ለዚህም የሲኦል ፍርድ እንደሚገባኝ አውቃለሁ፤

ነገር ግን አንተ ለኔ በመስቀል ላይ እንደሞትክልኝ እና እንደተነሳህልኝ አመናለሁ፡፡

እባክህ አሁን አድነኝ፤ የዘላለም ሕይወትን ስጠኝ፡፡ አንተን ብቻ አምናለሁ ኢየሱስ፤ አሜን፡፡

 

 

 

mouseover